ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ የ አቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤት ከሳዑዲ ዓረቢያ የሃይማኖት አታሼ ቢሮ ገንዘብ ይዘው ሲወጡ ተይዘው መታሰራቸውን ሰንደቅ ጋዜጣ ዘገበ።
ጋዜጣው ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ጁነዲን ሳዶ ባለቤት ወ/ሮ ሃቢባ መሐመድ መሐሙድ ፤በወረዳ 17 ወርቁ
ሕንፃ አጠገብ ከሚገኘው ከሳዑዲ ዓረቢያ የሃይማኖት አታሼ ቢሮ ግምቱ ከሃምሳ እስከ መቶ ሺ ብር የሚገመት የታሰረ
ገንዘብ እና በዓረብኛ የተፃፉ መፅሐፍት ይዘው ሲወጡ በፌዴራል ፖሊስ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።









