ኢሳት ዜና:- ሰኔ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንደጠቀሰው
የበሀይሌ ሊ/መንበር የሆኑት አቶ አሊ ማያቤ፣ የአካባቢው የጎሳ ተጠሪ የሆኑት አቶ ዳቶና ሙሀመድ ፣ አቶ አሊ ናስሪ
ሙሀመድ፣ አቶ ኦማር ሀቴ፣ አቶ ዳውድ አሊ፣ አቶ ማያቢሄ ሞሀመድ፣ አቶ ካድር አስከሪ እና አቶ ሙሀመድ ኢጋሀሌ
በፌደራል ፖሊስ ከተወሰዱ በሁዋላ እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም።
ድርጅቱ እንዳለው ካለፈው መጋቢት ወር
ጀምሮ በክልሉ ነዋሪዎች ላይ የሚፈጸመው ግፍ በከፍተኛ ደረጃ ጨመሯል። በአሁኑ ጊዜ የአዳቢቶሊ፣ የገዋኒ፣ አሳይታ
እና የበሀይሌ አካባቢዎች በመከላከያ ሰራዊት ተከበዋል። እንደ ድርጅቱ መግለጫ በቅርቡ የተነሳው ግጭት መንስኤ አንድ
የመካላከያ ሰራዊት መኮንን እና የሴት ጉዷኛው መገደላቸው ነው።






