Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Saturday, July 7, 2012

በጎሳ ግጭት ከ40 በላይ ሰዎች አለቁ ግጭቱ እንደቀጠለ ነው

ኢሳት ዜና: ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በቦረና ዞን አሬሮ ወረዳ ውስጥ በገብራና በቦረና ጎሳዎች መካከል በተነሳ ግጭት እስካሁን ድረስ ከ40 ያላነሱ ሰዎች ተገድለዋል። ግጭቱ ዛሬ ድረስ የቀጠለ ሲሆን አድማሱን እያሰፋ መምጣቱንም የአካባቢው ሰዎች ለኢሳት ተናግረዋል።

የአካባቢው ሰዎች እንደሚናገሩት በእስካሁኑ ግጭት የዛሬውን ሳይጨምር ከገብራ 21 ከቦረና ደግሞ 19 ሰዎች ተገድለዋል። በዛሬው እለትም የውጊያው አድማስ ሰፍቶ ሱልሉታ ወደሚባለው የያቬሎ አካባቢ ተስፋፍቷል።

ሁለቱ የኦሮሞ ጎሳዎች ከዚህ በፊትም ደም አፋሳሽ የሆነ ውጊያ አድርገው ነበር ። አንድ የአካባቢው ሰው ሁለቱ ለዘመናት ተፋቅረው የነበሩት ህዝቦች በአሁኑ ጊዜ ወደ ደም አፋሽ ጦርነት የገቡት በኢህአዴግ የዘር ፖለቲካ የተነሳ ነው ይላሉ የመከላከያ ሰራዊትም ሆነ የፌደራል ፖሊስ እስካሁን ድረስ በአካባቢው ተገኝተው ውጊያውን ለማስቆም አለመቻላቸው የአካባቢውን ሰዎች አስቆጥቷል። ከአራት ወራት በፊት የሶማሊ ተወላጆች በሆኑ ገሪዎችና የኦሮሞ ተወላጅ በሆኑት ቦረናዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በርካታ ሰዎች ማለቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከጋሞ የክልል ጥያቄ ጋር በተያያዘ በአርባ ምንጭና አካባቢዋ ውጥረት መኖሩን ዘጋቢያችን ገለጠ። በሲዳማ ዞን የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ሰሞኑን በአርባ ምንጭና አጎራባች ወረዳዎች ተመሳሳይ ችግሮች እየታዩ ነው። የፌደራል ፖሊስ አባላት በአካባቢው መስፈራቸውን እና እያንዳንዱዋን እንቅስቃሴ በመቃኘት ላይ መሆናቸውን ዘጋቢያችን ገልጧል። በኢትዮጵያ ውስጥ ከጎሳ ጋር በተያያዘ የሚነሱ አለመግባባቶች እየጨመሩ መምጣታቸው እየተነገረ ነው።

No comments:

Post a Comment