Ethio-train construction |
ከአውሮፓ ህብረት በተገኘው 41 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 1 ቢሊዮን ብር ከኢትዮጵያ ጅቡቲ ያለውን 114 ኪሎሜትር የባቡር ሀዲድ ለማስገንባት ስምምነት ተፈርሞ የነበረ ቢሆንም ፣ ኮንስታ የተባለው ኩባንያ ሰርቶ ያስረከበው 24 ኪሎሜትር ብቻ መሆኑን፣ ይህም ቢሆን አገልግሎት ላይ አለመዋሉን ጠቅሷል።
ኢሳት
የህዝባዊ ወያን ሀርነት ትግራይ ንብረት የሆነው መስፍን ኢንጂነሪንግ በሀዲድ አምራችነት እንደተሳተፈ አድርጎ
ያቀረበው ዘገባ ትክክል አለመሆኑን የጠቀሰው ደብዳቤ፣ መስፍን ኢነጂነሪንግ ስምምነት የተፈራረመው በመንገዱ ላይ
ያሉትን 9 አዳዲስ ድልድዮችን ለመስራትና 40ዎችን ደግሞ የማጠናከር ስራ ለመስራት መሆኑንና ሀዲዶቹ ከጣሊያን አገር
ተጭነው መምጣታቸውን ገልጧል።
ኮስታ ኩባንያ ከታክስ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ አይን እንደተጣለበት አንድ ደይሊ የተባለ የጣሊያን ጋዜጣ ዘግቧል። ማቲዮሊ፣ ኤስቲ ኢነርጂ፣ ሶልስ እና ኢሶዲል የተባሉ ኩባንያዎችን አቅፎ የያዘው ኮንስታ ከድሬዳዋ እስከ ሽንሌ ያለውን 10 ኪሎሜትር እንደነገሩ አድረጎ በማጠናቀቅ ካሳምንት በፊት ማጠናቀቁን ማስረከቡን መዘገባችን ይታወሳል።
ሥራው እንደተጀመረ ተቆጣጣሪ መሐንዲስ በመሆን በትውልድ ኢትዮጵያዊና በዜግነት ስፔናዊ የሆኑ አቶ አስረስ ኪዳኔ የተባሉ ባለሙያ ሥራው በጥራት እየተሰራ አለመሆኑን፣የድልድይ ግንባታ ሥራ በዘርፉ ልምድ ለሌለው መስፍን ኢንጂነሪንግ የተባለው የህወሀት የንግድ ድርጅት መሰጠቱን በመቃወማቸው ምክንያት አለመግባባት ተፈጥሮ ሥራውን ጥለው ለመውጣት መገደዳቸውን መዘገባችን ይታወቃል በአሁኑ ሰዓት የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር በኪሳራ ላይ በመሆኑ በኢትዮጵያ በኩል ሰራተኞቹን ብቻ ተቀብሎ የሚያስተዳድረው የብረታብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሸን የሚባለው ተቋም ነው፡፡
የኢትዮጵያ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርም ደሳለኝ ከሳምንት በፊት በፓርላማ ተገኝተው የመንግስታቸውን አቋም በገለጹበት ንግግራቸው አጓጊ ካሏቸው ፕሮጀክቶች መካከል ባቡር አንዱ ሲሆን አፈጻጸሙም በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ መግለጻቸው ይታወሳል።
መንግስት በአምስት አመቱ የልማት እቅድ ውስጥ
ሊሰራቸው ከሚያስባቸው የሀዲድ እና የመንገድ ግንባታዎች ውስጥ የህወሀት ኩባንያዎች በስፋት እየተሳተፉ መሆኑ
ይታወቃል። ብሉምበርግ በቅርቡ እንደዘገበው ሌላው የህወሀት ኩባንያ የሆነው ሱር ኮንስትራክሽን ባለፈው አመት ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማግኘቱን መግለጹ ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment