ኢሳት ዜና:-የግንቦት ሰባት የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ባወጣው ጥናት እንዳመለከተው በስልጣን ላይ
ያለው መንግስት ኢትዮ ቴልኮምን ከነጻ ኩባንያነት አውጥቶ የአንድ ብሄር መሰባሰቢያና የስለላ ተቋም አድርጎታል።
በድርጅቱ ውስጥ ኤን አንድና ኤን ሁለት የሚባሉ ከፍተኛ የአስተዳደር እርከኖች መኖራቸውን ያስታወሰው ጥናቱ ፣
በኤን አንድና ሁለት የተመ ደቡትን በማኔጅመንት ደረጃ ያሉ ኢትዮጵያውያንና ፈረንሳዮችን የሚያጠቃልል
ነው።
በኤን አንድና በኤን ሁለት የማኔጅመንት ደረጃ የስራ ድርሻ የተሰጣቸዉ ኢትዮጵያዉያን ቁጥር 54 ሲሆኑ ከነዚህ መካከል 46.3 በመቶ ወይም 25ቱ የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ። በዚህ ከፍተኛ የማኔጅመንት እርከን ዉስጥ የኦሮሞ 18.5 በመቶ ወይም 10 ሰዎች ፤ የአማራና 29. 6 በመቶ ወይም 15 የተቀሩት ደግሞ 5.6 በመቶ 3 ብቻ ናቸዉ።
ከሁለቱ የማኔጅመንት እርከኖች ዉስጥ ኤን አንድ የሚባለዉ ከፍተኛዉ ሲሆን በዚህ እርክን ዉስጥ ስምንት የትግራይ
ተወላጆች ሲኖሩ የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች እያንዳንዳቸዉ ሁለት ቦታ ይዘዋል። በዚህ ከፍተኛ የአመራር እርከን
ዉስጥ ከተቀሩት ስድስት ክልሎች የተመደበ አንድም ሰዉ የለም እንደ ጥናቱ ውጤት።
ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታይ ከእያንዳንዱ 3.3 ሚሊዮን የኦሮሞ ተወላጅ ዉስጥ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ
የተሰጠዉ አንድ የኦሮሞ ተወላጅ ብቻ ሲሆን፣ ትግራይን ስንመለከት ግን ከእያንዳንዱ 194 ሺ የትግራይ ተወላጅ
ዉስጥ ቢያንስ አንድ ሰዉ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ ተቀምጧል።
ይህ የስራ አመዳደብ የትምህርት ችሎታንና ልምድን ተከትሎ የተሰራ ነዉ ቢባል እንኳን የላቀ የትምህርት ደረጃና
የስራ ልምድ ያላቸዉ የኦሮሞ ተወላጆች ቁጥር ተመሳሳይ የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ካላቸዉ የትግራይ ተወላጆች
ቁጥር በአስር እጥፍ መብለጡ ምንም ጥርጥር የለዉም የሚለው ጥናት ፣ 66 ነጥብ 2 በመቶ የሚሆነዉን የኢትዮጵያ
ህዝብ ከሚያቅፉት ከኦሮሚያና ከአማራ ክልል N1 በሚባለዉ ከፍተኛ የአመራር አርከን ዉስጥ በአመራር ቦታ የተቀመጡ
ዜጎች ብዛት አራት ማለትም ሁለት ከኦሮሚያ ሁለት ከአማራ ብቻ ነው። ከጠቅላላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ዉስጥ 5.4
በመቶዉ ብቻ ከሚኖርበት ከትግራይ ክልል በአንጻሩ ስምንት ሰዎች ኤን አንድ በሚባለዉ ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ
ተቀምጠዋል።
በ2012 ከኦሮሚያ፤ ከአማራና ከትግራይ ክልል ዉጭ በተቀሩት ስድስት ክልሎች ዉስጥ የሚኖረዉ ህዝብ 25 ሚሊዮን
627 ሺ 349 የሚገመት ሲሆን፣ ከዚህ ህዝብ ዉስጥ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ የመቀመጥ እድል
ያገኙት 0.000012 በመቶ ብቻ ወይም ከእያንዳንዱ 8.5 ሚሊዮን ህዝብ አንዱ ብቻ ነዉ።
የግንቦት ሰባት የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከዚህ ቀደም መንግስት “የኢትዮጵያ መከላከያ” ጦር እያለ
የሚጠራዉን ሠራዊት ምን ያክል የኔ በሚላቸዉ የህወሀት ሰዎች ብቻ እንደሚቀጣጠር የሚያሳይ መግለጫ በመረጃ አስደግፎ
ለህዝብ ማቅረቡ የሚታወስ ነዉ።
የኢንፎርሜሺን ደህንነት ኤጀንሲ ሹም ብ/ጄኔራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ “የኢትዮጽያ ቴሌኮምኒኬሽን”
የኀብረተሰቡን ሰላም የሚያጠፉ ዌብሳይቶችን የመቆጣጠርና የኢንተርኔት ድረገጾችና ብሎጎችን የማገድ አቅም ሊኖረው
ይገባል፡፡መርሁም ይህ ነዉ በማለት በአዳባባይ መናገራቸው ይታወሳል።
ግንቦት7 ጥናቱን ለአንድ አመት ያክል ማካሄዱን ገልጿል። ኢህአዴግ በቅርቡ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት የብሄር ብሄረሰቦችን እኩልነት የተረጋጋጠበትን ቀነው በሚል በባህርዳር ማክበሩ ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment