ኢሳት ዜና:- ሰኔ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በትናንትናው እለት የክልሉ መስተዳደር ሀላፊ የሆኑት
አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የአዋሳ ከተማ ነዋሪዎችን በአዋሳ ባህል አዳራሽ ውስጥ በሰበሰቡት ወቅት ነው ውዝግቡ የተፈጠረው።
አቶ ሽፈራው ” ሲዳማ ክልል እንዲሆን የጠየቃችሁት መቼውንም አይሳካም ቁርጡን እወቁት ” በማለት ሲናገሩ
ተሰብሳቢው ተቃውሞውን ገልጧል።
በአዋሳ ተወልደው የኖሩ የሲዳማ ብሄረሰብ ተወላጅ ያልሆኑ የከተማው
ነዋሪዎች ” እኛን የሲዳማ ህዝብ አላጠቃንም፣ ሲዳማ እኛን አይጠላንም፣ እኛን እያስጠቃን ያለው አመራሩ የሚያወጣው
ህግ ነው፣ እኛ ተከባብረን፣ ተዋልደን የምንኖር ህዝብ ነን” በማለት አስተያየት ሲሰጡ፣ ከሲዳማ ተወላጆች በስተቀር
የሌላ አካባቢ ተወላጆች አዳራሹን ለቀው እንዲወጡ አቶ ሽፈራው ሲናገሩ ነው፣ ውዝግቡ የተፈጠረው።
የከተማው
ነዋሪዎችም እኛ የትም አንሄድም፣ ብትፈልጉ እንደ ጓደኞቻችን እዚሁ እሰሩን በማለት ሲቃወሙ ከዋሉ በሁዋላ አንድ
ሽማግሌ ” ህዝቡ አልቆ ሲዳማ የሚለው ስም እሲኪሰረዝ ድረስ ትግላችንን አናቆምም፣ ጥያቄያችን እስኪመለስ ድረስ”
በማለት ተናግረው አዳራሹን ለቀው ሲወጡ፣ ህዝቡም ተከትሎአቸው ወጥቷል።
በስብሰባው ላይ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ
በሲዳማ ተወላጆችና በሌሎች ነዋሪዎች መካከል ልዩነት በመፍጠር ግጭት እንዲፈጠር ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም
አልተሳካለቸውም ሲል በአዳራሹ የተገኘው ዘጋቢያችን ገልጧል። ህዝቡም በግልጽ ከሌሎች ወንድሞቻችን ጋር ልታጋጩን
አትሞክሩ በማለት ተቃውሞውን አሰምቷል።
በቡድን የተደራጁት የአዋሳ ወጣቶች ህዝቡን እያስመቱ የሚገኙ
የመንግስት ባለስልጣናት የሚል በርካታ ስም ዝርዝሮችን የያዙ ወረቀቶችን እየበተኑ ነው። የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች
የሚመሩት የአዋሳ የወጣቶች ድርጅት በህእቡ መመስረቱን፣ አንድ የድርጅቱ አመራር ለኢሳት ዘጋቢ ተናግሯል። ይህ
ድርጅት ባ 14 ገጽ ወረቀትም በከተማዋ በትኖአል።
በሌላ ዜና ደግሞ በትናንትናው እለት በጩኮ ከተማ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የታሰረው ሰው ቁጥር 15 ደርሷል። የፌደራል ፖሊሶች ሶስት ሆነው የሚቆሙ ወይም የሚጓዙ ሰዎችን ይበትናሉ። የጭኮ ተወላጆች “አፊኒ” በሚባለው ባህላቸው መሰረት በሂደት ስለሚወስዱት እርምጃ ከጎሳ መሪዎች ጋር ለመነጋገር ወደ ገጠር እየተጓዙ መሆኑንም ዘጋቢያችን ገልጧል።
በሲዳማ
ዞን ከአዋሳ ከተማ እጣ ፋንታና ከዞን ጥያቄ ጋር የተነሳው ውዝግብ እየተካረረ በመሄድ ላይ ነው። በትናንትናው
እለት የችኮወረዳ የፖሊስ አዛዥ ን ጨምሮ ታዋቂ ባለሀብቶች እና የመንግስት ሰራተኞች መታሰራቸውን መዘገባችን
ይታወሳል። በርካቶች የዘር ፖለቲካው አስከፊ ገጽታ የኢትዮጵያን ህልውና አደጋ ውስጥ እየከተተው መምጣቱን ይናገራሉ።
No comments:
Post a Comment