ወጣቶች በነፃነት ለመደራጀት ጥሪ እያቀረቡ ነው።
የባለራዕይ ወጣቶች ማኅበር የተሰኘ ስብስብ በነፃነት ለመደራጀት አደረግኹ ያለው ጥረት እንቅፋት እንደገጠመው አስታውቋል። በአዲስ አበባ አሥሩም ክፍለ ከተሞች ለማካሄድ ካቀዱት የምክር ቤቶች ምሥረታ የመጀመሪያ የሆነው ስብሰባ በፀጥታ ኃይሎች መበተኑን ወጣቶቹ ገልፀዋል።
ጥር 14 ቀን 2004 ዓ.ም የበጎ አድራጎትና ማኅበራት ኤጄንሲ የሰጠው የምዝገባ ፈቃድ የምሥክር ወረቀት እንደሚያሣየው ባለራዕይ የኢትዮጵያ ወጣቶች ማኅበር የኢትዮጵያ ማኅበር ሆኖ ተመዝግቧል። ወጣቶቹ ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ እንደገለፁትም ከዚህ ማኅበር አመራር አባላት አብዛኞቹ እስከ ቅርብ ዓመታት ድረስ የገዥዉ ፓርቲ አባላትና የወጣት ማኅበራት መሪዎች የነበሩ ናቸው።
የዚሁ ማኅበር አመቻች ኮሚቴ ሊቀመንበር ሀብታሙ አያሌው ለምሳሌ ከ1999 ጀምሮ የአዲስ አበባ ወጣቶች ፎረም
ሊቀመንበር ሆኖ አገልግሏል። ከ2001 ጀምሮ ደግሞ የኢህአዴግን የወጣት ሊግ ጨምሮ የተለያዩ ማኅበራትን ያቀፈውን
የአዲስ አበባን ወጣቶች ፌዴሬሽን በፕሬዚዳንትነት መርቷል።
ማኅበራቱ ነፃ ሆነው መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው ግን ከገዥው ፓርቲ አባልነትና ከፎረሙ ሊቀመንበርነት እራሱን ማግለሉን አብራርቷል። ዝርዝሩን ከእስክንድር ፍሬው ዘገባ ያድምጡ።
(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከማጫወቻዎቹ አንደኛውን ብቻ አስቀርተው የቀሩትን ያቁሟቸው፡፡)
No comments:
Post a Comment