Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Sunday, October 28, 2012

አርበኞች ግንባር በሰሜን ጎንደር ጭልጋ ወረዳ የተሳካ ወታደራዊ ማጥቃት አካሄደ

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በጥቅምት 15-2005 ዓ.ም ከወያኔው የመከላከያ ሰራዊትና ሚሊሻ ጋር በሰሜን ጎንደር ጭልጋ ወረዳ ልዩ ስሙ ዳንጉራ በሚባል ስፍራ በወሰደው

ድንገተኛ ወታደራዊ ማጥቃት አስር(10) የስርዓቱን ቅጥረኛ ወታደሮች በመግደልና አምስት (5) በማቁሰል በአናሳው ቡድን የሃይል ጣቢያ ላይ ከፍተኛ ድልን ተጎናጽፏል።

በእለቱ በአካባቢው ሲንቀሳቀስ የነበረው ነበልባል ሻምበል በወሰደው ድንገተኛ ማጥቃትና በተመዘገበው ድል በአካባቢው የሚኖረው ማህበረሰብ አንጀቱ መራሱንና ወያኔው በአሁኑ ወቅት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ እያወረደ በሚገኘው የጅምላ ጭፍጨፋና እስራት በንፁሃን የሙስሊም ሃይማኖት ተከታዮች ውስጥ በሃይማኖት ጉዳዮች በመግባት የእምነቱ መሪዎችን ፣ የእምነቱ አግልጋዮችና አዳሪዎች ሳይሆኑ በሃይማኖት ሽፋን የአገዛዙ የፕሮፓጋንዳ አስተጋቢዎችና የፖለቲካ ሹሞች መሆን ይኖርባቸዋል በማለት እብሪተኛው ቡድን የራሱን ሰዎች የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች እንዲሆኑ ያለ የሌለ ሃይሉን በመጠቀም የሃይማኖት ነፃነት ያስጠብቃል ተብሎ የወጣው የይስሙላ ሕገ-መንግስት የሰጠውን መብት እንኳን ሕዝበ-ሙስሊሙ ሊከበርለት አልቻለም።

ይህን ጉዳይ ሕዝበ-ሙስሊሙንም  ሆነ የሌላ ሃይማኖት ተከታይ የሆነው ኢትዮጵያዊ ሁሉ አግባብነት የሌለው ጭፍን እርምጃ መሆኑን በአደባባይ እየመሰከሩና ከአምባገነኑ ስርዓት ጋር በተቃውሞ ትዕይንት ፊት ለፊት እየተጋፈጠ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ነበልባል በመባል የሚታወቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ከሰሜን ጎንደር ጭልጋ ወረዳ በወያኔው መከላከያና ሚሊሻ ታጣቂ ሃይል ላይ ከወሰደው ወታደራዊ ማጥቃት ባሻገር በአካባቢው ለሚገኘው ማህበረሰብ በወቅታዊ የወያኔው የግፍ አገዛዝን አስመልክቶ እንዲሁም የድርጅቱን ዓላማና እንቅስቃሴ ገለፃ አድርጓል።

በስብሰባው የተገኙ በግብርናና በንግድ ስራ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች ለግንባሩ እያደረጉት የሚገኘውን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚገፉበት በቃላቸው አረጋግጠዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ የድርጅቱ በራሪ ወረቀቶችና መጽሄቶች በጎንደር ጭልጋ፣ መተማና ወልቃይት ፣ በባህር ዳርና በመዲናችን አዲስ አበባ በከፍተኛ ሁኔታ ተበትኗል።

No comments:

Post a Comment