Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Wednesday, October 31, 2012

በማረቃ ወረዳ የየኔሰው ገብሬ ጓደኛ የሆነው ወጣት ራሱን በአደባባይ ሰቀለ

Yenesew Gebre best Friend hang himself
ኢሳት ዜና:-በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ በኢኮኖሚክስ የትምህርት ክፍል የሜዳሊያ ተሸላሚ  የነበረው ወጣት ግርማ ወ/ማርያም ራሱን በአደባባይ ለመስቀል የተገደደው በአካባቢው ያለውን የመልካም አስተዳዳርና የፍትህ እጦት በመቃወም መሆኑን ጓደኞቹና ቤተሰቦቹ ለኢሳት ገልጠዋል።

በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ክልል ፣ በዳውሮ ዞን ፣በማረቃ ወረዳ ፣ በዋካ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ወጣት ግርማ ወ/ማርያም፣ በ1980 ዓም ነበር የተወለደው ። የ10ኛ ክፍል ትምህርቱን 3 ነጥብ 8 በማምጣት  በአንደኝነት አጠናቆ ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ መግባቱንና የኢኮኖሚክስ ትምህርቱን በከፍተኛ ውጤት ማጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል።


ትምህርቱን እንዳጠናቀቀም በማረቃ ወረዳ በታክስና አስተዳዳር ተቀጥሮ መስራቱን፣  ይሁን እንጅ በስራ ላይ እያለ ከፍተኛ የሆነ የአስተደዳር በደል እንደደረሰበት በተለይም ወጣት የኔሰው ገብሬ ራሱን በማቃጠል ከገደለ በሁዋላ ወጣቱ የየኔሰውን ጥያቄዎች ያቀነቅናል በሚል ከፍተኛ ጫና ሲደርስበት እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ። የወረዳው ባለስልጣናትም ወጣት ግርማ ከስራው እንዲታገድ በማድረግ ለ4 ወራት ያክል ምንም ክፍያ ሳያገኝ ያለስራ እንዲቀመጥ አድርገዋል። 

ወጣት ግርማ ወደ ባለስልጣናት በተደጋጋሚ በመመላለስ መፍትሄ ለማግኘት ጥረት ቢያደርግም ሊሳካለት ባለመቻሉ ባለፈው አርብ ራሱን በአደባባይ በገመድ በመስቀል አጥፍቷል። ኢሳት ከወጣት ግርማ ወ/ ማርያም ቤተሰቦች ጋር ቃለምልልስ አድርጓል። በሌላ በኩል የማረቃ ወረዳ  አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ መላኩ ወጣት ግርማ ወ/ ማርያም በመልካም አስተዳዳር እጦት ራሱን አጥፍቷል የሚለውን እንደማይቀበሉት ለኢሳት ገልጠዋል።

በማረቃ ወረዳ ነዋሪ የነበረው የኔሰው ገብሬ ፍትህና መልካም አስተዳዳር በሌለበት ሁኔታ መኖር አልፈልግም በማለት ራሱን በቤንዚን አቃጥሎ መግደሉ ይታወሳል። ወጣት የኔሰው ራሱን ካጠፋ በሁዋላ ከ6 ያላነሱ የአካባቢው ሰዎች ራሳቸውን በተለያዩ መንገዶች ማጥፋታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። 

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ ሰው ወጣት ግርማ ከመሞቱ በፊት ወረቀት ጽፎ እንደነበር፣ ፖሊሶች በፍጥነት ደርሰው ወረቀቱን እንደወሰዱበት ተናግሯል።  ከዚህ ቀደም በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሰጠሁት መግለጫ ችግር ደርሶብኛል ያለው ወጣት እንደገለጠው ፣ የወታት ግርማ ወ/ ማርያም ቤተሰቦች በተቃዋሚነት በርካታ ችግሮች ደርሶባቸዋል። በማረቃ ወረዳ ከወረዳና ከመልካም አስተዳዳር እጦት ጋር በተያያዘ ተደጋጋሚ ችግሮች መኖራቸውን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment