Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Tuesday, July 17, 2012

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ አበባ መግባት እና የፖለቲካው አሰላለፍ

ቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ አበባ መግባት እና የፖለቲካው አሰላለፍ

ህመማቸው ፀንቶ ቤልጂየም ሀገር በመታከም ላይ ይገኙ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ትላንትና ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል። ሕይወታቸው እንዳለፈ ሲነገር የነበረው አቶ መለስ ወደ ቤተመንግስታቸው የተመለሱት ‹‹ከህመማቸው አገግመው›› ይሁን ወይም ‹‹ከዚህ በኋላ በህክምናው አትድንም ተብለው በተስፋ መቁረጥ›› ይሁን እስከ አሁን ለማረጋገጥ አልቻልኩም። የተረጋገጠው በህይወት መግባታቸው ብቻ ነው፡፡

የአቶ መለስን መታመም ተከትሎ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ አራት ሀይሎች ‹‹በሸዋ ፖለቲካ›› ጥበብ ግብግብ ገጥመዋል። በእርግጥ አንደኛው ሀይል (ቡድን አንድ) የበላይ የመሆን ዕድሉን እያሰፋ ነው። 

(እኔ ካገኘሁት መረጃ አንፃር አሸናፊው ቡድን እንዲህ አይነት ገፅታ ሊኖረው ይችላል፡፡ አቀራረቤም በአገኘሁት መረጃ ላይ ተንተርሼ ለመተንተን የሞከርኩት ነው፡፡ መቼም የህወሓት ባህሪ ሊጨበጥ እንደማይችል ሁላችንም እናውቀዋለን)
የኃይል አሰላለፉም እንደሚከተለው ነው፡

ቡድን-1. 

የቡድኑ አስተባባሪ አቦይ ስብሃት ነጋ ሲሆኑ
የቡድኑ ቁልፍ ሰዎች
1. ስዩም መስፍን
2. ብርሃነ ክርስቶስ
3. አባይ ፀሐዬ
4. አባይ ወልዱ (የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት)
5. ጄኔራል ሳሞራ የኑስን ጨምሮ በርካታ ጄኔራሎች
ይህ ቡድን ካሸነፈ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን አለመመለሳቸውን ካረጋገጠ፡-
በጠቅላይ ሚኒስትርነት ኃይለማርያም ደሳለኝን
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ም/ጠ ሚኒስትርነት ደግሞ ብርሃነ ክርስቶስን ለማድረግ ወስኖአል።

ቡድን-2. 

የቡድኑ አስተባባሪ አዜብ መስፍን እና በረከት ስምኦን ሲሆኑ
ይህ ቡድን በርካታ ሚኒስትሮችን፣ ጥቂት የህወሓት አመራሮችን እና ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖምን ያካተተ ሲሆን፣ ብአዴንን ሙሉ በሙሉ ከጎኑ ማሰለፍ የቻለ ይመስላል። በአሁኑ ሰዓት በሀገሪቱ ላይ የተሻለ ስልጣንም አለው።
ይህን ቡድን ካሸነፈ ኩማ ደመቅሳን/ ሀይለማሪያም ደሳለኝን ጠቅላይ ሚኒስትርነት ያደርጋል። 

ቡድን-3. 

ኦህዴድ ሲሆን፣ የዚህ ቡድን አስተባባሪ ተለይቶ አይታወቅም። ከኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች (ህወሓት፣ ብአዴን እና ደኢህዴን) ጋርም እየሰራ አይደለም።  ዕድል ከቀናው ጠቅላይ ሚኒስትር ኩማ ደመቅሳን ያደርጋል። 

ቡድን-4. 

የዚህ ቡድን አስተባባሪ የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ አለቃ ፀጋዬ በርሄ ሲሆኑ፣
ቁልፍ የሃይል ሚዛናቸው የደህንነት ሀላፊውን (ጌታቸው አሠፋን) ከጎናቸው ማድረጋቸው ነው። (በነገራችን ላይ አቶ መለስ ባይታመሙ ኖሮ የደህንነት ሚንስትሩን የመቀየር ሃሳብ እንደነበራቸው ይነገራል)
ይህ ቡድን ካሸነፈ ጠቅላይ ሚኒስትር ለማድረግ ያሰበው ኃይለማርያም ደሳለኝን ነው። 

በእርግጥ ይህ ቡድን ላይ ብዙዎች ጥርጣሬ አላቸው። ምክንያቱም የቡድኑ አስተባባሪ አለቃ ፀጋዬ የአቦይ ስብሃትን ታናሽ እህት ቅዱሳን ነጋን ያገቡ ከመሆኑም በላይ በአሁኑ ሰአት ለብቻ የተገነጠሉ እንዲመስሉ የተደረገውም የእነ አቦይ ቡድን ማቀፍ ያልቻለውን የህወሓት አመራር እና ሌሎች ቁልፍ ሰዎችን እንዲሰበስብና ሀይል እንዳይበታተን ለማድረግ የታቀደ ነው እያሉ ነው።

(አለቃ ፀጋዬ በ1993ቱ ክፍፍል ወቅትም እንዲህ አይነት ሚና ተጫውተዋል። እስከመጨረሻው ዕለት ድረስ ከእነስዬ ቡድን ጋር እንደቆሙ ሲናገሩ ቆይተው በመጨረሻዋ ዕለት ወደ እነ መለስ ቡድን ገብተዋል። ለዚህም ነው በ2002ቱ ምርጫ ወቅት መድረክ በመቀሌ በጠራው ስብሰባ ላይ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ‹‹አለቃ ፀጋዬ ማታ ዕራት ከእኛ ጋር በልቶ ለቁርስ ከእነ መለስ ጋር አገኘነው›› ያሉት)

Source: Temesgen Desalegn Face book

No comments:

Post a Comment