Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Tuesday, July 17, 2012

የአውሮፓ ህበረት በእነ አቶ አንዱለአም አራጌ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ አወገዘ

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ህብረቱ ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኞችን እና የተቃዋሚ መሪዎችን አወዛጋቢ በሆነው የጸረ ሽብርተኝነት ህግ ሰበብ አድርጎ ማሰሩ በአለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ሳይቀር እንዲተች አድርጎታል።

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሀላፊ የሆኑት ካተሪና አሽተን የፍርድ ሂደቱን አዲስ አበባ በሚገኙ ዲፕሎማቶች አማካኝነት ሲከታተሉት መቆየታቸውን ያወሳው የህብረቱ መግለጫ፣ ምንም እንኳ ኢትዮጵያ ራሱዋን ከሽብረተኝነት የመከላከል መብት ቢኖራትም ፣  የጸረ ሽብረተኝነት ህጉ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ሳይቀር እንደ ሽብር መመልከቱ ጉዳዩን አሳሳቢ አድርጎታል።


 ካተሪና አሽተን በእስረኞች ላይ የተላለፈው ውሳኔ በእጅጉ እንዳሳሰባቸው መግለጫው አትቷል። ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ የሆኑ የአውሮፓ ህብረት ዲፕሎማቶች በኮተኑ ስምምነት መሰረት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በሚያደርጉት ድርድር፣ ለሰብአዊ መብትና ለፕሬስ ነጻነት ትኩረት እንዲሰጡ አሽተን አሳስበዋል።

በአቶ አንዱአለም አራጌ መዝገብ በተከሰሱት ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ላይ የተላለፈውን ውሳኔ የአሜሪካ መንግስትን ጨምሮ በርካታ አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች አውግዘውታል።


No comments:

Post a Comment