Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Thursday, August 16, 2012

ሰበር ዜና: ቅዱስ ፓትርያርኩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

(ደጀ ሰላም ነሐሴ 10/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 16/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸውን ከሐምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ወሩ መገባዳጃ ሲያከበሩ የቆዩት አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመው ነሐሴ 8 ማምሻውን ወደ ደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ከገቡ በኋላ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ማረፋቸውን ምንጮቻችን እየገለጹ ነው።

Wednesday, August 15, 2012

አቶ ስብሐት ነጋ ስለ አቶ መለስ ዜናዊ በ10 ቀናት ውስጥ መመለስ መናገራቸው ስህተት እንደነበረ ለኢሳት ገለጡ

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
አቶ መለስ ዜናዊ በ10 ቀናት ውስጥ ወደ ስራ ገበታቸው እንደሚመለሱ ከሶስት ሳምንት በፊት ያስታወቁት አቶ ስብሐት ነጋ አባባላቸው ስህተት መሆኑን ለኢሳት ገለጡ።

አቶ በረከት ስምኦን ከአዲሱ አመት በፊት አቶ መለስ ወደ ስራ ገበታቸው እንደሚመለሱ የሰጡትን መግለጫ በተመለከተ ይህንን የማረጋገጥም ሆነ የማስተባበል መረጃ እንደሌላቸው አመልክተዋል።

ኢነጋማ በፍትህ ጋዜጣ ላይ የተወሰደውን እርምጃ በጥብቅ አወገዘ

ኢሳት ዜና:-” ነሀሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የወቅቱ የኢትዮጵያ አስተዳደር የፍትህ ጋዜጣን  ማገዱ፤ በኢትዮጵያ ጭል ጭል ሲል የነበረው የፕሬስ ነፃነት ሙሉ ለሙሉ መዳፈኑን የሚያመለክት ነው” ሰል  ኢነጋማ ገለጸ።

በስደት የሚገኘው የ ኢትዮጵያ ነፃ ጋዜጠኞች ማህበር፦“በፍትህ ጋዜጣና በአዘጋጁ ላይ እየተወሰደ  ያለው እርምጃ፤ በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት መብት ጨርሶ መጥፋቱን የሚያረጋግጥ ክስተት ነው” በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ፤ፍትህ ጋዜጣ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ ብቸኛ የነፃ ፕሬስ አማራጭ በመሆን፤ የህዝብን የማወቅ መብት ተግባራዊ ለማድረግ የተጣለባትን ተጽ እኖና አፈና ተቋቁማ  ስትንቀሳቀስ  መቆየቷን አውስቷል።

ኢራፓ፦”አገሪቷን ማን እንደሚመራት ባለመታወቁ በስጋት እየታመሰች ትገኛለች”አለ

ኢሳት ዜና:-ነሀሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሥራ ላይ አለመሆናቸው ከተነገረና ከተረጋገጠ ጊዜ አንስቶ፣ ኢትዮጵያን ማን እየመራት እንደሆነ ለሕዝብ ይፋ ባለመገለጹ አገሪቱ በወሬ፣ በሐሜት፣ በፍርኀትና በሥጋት እየታመሰች ትገኛለች ሲል የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ ገለጸ።

ኢራፓ ባወጣው ወቅታዊ መግለጫ   አገሪቱ በማን እየተመራች እንደሆነ  ለኢትዮጵያ ህዝብ በግልጽ እንዲነገረው አሣስቧል።
ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
 “ጠቅላይ ሚ/ር መለስ ዜናዊ ዞር ሲሉ፤ ግብፆች ፦” ኢትዮጵያውያን ከጥቅማቸው በተቃራኒ ይቆማሉ” ብለው ማሰባቸው ስህተት ነው” ሲሉ አንድ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣን ተናገሩ፡፡

በኢፌድሪ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የኮሙኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ረዳ ይህን ያሉት፤ አንድ የግብጽ የመስኖ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን የዛሬ ሳምንት ፦” ከመለስ ዜናዊ በሁዋላ የሚኖረው አዲሱ የኢትኦጵያ አመራር -ከአዲሶቹ ከግብጽ መሪዎች ጋር በጋራ  በመሆን  በዓባይ ወንዝ ምክንያት  በአገሮቹ መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ያረግቡታል የሚል እምነት አለኝ” ማለታቸውን ተከትሎ ነው።

አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር 16 በመቶ ጨመረ

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ግብርና ሚኒስቴር እና የውጭ ለጋሾች ትናንት በጋራ ያቀረቡት ሰነድ እንደሚያሳየው ከሀምሌ እስከ ታህሳስ ወር ባለው ጊዜ ውስጥ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር ከ3 ሚሊዮን 200 ሺ ወደ 3 ሚሊዮን 700 ሺ ከፍ ብሎአል። ለእነዚህ ተረጅዎች ከ189 ሚሊዮን ዶላር ወይም ከ3 ቢሊዮን 4 መቶ ሚሊዮን በላይ ብር እንደሚያስፈልግ ታውቛል።

41 በመቶ የሚሆኑት ተረጅዎች በሶማሊ፣ 27 በመቶ በኦሮሚያ፣ 10 በመቶ በትግራይ፣ 8 በመቶ በአማራና በደቡብ፣ እንዲሁም 4 በመቶ በአፋር ክልል ይገኛሉ። በአጠቃላይ 193 ሺ 866 ሜትሪክ ቶን ምግብ እንደሚያስፈልግ በሰነዱ ተመልክቷል።

Tuesday, August 14, 2012

የአዜብ መስፍን እህት ሰርግ ተሰረዘ

የኢሳት ዜና የጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ቤተሰቦች ለመስከረም 10 ታቅዶ የነበረ ሰርግ እንዲሰረዝ ማድረጋቸውን ታማኝ የኢሳት ምንጮች ጠቁመዋል።

ከጠቅላ  ሚኒስትሩ ደብዛ መጥፋት ጋር በተያያዘ በቤተመንግስት አከባቢ በተፈጠረው ቀውስና ትርምስ የተጨነቁት እነዚሁ የቤተሰብ አባላት የወ/ሮ አዜብ ታናሽ እህት ሶሻል ይልማ ሰርግ ለመሰረዝ መገደዳቸውን  ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የኢሳት ምንጮት ጠቁመዋል።

ሰራዊቱ አሁንም በአንደኛ ደረጃ ተጠንቀቅ ላይ ነው

የኢሳት ዜና: የአቶ መለስ ዜናዊን መሰወር ተከትሎ በኢትዮጵያ ያለው ውጥረት እንደቀጠለ ሲሆን፤ ጦር ሰራዊቱ በአንደኛ ደረጃ ተጠንቀቅ እንዲቆም የታዘዘው፤ በቅርቡ በተመሰረተውና በጦር ሰራዊቱ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ውይይት በጫረው ነጻ የኢትዮጵያ ሰራዊት ንቅናቄ (ነኢሰን) መግለጫ ጭምርም እንደሆነ አስተማማኝ የውስጥ ምንጭ ገለጸ።

ለመከላከያ ሚኒስቴር ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ በቅርቡ የተመሰረተበትን መግለጫ የበተነው ነጻ የኢትዮጵያ ሰራዊት ንቅናቄ፤ ከተመሰረተ ግዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ውስጥ ከፍተኛ ውይይት እንደጫረና፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አለመኖር ታክሎበት ስጋት በመፍጠሩ ምክንያት፤ አየር ሀይሉን ጨምሮ የጦር ሰራዊቱ በሙሉ በአንደኛ ደረጃ በተጠንቀቅ እንዲቆም መደረጉ ታውቋል።

(Breaking News) Abune Paulos hospitalized ፓትርያርኩ በጠና ታመዋል


. ማምሻውን ወደ ባልቻ ሆስፒታል ገብተዋል

(Deje Selam, August 14/2012):- Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tehwadeo Church, His Holiness Abune Paulos, is hospitalized today at Balcha Hospital.  Sources close to the Patriarchate say "he is in critical condition". The patriarch has been attending medications for a long time. Detail news coming soon. Stay tuned.

(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 8/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 14/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸውን ከሐምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ወሩ መገባዳጃ ሲያከበሩ የቆዩት አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመው ምሽቱን ወደ ደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል መግባታቸው ተሰማ፡፡

አቦይ ስብሐት “አዲስ አድማስ ጋዜጣ ውሸቱን ነው መለስ በቤታቸው የሉም” አሉ


ስለ አቶ መለስ ዜናዊ ማውራት ደክሞኝ ነበር። ሳስበው ሳስበው እርሳቸው የሆኑትን ሆነው ደከመኝ ሳይሉ እኔ እንዴት ደከመኝ እላለሁ ብዬ ተፀፅቻለሁ። መቅደላዊት የተባለች ወዳጄም ከሪያድ በሰደደችልኝ አስተያየት ሀዘኑን እንረሳው ዘንድ ስለርሳቸው መጨዋወታችንን እንቀጥል እንጂ ድንኳን ሳይነሳ የምን ዝም ዝም ነው የሚል ወቀሳ ሰንዝራልኛለች። እኔም በሆዴ የምን ሀዘን ብዬ ሳበቃ  “እውነት ግን ምን ነካኝ…!” ብዬ ሂሴን ውጫለሁ!