Welcome!
"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu
Wednesday, July 11, 2012
የኦሮሞ ነጸናት ግንባር በቶሮንቶ የተሳካ ስብሰባ አደረገ
ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በብርጋዲየር ጄ/ል ከማል ገልቹ የሚመራው የአሮሞ ነጸናት ግንባር ባለፈው ቅዳሜ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ጁላይ 6 ቀን 2012 በቶሮንቶ ካናዳ የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባ አድረገ።
በዚህ
በቶሮንቶ አካባቢ የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆችና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን በተገኙበት የግማሽ ቀን ስብሰባ ላይ፤ የድርጅቱ
የበላይ አመራር አካላት፡ ማለትም ብርጋዲየር ጄነራል ሀይሉ ጎንፋ ከአስመራ በስልክ፡ ዶ/ር ኑሮ ደደፎና የድርጅቱ
ቃል አቀባይ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ሀይል ባለሟል አቶ ተማም ባቲ፤ በአካል ተገኝተው፤ ንግግር በማድረግ
ከተሰብሳቢው ጋር ተወያይተዋል።
የህዝበ-ሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል ከሆቴላቸው በፖሊስ ታፍነው ተወሰዱ
ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በኮምቦልቻ ከተማ በዛሬዉ እለት በተካሄደዉ ደማቅ የአንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም ላይ ተካፍለዉ የነበሩት የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ሼህ መከተ ሞሄ በፖሊስ ታፍነዉ መታሰራቸዉን በስፍራው የሚገኘው የኢሳት ወኪል ዘግቧል።
ሼህ መኸተ ሞሄ የታሰሩት ፕሮግራሙን ጨርሰዉ ወደ ማረፊያ ሆቴላቸዉ ከገቡ ቡሁዋላ በበርካታ ፖሊሶች ታፍነው ነው።
ከሸህ መከተ በተጨማሪ በኮምቦልቻ ፕሮግራም ላይ ከተካፈሉት መካከል፤ ታዎቂዉ “ዳኢ” እና የሙስሊሙ ማህበረሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የሆነዉ ኡስታዝ ያሲን ኑሩም በፖሊሶች እየተፈለገ መሆኑን ወኪላችን ያጠናቀረው ዘገባ ያመለክታል።
በአሁኑ ጊዜ የአካባቢው ፖሊስ ኡስታዝ ያሲን ኑሩን ለማሰር ከተማዋን እያሰሰ መሆኑን ምንጮች ገልፀዋል!!
Source: Ethsat news :የህዝበ-ሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል ከሆቴላቸው በፖሊስ ታፍነው ተወሰዱ

Monday, July 9, 2012
የአቶ መለስ ዜናዊ የጤና ሁኔታ አሁንም ሚስጢር እንደሆነ ነው
ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የፓርላማ አባላት ግራ ተጋብተዋል፣ የተለያዩ ዝግጅቶች ተሰርዘዋል ፣ አንዳንድ መረጃዎች አቶ መለስ የወራት እድሜ እንዳላቸው ይጠቁማሉ ዝርዝሩ ኢሳት
የፓርላማው መዝጊያ በአንድ ሳምንት እንደሚራዘም፣ ምክንያቱ ደግሞ የአቶ መለስ ዜናዊ የጤና ችግር እንደሆነ ከዘገበ
በሁዋላ ፣ የአቶ መለስ የጤና ሁኔታ የመላው ኢትዮጵያውያን የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል።
በኢህአዴግ ዙሪያ
የተሰባሰቡ አባላት ሳይቀሩ ግራ ተጋብተዋል። አቶ መለስ ዜናዊ በተገኙበት በፈጠራና ምርምር የላቀ ውጤት ላስገኙ ስድስት ኢትዮጵያዊያን በጠ/ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ሰሞኑን ሊሰጥ የታሰበው ሸልማት ለሁለተኛ ጊዜ ተላልፏል፡፡ በሳይንስና
ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሰኔ 21 ቀን 2004 ዓ.ም ሊሰጥ ታሰቦ የነበረው ሸልማት በሥራ መደራረብ ምክንያት ለሰኔ
28 ቀን 2004 ዓ.ም መተላለፉን በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ጭምር ይፋ ከተደረገ በኃላ እንደገና ምክንያት
ባልተገለጠበት ሁኔታ ዝግጅቱ እንዲቀር ተደርጓል፡፡
በደርግ ዘመነ መንግስት የነበረውን ጥበባዊ አሻራ ለማስቃኘት ታሰቦ የተከፈተው የሥዕል ኤግዚቢሸን በኢቲቪ እንዳይተላለፍ ታገደ
ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የኤግዚቢሸኑ ዜና በኢቲቪ ከተዘገበ በኃላ እንዳይተላለፍ የታገደው ያለፈውን ሥርዓት የሚያንቆለጻጽስ ነው በሚል ነው፡፡
በአዲስ
አበባ ዩኒቨርሲቲ በእስክንድር በጎሲያን ሥነ ጥበባት ኮሌጅ ሥር የሚገኘው ትምህርት ቤት ከ1967 እስከ 1983
ዓ.ም. ድረስ ተማሪዎቹ ከሠሯቸው ልዩ ልዩ ሥዕሎች መካከል የተመረጣቸውን ሥዕሎች በሰኔ ወር መጀመሪያ ጀምሮ ለእይታ
አብቅቷል፡፡
ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሽብርተኝነት ከተከሰሱት ሰዎች በአራቱ ላይ የቅጣት ውሳኔ አሳለፈ
ኢሳት ዜና:- ሰኔ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በእነ አንዱዓለም አራጌ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት
ክስ ተመስርቶባቸው፣ የከፍተኛው ፍርድ ቤት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ አሰናብቷቸው የነበሩ አራት ተከሳሾች ላይ
የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከ10 እስከ እድሜ ልክ የሚደርስ የቅጣት ውሳኔ ዛሬ አሳለፈ።
የመንግስት
አቃቤ ሕግ ብርሃኑ ወንድምአገኝ በነኚሁ አራት ግለሰቦች ላይ፣ ማለትም በ21ኛው ተከሳሽ ኮሎኔል አለበል አማረ፣
በ12ኛ ተከሳሽ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ፤ በ19ኛው ተከሳሽ አቶ ኤልያስ ሞላ እና በ20ኛው ተከሳሽ አቶ ደሳለኝ አራጌ
ላይ ያቀረበው ክስ እንደሚያስረዳው ተከሳሾቹ የተወነጀሉት ከግንቦት 7 ፓርቲ ጋር ግንኙነት በመፍጠር የሽብር
ተግባርን ለመፈጸም በማቀዳቸው እንደሆነ ይጠቅሳል።
‹‹ይቅርታ›› የኢህአዴግ ቃጭል? ወይስ…
1998
አዲስ አበባ በለውጥ ፍላጐት ከአፍ እስከ ገደቧ ታጥናለች። እዚህም እዚያም የፖለቲካ ወግ ጠሰቃል። በቡድን ሆነው፣ በስሜት ተውጠው በፖለቲካ ጉዳይ የሚከራከሩ በርክትዋል፡፡ ለዓመታት የፖለቲካ ጉዳይ ‹‹ፆም›› የሆነባቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሳይቀሩ ጎራ ለይተው በሚከራከሩ ራተኞቻቸው ተፈስገዋል፡፡ ‹‹ቅንጅቱ መንግሥት ለመመስረት የሚያስችል ድምፅ አግኝቷል›› ይላል አንዱ። ‹‹ቢሆንም ኢህአዴግ ይገግማል!›› ሲል ይመልሳል፤ ኢህአዴግ በምርጫ ስልጣን አይለቅም የሚል አቋም ያለው ተከራካሪ፡፡

…የጋዜጦች እትሞች ከምርጫው በፊት ከነበረው ቅጂ ከሶስት እስከ አምስት እጥፍ ድረስ ጨምረዋል። ማንበብ የሚችለውም፣ ማንበብ የማይቻለውም ቋሚ የጋዜጣ ሸማች ሆኖአል-እድሜ ለምርጫው። በኢትዮጵያ ‹‹መንግሥት…›› ሲባል የተቃወመውን በሙሉ የሚገድል እንደሆነ ከልምድ የተገነዘቡ ወላጆች ለልጆቻቸው በመስጋታቸው ጭንቀታቸው ጨምሯል፡ ፡ እነዚህ ኩነቶች የድህረ ምርጫ 1998 ዓ.ም. ዋነኛ መገለጫዎች ነበሩ፡፡
ያስፈራል፤ ግን ኢትዮጵያ አትፈርስም!
By ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም
ይቺ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ስንት የመከራ ወንዞችን ተሻግራለች! ገና ስንት ትሻገራለች! ስንት የግፍ ተራራዎችን አቋርጣለች! ገና ስንት ታቋርጣለች! ስንት የበደል ሰይፎችንና ጦሮችን አምክናለች! ገና ስንት ታመክናለች! ስንት የውጭ ኃይሎችን አሳፍራለች! ገና ስንቱን ታሳፍራለች!
ስንት አምባገ- ነኖችን እያለቀሰች ቀብራለች! ገና ስንቱን
ትቀብራለች! ጭቆና ከኢትዮጵያውያን ደም ሙልጭ ብሎ ወጥቶ በነፃነት፣ በእኩልነት፣ በዳኝነት በጠራ ደም እስቲተካ
ድረስ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ዘርግታ ትጸልያለች! እግዚአብሔርም ቃል ኪዳን አለበት ይሰማታል!
የኃያላን ኃያል ኢትዮጵያ እንድትፈርስ አይፈቅድም!
Subscribe to:
Posts (Atom)