Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Tuesday, November 6, 2012

በሲዳማ ዞን ቡና አምራች አርሶ አደሮች ተቃውሞ አስነሱ

ኢሳት ዜና:-በደቡብ ክልል፣ ሲዳማ ዞን፣ በንታ ወረዳ ቡና አምራች ገበሬዎች ተቃውሞውን ያነሱት የቡና መሸጫ ዋጋ ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ሆኖአል በማለት ነው።


በትናንትናው እለት ቡና አምራቾች ለቡና ግዢ የሄዱ ነጋዴዎችን በተለያዩ መሳሪያዎች በማስፈራራት ፣ ሚዛኖቻቸውን በመሰባበርና ንብረታቸውንም በመቀማት አካባቢውን ለቀው አንዲወጡ ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሎአል።

የወረዳው ፖሊሶች ተቃውሞውን ለመቆጣጠር ሞክረው ሳይሳካላቸው እንደቀረ ታውቋል።

በአካባቢው ተፈጥሮአል ስለተባለው ግጭት አቶ ሲኤንአ የተባሉትን የአንድ የፖለቲካ ድርጅት አባል አነጋግረን ግጭት መነሳቱንና በአካባቢው ባሉ ቀበሌዎች ተጨማሪ ግጭቶች ሊነሱ ይችላሉ የሚሉ ስጋቶች መኖራቸውን ገልጠዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም ይሁን እንጅ ኢሳት ከሁለት ሳምንት በፊት የዞኑ አርሶአደሮች ተመሳሳይ ቅሬታ መቅረባቸውን የአካባቢውን ባለስልጣን በመጥቀስ ዘግቦ ነበር።

No comments:

Post a Comment