Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Sunday, January 20, 2013

የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን 70 በመቶው የአመራር ቦታ በህወሀት አባለት የተያዘ ነው ተባለ

ኢሳት ዜና:-ግንቦት7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለኢሳት በላከው ሁለተኛ ጥናቱ ላይ እንዳመለከተው በ11 መምሪያዎች የተዋቀረው በስሩ አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱስትሪዎቸን የሚያስተዳደርው የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን አስራ አንድ ትላልቅ መምሪያዎችና አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱሰትሪዎች በዋና ሀላፊነት፤ በዳይሬክተርነትና በምክትል ዳይረክትርነት የሚመሩ በ29 የከፍተኛ አመራር አባላት ነው።

ፍረደም ሐውስ የ 2013 ኢትዮጵያ ነጻነት የሌለባት ናት አለ

ኢሳት ዜና:-በአለም ላይ ያሉ አገሮችን ነጻነት ( ፍሪደም) በማወዳደር ሪፖርቱን የሚያወጣው አለማቀፋዊ እውቅና ያለው ፍሪደም ሀውስ የ2013 ሪፖርቱን ይፋ ሲያደርግ እንደገለጠው  ኢትዮጵያ ነጻነት የሌለባት አገር ናት ብሎአታል።
ፍሪደም ሐውስ የአለም አገራትን ነጻነት የሰፈነባቸው ከፊል ነጻነት ያለባቸውና ነጻነት የሌለባቸው አገራት በማለት በሶስት ከፍሎ የተመለከተ ሲሆን ፣ ነጻነት የሌለባቸው አገራት ተብለው የተፈረጁት መሰረታዊ የሆኑት የፖለቲካ መብቶች የሌሉባቸው፣ እንዲሁም የሰቪል ነጻነቶች የተነፈጉባቸው አገሮች ናቸው።

Friday, January 18, 2013

የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔ የተቃወሙት ዋና ጸሐፊው ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ አቀረቡ


    Ab Hizkiel
  • ‹‹ማንንም አሿሿሚ አይደለሁም፤ የሥልጣን ጥመኞችን አላገለግልም››
    ከትናንት በስቲያ ስብሰባውን ረግጠው እንደወጡ ዘ-ሐበሻ የዘገበችላቸው የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ከሐላፊነት የመልቀቂያ ደብዳቤ ለዐቃቤ መንበሩ ማቅረባቸውን ምንጮቻችን ገለጹ። የዘ-ሐበሻ ምንንጮች እንደሚሉት ዋና ጸሐፊው ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ የወሰኑት ከጥር 6 እስከ ጥር 8 ቀን 2005 ዓ.ም ሲካሄድ የነበረው የሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ጉባኤ እንደተጠናቀቀ ነው ያሉት የዜና ምንጮቻችን “ማንንም አሿሿሚ አይደለሁም፤ የሥልጣን ጥመኞችን አላገለግልም” በሚል የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ ማቅረባቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል። እንደ ዘ-ሐበሻ ምንጮች ከሆነ ለሕሊናቸው ያደሩ እውነተኛ አባቶች የአቡነ ሕዝቄልን ፈለግ ሊከተሉ እንደሚችሉ ያላቸውን ግምት ገልጸዋል።
    ውድ የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ይህ ዘገባ ከደረሰን በኋላ ሐራ ተዋሕዶ የተሰኘው ድረ ገጽ በአቡነ ሕዝቅኤል የሥልጣን መልቀቂያ ዙሪያ የሚከተለውን ሰፊ ዘገባ አቅርቧል። እንደወረደ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች

ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፌስ ቡክ እንዳተመው

ከመለስ ሞት በኋላ መረጋጋት የተሳነው ኢህአዴግ ከበርካታ ችግሮች ጋር ፊት ለፊት
ተፋጧል፡፡ ከችግሮቹ በከፊልም የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡
• በረከት ስምኦን የነበረው ተደማጭነት እየተሸረሸረ ሲሆን፣ የበረከት ባለቤት
የበረከትን መፅሃፍ ለመሸጥ (ገዥ ፍለጋ) በየተቋማቱ እየተንከራተቱ ነው፣
• አዲሱ ለገሰ የተደማጭነት መስመሩን ‹‹ኢህአዴግን ለማጠናከር›› በሚል ምክንያት
ይበልጥ እያደረጀ ነው፣

ኢትዮቴሌኮም የወያኔ ዘረኝነት ፖሊሰ መንጸባረቂያ መሆኑን የግንቦት ሰባት የአገር ዉስጥ ኢንተሊጀንስ አጋለጠ

የመረጃ ቴክኖሎጂ መሠረት የሆነዉ የቴሌኮሚኒኬሺን ዘርፍ አፍሪካ፤ ላቲን አሜሪካና ኢሲያ ዉስጥ የሚገኙ በእደገት ወደ ኋላ የቀሩ አገሮችን ለዘመናት ከተዘፈቁበት የኋለ ቀርነት ማጥ ዉስጥ ጎትቶ አዉጥቶ ወደ ፈጣን የእድገት ጎዳና ይወስዳቸዋል ተበሎ የታመነበትና በአንዳንድ አገሮች ዉስጥ ይህ ለእድገት አመቺነቱ በተግባር የተመሰከረለት ዘርፍ ነዉ። ይህንን ጥናት በPDF ዳወንሎድ ለማድረግ ከዚህ ላይ ይጭሃኑ

ይህ ዘርፍ ገበሬዉ፤ ሰራተኛዉ፤ ተማሪዉ፤ ወታደሩና ለሌላም በማንኛዉም የስራ ዘርፍ ለተሰማራ የህብረተሰብ ክፍል የእዉቀት ምንጭ በመሆን የስራ ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የሚረደና በህብረተሰብ መካከል ፈጣን የሆነ የመረጃ ልዉዉጥ አንዲኖር የሚያደርግ ዘርፍ ነዉ። በእድገት ወደ ኋላ ለቀረችዉ አገራችን ኢትዮጵያም ይሀ ዘርፍ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነ ዘርፍ ነዉ። ነገር ግን በአፍሪካ ዉስጥ አገራችን ኢትዮጵያ እጅግ በጣም ወደኋላ ከቀርችባቸዉና ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ ሆን ብሎ እድገታቸዉ እንዲገታ ካደረጋቸዉ ኋላ ቀር ዘርፎች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ይሄዉ የቴሌኮሚኒኬሺን ዘርፍ ነዉ።

Monday, January 14, 2013

ቻይና በኢትዮጵያዊያን ላይ የምታደርሰው ሰቆቃ

ቻይና ከወያኔ ጋር በሚያደርገው የጠበቀ ግኑኝነት በኢትዮጵያ ያሉ ቻይናዊያን በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚያደርሱት ሰቆቃ ለማመን የሚከብድ ነው። ቻይናዊያን በኢትዮጵያ በጣም ወጣት የሆኑ ኢትዮጵያዊያንን ጉልበት መበዝበዝ (ባርነት) ፣ አስገድዶ መድፈር ፣ ማስር ፣ የአካል ጉዳት ማድረስ (ቶርቸር) እና እስክ መግደል ድረስ ስልጣን አላቸው። በዚህ ቪዲዎ ውስጥ ይህን የቻይናዊያንን ኢ-ሰባዊ ተግባራት የሚያረጋግጡ በኢሳት ራዲዩዎ ከሁለት ሰዎች ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ ይገኝበታል።

Sunday, January 13, 2013

አዲስ አበባ በህገወጥ ልማዶችና የወሲብ ድርጊቶች እየተናጠች ነው

ኢሳት ዜና:-እንደ አዲስ አድማስ ዘገባ፤ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ፖሊሶችና ነጋዴዎች የአነቃቂ እፆች ተጠቃሚ ናቸው ተባለ በአዲስ አበባ ህገወጥ ተግባራት የሚከናወኑባቸው ቤቶች በከፍተኛ መጠን እየጨመሩ መምጣታቸውንና ከተማዋ አደጋ ላይ እንደሆነች ሰሞኑን ይፋ የተደረገ ጥናት አረጋገጠ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በትናንትናው ዕለት ይፋ የተደረገው ጥናት “መጤ ባህሎችና ልማዳዊ ድርጊቶች በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በተለይም በወጣቶችና ሴቶች ላይ እያስከተሉት ያለው አሉታዊ ተጽእኖ” በሚል ርዕስ የተካሄደ ሲሆን ከ3600 በላይ ህገወጥ የወሲብ ድርጊት የሚፈፀምባቸው ቤቶች እንዳሉ ጠቁሟል፡፡

Saturday, January 12, 2013

4 አመት የተፈረደባቸው የሜጋው ባለስልጣን በሳምንቱ ከእስር ተፈቱ

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በሜጋ ኪነጥበባት ኀ/የተ/ግ/ማ እና በቀድሞ ስራአስኪያጁ አቶ ዕቁባይ በርሄ ላይ በመሰረተው ክስ መሰረት አቶ ዕቁባይ አራት ዓመት ከአምስት ወራት ቅጣት ከተላለፈባቸው በኋላ ቅጣቱ በገደብ ተደርጎላቸው ተለቀዋል። የባለስልጣኑ መለቀቅ የፍትህ ሥርዓቱ አድሎአዊነት በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን አንድ የሕግ ባለሙያ ገለጸዋል፡፡

የባለስልጣኑ ዓቃቤ ሕግ ባቀረበው ክስ መሰረት የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አስረኛ ወንጀል ችሎት ጉዳዩን ሲመለከት ቆይቶ ተጠርጣሪዎቹ በሁሉም ክሶች ጥፋተኛ ናቸው ያላቸው ሲሆን ድርጅቱም ሆነ ግለሰቡ ጥፋተኛ የተባሉበት አንቀጾች የ15 ዓመት ጽኑ እስራትና የ50 ሺ ብር መቀጫን የሚያስከትሉ ቢሆንም ባልተለመደ መልኩ አቶ ዕቁባይ 12 እርከን ዝቅ ያለ ቅጣት ማለትም አራት ዓመት ከአምስት ወራት ፍ/ቤቱ ከማስተላለፉም በተጨማሪ ቅጣቱም በገደብ እንዲያዝላቸው ትላንትና የሰጠው ውሳኔ የፍትህ ስርዓቱን ጥያቄ ውስጥ የሚጥል አሳዛኝ ውሳኔ ነው ሲሉ ባለሙያው ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮቴልኮም በአንድ ዘር ቁጥጥር ስር እየገባ መሆኑ ታወቀ

ኢሳት ዜና:-የግንቦት ሰባት የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ  ባወጣው ጥናት እንዳመለከተው በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ኢትዮ ቴልኮምን ከነጻ ኩባንያነት አውጥቶ የአንድ ብሄር መሰባሰቢያና የስለላ ተቋም አድርጎታል።

በድርጅቱ ውስጥ ኤን አንድና ኤን ሁለት የሚባሉ ከፍተኛ የአስተዳደር እርከኖች መኖራቸውን ያስታወሰው ጥናቱ ፣ በኤን አንድና ሁለት የተመ ደቡትን በማኔጅመንት ደረጃ ያሉ ኢትዮጵያውያንና ፈረንሳዮችን የሚያጠቃልል ነው።

“የመለስን ሌጋሲ ማስቀጠል የማንችል ከሆነ ህዝቡ እሳት ሆኖ እንዳያቃጥለን እንሰጋለን” ሲሉ የኢህአዴግ አባላት ተናገሩ

ኢሳት ዜና:-በሚስጥር የደረሰን በአዲስ አበባ  የኢህአዴግ ድርጅት ጽህፈት ቤት ያዘጋጀው ሚስጢራዊ ሪፖርት እንደሚያመለክተው  የኢህአዴግ አባላት ከመለስ ሌጋሲ እና ከልማት ጋር የተያያዙ በርካታ ጥያቄዎችን ማንሳታቸው ተመልክቷል።

የኢህአዴግ አባላት  ካነሱዋቸው ሀሳቦች መካከል “  መስመሩን ያላወቁ አባላት ባለበት እንዴት ሌጋሲውን ማስቀጠል ይቻላል? አባሎች ራሳቸው ጀርባቸው መጠናት አለበት፣ ንፋስ ወደ ነፈሰበት የሚነፍሱ ቁጥራቸው እየበዛ ነው፣ የመለስ ሌጋሲ ሊኖር የሚችለው ስርአቱ እስካለ ድረስ ነው፣ የሚስጥር ጠባቂነት ችግር በአመራሩ ከላይ እስከታች አለ፣ አመራሩ ኪራይ ሰብሳቢነትን አምርሮ አይታገልም፣ህወሀት ሀይለማርያምን ማስቀጠል የለበትም ምክንያቱም ታግሎ የመጣ ሰው ነው መምራት ያለበት”   የሚሉት ይገኙበታል።