Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Tuesday, May 8, 2012

በመሀል ፒያሳ ራሱን ያቃጠለው ግለሰብ ሕይወቱ አለፈ

 Fetehe.com
ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ዕለት ፒያሳ- ዳግማዊ ሚኒልክ አደባባይ በሚገኘው የስራ ማስታወቂያ በሚለጠፍበት ጐዳና አካባቢ ሰውነቱ ላይ ቤንዚን አርከፍክፎ ራሱን በማቃጠሉ ወዲያውኑ ለሕክምና የካቲት 12 ሆስፒታል ገብቶ የነበረው ዳዊት ለንዳሞ በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ እሁድ ዕለት ሕይወቱ ማለፉ ታውቋል።

‹‹የፖሊስ አባል ነበረ›› የተባለው ዳዊት ለንዳሞ፣ ረቡዕ ዕለት ከድንገተኛ ክፍል ወደ ቃጠሎ ሕክምና መኝታ ኬዝ ቲም ተዘዋውሮ በሆስፒታሉ ሕክምና እየተከታተለ ነበር፡፡

ሆኖም ግለሰቡ የደረሰበት ቃጠሎ ጥልቀት ስለነበረው እሁድ እለት ከጠዋቱ 1፡ 30 ሰዓት ገደማ ሕይወቱ እንዳለፈ የሕክምና ክፍሉ ኃላፊ ሲስተር ታደለች በቀለ ለፍትሕ አስረድተዋል።

ወደ ሆስፒታሉ ከገባ ጊዜ ጀምሮ ከጓደኞቹ በስተቀር ዘመዱ ነኝ ያለ ማንም ሰው እንዳልነበረ  ስታወሱት ኃላፊዋ ለቀናቶች የሕክምና ወጪውን የቻለለት ሆስፒታሉ መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል። በቃጠሎው ምክንያት ህይወቱ ያለፈው የዳዊት ለንዳሞ አስከሬን ወደ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል መላኩን ሲስተር ታደለች ጨምረው ለፍትሕ ገልፀዋል።

ግለሰቡ በወቅቱ ራሱን ሲያቃጥል ‹‹የምበላው አጣሁ፣ ምን ልብላ?›› ሲል እንደነበረ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች በወቅቱ በቦታው ደርሶ ለነበረው የፍትሕ ዘጋቢ መግለፃቸውን በመጥቀስ ባለፈው ሳምንት እትማችን ዜናውን ማስነበባችን ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment