ኢሳት ዜና:-የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት 4ኛ ወንጀል ችሎት ትናንት 4፡30 ላይ ጀምሮ ማእከላዊ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ሙስሊም ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ እና የሀይማኖት መብታችን ይከበርልን ባሉ ሼሆችና ኡላማዎች ላይ የፌደራሉ አቃቢ ህግ ክስ ከመሰረተባቸው ሰዎች መካከል አንዷ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒሰትሩ ባለቤት የሆኑት 28ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ ሀቢባ ሙሀመድ መሆናቸው ታውቋል።
በክስ
ቻርጁ ላይ ” ተከሳሽ ሀቢባ ሙሀመድ ከ27ኛ ተከሳሽ አብዱራህማን ኡስማን ጋር በመገናኘትና 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን
ብር በላይ በመቀበል ከመጅሊስ እውቅና ውጭ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ አክራሪነትን በማስፋፋትና ቦታውን በማስገንባትና
በአዲስ አበባ ከሚገኘው የሳውዲ አረብያ ኢምባሲ የሀይማኖት ክፍል ግንኙነት በመፍጠር ለአክራሪነት ማስፋፊያ የሚሆን
በ9?11?2004 ዓም 50 ሺ ብር በመቀበል እንዲሁም ለህገወጥ አላማ እየተጠሩ የነበሩትን የሰደቃ ፕሮግራም
ለመደገፍ የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ይዛ ስትንቀሳቀስ እጅ ከፍንጅ ” መያዛቸውን ይገልጣል።
በአሁኑ ሰአት ታይላንድ ባንኮክ የሚገኙት አቶ ጁነዲን ሳዶ የባለቤታቸውን መታሰር በመቃወም አንድ ጽሁፍ በጋዜጦች ላይ ማውጣታቸው ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment