ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
“በኢትዮጵያ የመሪነት ሥልጣን የሚይዘው
ሰው የሚመራበትን ሁኔታ ራሱ መምረጥ ይኖርበታል፡፡ የሚመራበትን ሁኔታ በፓርቲ ማዕቀፍ ውስጥ አስገብቶ መስጠት
የሚመራውን ሰው መናቅ ነው ብዬ ነው የማስበው” ሲሉ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ ተናገሩ።
በፓርላማ
ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ አቶ ግርማ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሞት ሀዘን እንደተሰማቸው በመግለፅ፦”
፤”ከእንግዲህ በሞተ ሰው ላይ እንዲህ ነው- እንዲያ ነው ማለት አስፈላጊ አይደለም፡፡ ሳይሞቱ ቢሆን ኖሮ ብዙ ነገር
መማማር ይቻል ነበር፡፡ በሕይወት እያሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩን፦ አምባገነን፣ ጨካኝ፣ ወዘተ በማለት ብዙ ኃይለ ቃል
ተጠቅመን ገልጸናቸው ይሆናል፡፡ አሁን በሞተ ሰው ላይ ምንም ማለት አስፈላጊም አይደለም”ብለዋል።




