ኢሳት ዜና:-በአለም ላይ ያሉ አገሮችን ነጻነት ( ፍሪደም) በማወዳደር ሪፖርቱን የሚያወጣው አለማቀፋዊ እውቅና
ያለው ፍሪደም ሀውስ የ2013 ሪፖርቱን ይፋ ሲያደርግ እንደገለጠው ኢትዮጵያ ነጻነት የሌለባት አገር ናት
ብሎአታል።
ፍሪደም ሐውስ የአለም አገራትን ነጻነት የሰፈነባቸው ከፊል ነጻነት ያለባቸውና ነጻነት የሌለባቸው አገራት
በማለት በሶስት ከፍሎ የተመለከተ ሲሆን ፣ ነጻነት የሌለባቸው አገራት ተብለው የተፈረጁት መሰረታዊ የሆኑት የፖለቲካ
መብቶች የሌሉባቸው፣ እንዲሁም የሰቪል ነጻነቶች የተነፈጉባቸው አገሮች ናቸው።
ኢትዮጵያ ነጻነት የሌለባቸው አገሮች ተብላ የተፈረጀችው በአገሩ የፕሬስ ነጻነትን ጨምሮ ሌሎች የሰብአዊ እና ፖለቲካዊ መብቶች ባለመከበራቸው ነው።በአፍሪካ ውስጥ ነጻነት የሰፈነባቸው ተብለው የተጠቀሱት አገሮች ቤኒን፣ ቦትስዋና፣ ኬፕ ቨርዴ፣ ጋና፣ ሌሶቶ፣ ማሊ፣ ሞሪሺየስ፣ ናምቢያ፣ ሳኦቶሚና ፕሪንሲፒ እና ደቡብ አፍሪካ ናቸው።
ነጻነት ከሌለባቸው አገሮች መካከል ኢትዮጵያ፣ አንጎላ፣ ካሜሩን፣ ቻድ፣ ሁለቱ ኮንጎዎች፣ ጅቡቲ፣ ኢኳቶሪያን ጊኒ፣ ኤርትራ፣ ጋቦን፣ ጋምቢያ፣ ጊኒ ቢሳው፣ ማሊ፣ ሞሪታኒያ፣ ሩዋንዳ እና ሶማሊያ ይገኙበታል።ከአፍሪካ ቀንድ አገሮች በከፊል ነጻነት ያለባቸው ኬንያ እና ዩጋንዳ ናቸው።
የህወሀት/ ኢህአዴግ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ የሰብአዊ እና ፖለቲካ መብቶች መከበራቸውን በተደጋጋሚ
ቢገልጽም፣ የፍሪደም ሐውስ ሪፖርት እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ በ እኤአ 2010 ከነበራት ከፊል ነጻ ደረጃ ወደ
ነጻነት ወደ ሌለባቸው አገራት ደረጃ መውረዷን ነው። Watch the full discussion
here. Look at the full pdf report here.
here. Look at the full pdf report here.
No comments:
Post a Comment