Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Tuesday, July 24, 2012

እነ ናትናኤል መኮንን ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተዛወሩ

                            -አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር ለብቻቸው ታሰሩ
በእነ አንዱዓለም አራጌ የክስ መዝገብ ተከሰው በቅርቡ የተፈረደባቸው የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ም/ ቤት አባል መምህር ናትናኤል መኮንን፣ የቀድሞ የፓርላማ አባል አቶ አንዱዓለም አያሌው የአንድነት ፓርቲ የባህር ዳር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሻምበል የሺዋስ ይሁንዓለም፣ አቶ ክንፈሚካኤል ደበበ/አበበ ቀስቶ/ ፣ አቶ ዮሐንስ ተረፈና አቶ ምትኩ ዳምጤ ከነበሩበት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከፍተኛ ጥበቃ ወዳለበት ቂሊንጦ ወደሚገኘው እስር ቤት መዛወራቸውን ቤተሰቦቻቸው ለዝግጅት ክፍላችን
ገልፀዋል፡፡ 


 ምንጮች እንደገለፁት በክስ መዝገብ ውሳኔ ከተሰጣቸው ውስጥ በአሁኑ ጊዜ ቃሊቲ እስር ቤት ያሉት አቶ አንዱዓለም አራጌና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ናቸው ተብሏልል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በእነ ኤልያስ ክፍሌ የክስ መዝገብ ተከሰው 17 ዓመት እስራትና 50 ሺህ ብር ቅጣት ተወስኖባቸው በቂልንጦ እስር ቤት የሚገኙት የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ /ኢብአፓ/ ፕሬዘዳንት አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር ከነበሩበት ዞን ሁለት እስር ቤት ወጥተው እዚያው ቂሊንጦ እስር ቤት በተለምዶ ግንቦት ሰባት በሚባል ግቢ ለብቻቸው ታስረው እንደሚገኙ ታማኝ ምንጮቻችን ለዝግጅት ክፍላችን ገለፁ፡፡

የውስጥ አዋቂዎች ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጹት ‹‹እዚህ ማረሚያ ቤት ውስጥ እስረኞችን ታሳድማለህ፤ እስላሞች እንዲበጠብጡ የምታስደርገው አንተነህ›› ተብለው ቢሮ ተጠርተው የተጠየቁ ሲሆን እሳቸው ‹‹እኔ ማንንም ለአድማ አልቀሰቀስኩም፤ እዚህ በእናንተ ጥበቃ ስር ማረሚያ ቤት ውስጥ ተቀምጬ ሙስሊሞችን የማደራጅበትና እንዲረብሹ የምቀሰቅስበት አቅምም መንገድም የለኝም፡፡ እኔን ማጉላላት የምትፈልጉበት ጉዳይ ካለ የምትፈልጉትን ማድረግ ትችላላችሁ
ብለው›› መልስ ሰጥተዋቸዋል፡፡ 

ከዚያም ከነበሩበት እስር ቤት አውጥተው ልዩ እስር ቤት ውስጥ ለብቻቸው እንዲታሰሩ ተደርገዋል፡፡››
ብለዋል፡፡ ስለ ጉዳዩ የአቶ ዘሪሁን ቤተሰብ ሐሳብ እንዲሰጡን ብንጠይቅ ለብቻው መታሰራቸውን አምነው በሌላ ጉዳይ ምንም ዓይነት አስተያየት መስጠት እንዳማይፈልጉ ገልፀዋል፡፡

No comments:

Post a Comment