ኢሳት ዜና:- ማክሰኞ ነሐሴ 22 ቀን 2004 ዓ.ም፡-
የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፍትህ ሚኒስትር ፕሬዝዳንት ልዩ ትዕዛዝ በፌዴራል ዐቃቤ ህግ
የቀረበበት ክስ ተቋርጦ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲፈታ በተወሰነው መሰረት ዛሬ ከቀኑ 8 ሰአት ላይ ተፈትቷል።
ምንጮቻችን
እንደገለጹልን በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 16ተኛ ወንጀል ችሎት በዐቃቤ ህግ የቀረበበት ክስ የጋዜጠኛውን
የዋስትና መብት የማያስነፍገው ሆኖ ሳለ ዐቃቤ ህግ በማረሚያ ቤት ሆኖ ክሱን ይከራከርልኝ ስላለ ብቻ የችሎቱ ዳኛ
ማጽደቃቸው እና የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መታሰር፣ እንዲሁም በዕለቱ ችሎት የገዢው ፓርቲ ደጋፊ የሆነው የኢትዮ
ቻናል ጋዜጣ ባለቤት ሳምሶም ማሞ እና የትዳር አጋሩ የተከሰሱበት የንግድ ፈቃድ ሳያድሱ የመስራት ወንጀል በፍትህ
ሚንስትር ዲኤታ ውሳኔ ክሱ እንዲቋረጥ ተደርጎ መሰናበቱ የፍትህ ሥርዓቱን በሀገር ዓቀፍና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ
ያጋለጠና ያሳጣ ጉዳይ ሆኖ በመንግሥት ላይ ኪሳራ አምጥቷል፡፡






