Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Wednesday, May 9, 2012

ህዝቡ በዋጋ ንረቱ መማረሩን ሲቀጥል ስታትስቲክስ ቢሮ ግሽበቱ 2 በመቶ መቀነሱን ገለጠ

ኢሳት ዜና:- ግንቦት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም  
በያዝነው ወር ሀሉም ነገር መጨመሩን ከተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ዘጋቢዎቻችን ገልጠዋል። በአማራ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች ጤፍ እስከ 1300 ብር በመሸጥ ላይ ነው። በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋም የጤፍ ዋጋ መጨመር እንጅ መቀነስ አላሳየም። የበቆሎ እና ሌሎችም ለምግብ ፍጆታነት የሚውሉ ሸቀጦች ተነጻጻሪ ጭማሪ አሳይተዋል። የዘይት ዋጋ ባለበት ቢቆይም፣ ስኳር እና ሻይ ቅጠል ጭማሪ አሳይተዋል። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ 4 ብር የነበረው አንድ ባኮ ሻሂ ቅጠል ወደ 8 ብር ከፍ ብሎአል።

 አሁን የሚታየው የእህል ዋጋዎች ጭማሪ እንደሚቀጥል የተለያዩ የከተማ ነዋሪዎች ይናገራሉ። ገበሬው በማዳበሪያ እዳ መያዙ፣ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በግዳጅ እንዲያዋጣ መታዘዙ እና በቂ እህል አለኖሩ የእህል ምርት ዋጋን ከሚጨምሩት ምክንያቶች ተርታ ተሰልፈዋል። መንግስት የእህል ዋጋ አሁን ካለበት መጠን እንዳያልፍ 8 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለማረጋጊያ መግዛቱንና ከዚህም ውስጥ 3 ሚሊየን ኩንታል ወደ አገር ውስጥ መግባቱን ተናግሯል።

መጪው የክረምት ጊዜ እንደመሆኑ በመላ አገሪቱ ከፍተኛ የምግብ እጥረት ሊከሰት ይችላል የሚል ስጋት ባየለበት በአሁኑ ጊዜ ማእከላዊ ስታትስቲክስ በሚያዚያ ወር የዋጋ ግሽበቱ መቀነሱን የሚያሳይ ሪፖርት ይፋ አድርጓል። መስሪያ ቤቱ እንዳለው ያለፈው  ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 29 ነጥብ 8 ነው።

በሚያዚያ ወር 2004 ዓ.ም የተመዘገበው የ12 ወራት ተንከባላይ አማካይ አገራዊ የዋጋ ግሽበት ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ36 ነጥብ 3 በመቶ ጭምሪ እንዳሳየ ከአገራዊ የ12 ወራት ተንከባላይ አማካይ የምግብ ዋጋ ግሽበት ጋር ሲነጻጻር ደግሞ በ45 ነጥብ 5 በመቶ መጨመሩን አመልክቷል። በተመሳሳይ ምግብ ነክ ባልሆኑ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ግሽበት በ23 ነጥብ 4 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ጠቅሷል።

በበያዝነው አመት በሚያዚያ ወር የምግብ ዋጋ ግሽበት ከአምናው ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጻር በ36 ነጥብ 7 በመቶ አድጓል። በአገሪቱ ውስጥ ለታየው የዋጋ ግሽበት መጨመር ዋነኛ ምክንያት የሆነው የእህል ዋጋ በ45 ነጥብ 8 በመቶ መጨመሩ ነው።  ያሳለፍነው ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ቀደም ብሎ ከነበረው የመጋቢት ወር ጋር ሲነጻጸር  በ2 ነጥብ 1 ዝቅ ማለቱን ኤጀንሲው ገልጧል። በኢትዮጵያ የሚታየው የዋጋ ንረት የህዝቡን ብሶት እየጨመረው እንደሚገኝ መገናኛ ብዙሀን እየዘገቡት ይገኛሉ።

ኢትዮ ቴሌኮም ድብቅ መሳሪያ ተክለው ከውጪ አገር የሚደውሉ የስልክ ጥሪዎች እየተፈፀመ ነው አለ

 ኢሳት ዜና:-ግንቦት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢትዮጵያ ውስጥ ማንነታቸው ያልታወቁ  ግለሰቦች ወይም ኩባንያዎች  ድብቅ መሳሪያ ተክለው ከውጪ አገር የሚደውሉ የስልክ ጥሪዎችን በራሳቸው መሣርያዎች በመቀበልና ለደንበኞች በማስተላለፍ በሕግ የተከለከለ የስልክ አገልግሎት እየሰጡ ነው ሲል ኢትዮ ቴሌኮም  አጋለጠ።  በ1995 ዓመተ ምህረት ሟቹ ኢያሱ በርሄ እና ሌሎች ግለሰቦች በህገ-ወጥ መንገድ ባስገቧቸው የቪሳት መሳሪያዎች ተመሳሳይ አገልግሎት ሢሰጡ ተይዘው ክስ እንደተመሰረተባቸው ይታወሳል።

 ይሁንና   ኮርፖሬሽኑ  በግለሰቦቹ ምክንያት ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ እንዳጣ ቢረጋገጥም፤በክሱ  ምርመራ ሂደት  ከቀድሞው  የህወሀት ታጋይ ከ አርቲስት ኢያሱ በርሄ ጋር በመሆን  የተጠቀሰውን ተግባር እየፈፀሙ ከነበሩት ግለሰቦች መካከል አንዷ፦ ቀዳማይት እመቤት አዜብ መስፍን ሆነው በመገኘታቸው፤ ተከሳሾቹ በነፃ እንዲሰናበቱ  መደረጉ በወቅቱ ይታተሙ የነበሩ ጋዜጦች በስፋት ዘግበዋል::

 ለተከሳሾቹ በነፃ መሰናበት  በፍርድ ቤት በኩል የተጠቀሰው ምክንያትም፤የቀድሞው የ ኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን የደረሰበትን ኪሳራ በሚገባ ለፍርድ ቤቱ ማቅረብ አልቻለም የሚል እንደሆነም አይዘነጋም። ይህ  ከሆነ ከዘጠኝ ዓመት በሁዋላ ነው ኢትዮ-ቴሌኮም  ኢትዮጵያ ውስጥ  በድብቅ መሳሪያ የተከሉ ግለሰቦች ወይም ኩባንያዎች  ህገ ወጥ የቴሌ አገልግሎት እየሰጡ እንደሆነ ከሰሞኑ ይፋ ያደረገው።

ኢትዮ ቴሌኮም፦ ሱሉልታ በሚገኘው ሳተላይት ተቀብሎ ለደንበኞች ማስተላለፍ የነበረበትን የውጪ አገር ጥሪዎች፣ እነዚህ ማንነታቸው ያልታወቁ  ግለሰቦች ወይም ኩባንያዎች በውል ባልታወቀ ሥፍራዎች በተከሏቸው መሣርያዎች አማካይነት እየተቀበሉ በማስተናገድ ላይ እንደሆኑ ያጋለጡት፤ የኢትዮ ቴሌኮም አንድ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ ናቸው። ኢትዮ ቴሌኮም ይህ ሕገወጥ የስልክ አገልግሎት እየተካሄደ እንደሆነ ሊደርስበት የቻለውም፤ ከደንበኞች በደረሱት ጥቆማዎች እንደሆነ ኃላፊው አስረድተዋል::

የተለያዩ ደንበኞች ከአሜሪካና ከመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ወደ ሞባይላቸው በሚደወልላቸው ወቅት በሞባይላቸው ላይ የሚወጣው ቁጥር የውጪ ሳይሆን የአገር ውስጥ ሞባይል ቁጥር እንደሆነ  ሀላፊው ለኢትዮ ቴሌኮም አስታውቀዋል:: የኢትዮ ቴሌኮም የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አብዱራሂም አህመድ  በበኩላቸው፤ የተጠቀሰውን ጉዳይ አስመልክቶ መስሪያ ቤታቸው ጥቆማ እንደደረሰው አረጋግጠዋል::

ኢትዮ ቴሌኮም ጉዳዩን በጥንቃቄ በመመርመር ላይ እንደሆነ የተናገሩት አቶ አብዱራሂም፣ የተባሉት መሣርያዎች የተተከሉት ኢትዮጵያ ውስጥ ወይም በጐረቤት አገሮች ሊሆን  እንደሚችልም ጥርጣሬያቸውን ተናግረዋል:: ከተለያዩ አገሮች ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ ጥሪዎችን በሳተላይት ተቀብሎ ለደንበኞች የሚያስተላልፈው ኢትዮ ቴሌኮም ሲሆን፣ ለዚህም አገልግሎት የውጭ የቴሌኮም ኩባንያዎች በየዓመቱ መጨረሻ ይከፍሉታል::

በአንፃራዊ ሁኔታ ኢትዮጵያ ለዚህ አገልግሎት የምታስከፍለው ክፍያ ከፍ ያለ በመሆኑ፣ አቅሙ እና በአመዛኙ  ከባለስልጣናት ጋር ንክኪ  ግለሰቦች የራሳቸውን መሣርያዎች በመትከል ተመሳሳይ አገልግሎት በአነስተኛ ክፍያ በመስጠት  የቴሌን ሥራ እንደሚሰሩ ይነገራል። በ አሁኑ ጊዜ የቴሌ ማኒጅመንት እና አመራር ሙሉ በሙሉ በህወሀት ጀነራሎች ቁጥጥር ውስጥ መውደቁን ያወሱ  የቀድሞ የኮርፖሬሽኑ ሠራተኛ፤ ድብቅ መሳሪያ በመትከል የቴሌ አገልግሎት  በመስጠቱ ህገ ወጥ አሠራር ውስጥ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሙሰኞቹ  ህወሀቶች ተሳታፊ እንደሚሆኑ አያጠራጥርም ብለዋል።

“ከታች እስከ ላይ፤ ከተራ የስልክ ኦፕሬተር እስከ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ቴሌ በህወሀት ሰዎች ስር ወድቋል።  በድርጅቱ ውስጥ ባሉ የሀላፊነት መዋቅሮች በሙሉ የተቀመጡት ህወሀቶች ናቸው። ጥሪዎችን የሚጠልፉት፣የሚቆርጡት፣የሚቀጥሉት፣የሚፈቅዱት፣የሚከለክሉት…እነሱ ናቸው።እነሱ ሳያውቁት የሚደረግ አንድም ግንኙነት የለም” ያሉት እኚሁ ግለሰብ፤ “ቀደም ሲል ይህን ነገር ሲፈፅሙ የነበሩት እነ  ወይዘሮ አዜብ እንደነበሩ ልንረሳው አይገባም” ብለዋል።

ዋና ኦዲተር የመንግሥት መሥርያ ቤቶችን የሒሳብ ግድፈቶች አጋለጠ

  By Haile Mulu, Reporter
•    በደንቡ መሠረት ያልተወራረደ 1.2 ቢሊዮን ብር ተገኝቷል
•    ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ ያልተቻለ 2.03 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል
የመንግሥት መሥርያ ቤቶች በ2004 በጀት ዓመት የፈጸሙትን በርካታ የሒሳብ አያያዝ ግድፈቶችንና የውስጥ ቁጥጥር ድክመቶችን ይፋ አደረገ፡፡ ከደንብና መመርያ ውጭ የሆኑ አፈጻጸሞችም ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ አስገንዝቧል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ ባለፈው ሳምንት ለተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለጹት፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፋይናንስ አስተዳደር ደንብ በሚደነግገው መሠረት የተሰብሳቢ ሒሳብ በወቅቱ መወራረዱ ሲጣራ፣ በ59 መሥርያ ቤቶች 1.27 ቢሊዮን ብር በደንቡ መሠረት በወቅቱ ሳይወራረድ ተገኝቷል፡፡ ከዚህ ውስጥ የትምህርት ሚኒስቴር 723.77 ሚሊዮን ብር፣ የመከላከያ ሚኒስቴር 133.78 ሚሊዮን ብር፣ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና 115.02 ሚሊዮን ብር ባለማወራረድ ከፍተኛ ድርሻውን ይዘዋል፡፡

የገቢ ሰብሳቢ መሥርያ ቤቶችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በገቢ ግብር፣ በቀረጥና በታክስ እንዲሁም በሌሎች ገቢ መሰብሰብን በሚፈቅዱ አዋጆች፣ ደንቦችና መመርያዎች መሠረት የመንግሥትን ገቢ የሰበሰቡ መሆኑን ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፣ በ16 መሥርያ ቤቶች በድምሩ 952.94 ሚሊዮን ብር በተለያዩ ምክንያቶች ሳይሰበሰብ ተገኝቷል፡፡ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት  638.14 ሚሊዮን ብር፣ ምሥራቅ አዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት 132.56 ሚሊዮን ብር፣ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት 10.58 ሚሊዮን ብርና የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር 120.63 ሚሊዮን ብር ያልሰበሰቡ ዋና ዋና መሥርያ ቤቶች ናቸው፡፡

የመንግሥት ገቢ በወቅቱና በአግባቡ መሰብሰባቸውን ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፣ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና መሥርያ ቤትና በሥሩ ባሉ ሰባት ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ከውዝፍ ግብር፣ ከወለድና ከቅጣት መሰብሰብ የሚገባው  272.15 ሚሊዮን ብር ሳይሰበሰብ መቅረቱን በሪፖርታቸው የገለጹት ዋና ኦዲተሩ፣ ገቢን በወቅቱ መሰብሰብ መንግሥት ለሚያከናውነው የልማትና ማኅበራዊ ሥራዎች ወሳኝ በመሆኑ ለጉዳዩ ትኩረት ተሰጥቶት የመንግሥት ገንዘብ በወቅቱ እንዲሰበሰብ አሳስበዋል፡፡

ይኼው የዋናው ኦዲተር ሪፖርት እንዳመለከተው፣ የዕቃና አገልግሎት ግዢ በደንብና መመርያ መሠረት የተፈጸመ መሆኑን ለማጣራት ኦዲት ሲደረግ፣ በ33 መሥርያ ቤቶች 313.26 ሚሊዮን ብር የመንግሥትን የግዢ አዋጅ፣ ደንብና መመርያ ያልተከተለ ግዢ ተፈጽሞ ተገኝቷል፡፡ ከደንብና መመርያዎች ውጪ ግዢ ከፈጸሙ መሥርያ ቤቶች መካከል መቀሌ ዩኒቨርሲቲ 224.22 ሚሊዮን ብር፣ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ 41.38 ሚሊዮን ብር፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ 7.56 ሚሊዮን ብርና የመቀሌ ጤና ሳይንስና አይደር ሪፈራል ሆስፒታል 3.06 ሚሊዮን ብር ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ከላይ የተጠቀሱት መሥርያ ቤቶች ካልተከተሏቸው የግዢ ደንብና መመርያዎች ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያ በማውጣት ሊፈጸሙ የሚገባቸውን ግዢዎች ያለጨረታ ማስታወቂያ በመግዛት፣ በዋጋ መወዳደሪያ (ፕሮፎርማ) አማካይነት መፈጸም ያለበትን ግዢ ውድድር ሳይደረግ በመፈጸምና ተገቢ የውል ስምምነት ሳይደረግና በአቅራቢነት ካልተመዘገቡ ድርጅቶች ግዢ ማከናወን የሚሉት ይገኙበታል፡፡

 የግዢ መመርያን ሳይከተሉ ግዢ መፈጸም ለምዝበራና ለጥፋት የሚዳርግ መሆኑን በሪፖርታቸው የጠቆሙት አቶ ገመቹ፣ የመንግሥት ግዢ ደንብና መመርያን አክብረው በማይሠሩ መሥርያ ቤቶች ላይ የተጠናከረ ዕርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የመንግሥት ገንዘብ ወጪ ሆኖ የተገዛው ንብረት ለመሥርያ ቤቱ ገቢ ለመሆኑ የንብረት ገቢ ደረሰኝ የተቆረጠለት መሆኑን ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፣ በዘጠኝ መሥርያ ቤቶች በ83.99 ሚሊዮን ብር የተገዙ ዕቃዎች የንብረት ገቢ ደረሰኝ ሳይቆረጥላቸው ሒሳቡ በወጪ ተመዝግቦ ተገኝቷል፡፡ ከዚህ ውስጥ ትምህርት ሚኒስቴር 75.26 ሚሊዮን ብር፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ 4.02 ሚሊዮን ብርና የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ 3.9 ሚሊዮን ብር የተገዛው ዕቃና ንብረት ገቢ ለመደረጉ ማስረጃ ሳይቀርብ ሒሳቡን በወጪ ከመዘገቡት መሥርያ ቤቶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

በበጀት ዓመቱ መሥርያ ቤቶች የፈጸሙትን ክፍያ ትክክለኛነት ለማጣራት ኦዲት ሲደረግ፣ በስምንት መሥርያ ቤቶች 2.03 ቢሊዮን ብር በተለያዩ ምክንያቶች የወጪውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ያልተቻለ መሆኑ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

የወጪውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ካልተቻለው ሒሳብ ውስጥ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ለሠራዊት ደመወዝ ወጪ ያደረገው 1.87 ቢሊዮን ብር፣ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት 54.25 ሚሊዮን ብር፣ እንዲሁም የውስጥ ደኅንነት ጥበቃ ዋና መምርያ 33.34 ሚሊዮን ብርና የኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳይ ዋና መምርያ 49.99 ሚሊዮን ብር ወጪ ያደረጉ ዋና ዋና መሥርያ ቤቶች ናቸው፡፡

በሪፖርቱ ላይ እንደተጠቀሰው ሦስቱ የደኅንነት መሥርያ ቤቶች ለደመወዝ፣ ለነዳጅ፣ ለስልክ፣ ወዘተ ወጪ ያደረጉትን ሒሳብ ለማረጋገጥ ዝርዝር መረጃዎች እንዲያቀርቡ ተጠይቀው ባለመቅረቡ የወጪውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ለፌዴራል ዋና ኦዲተር በላከው መልስ ከመረጃው ሚስጥራዊነትና ከደኅንነት አንፃር ችግር ያለበት በመሆኑ፣ ለወደፊቱም ቢሆን እንደዚህ ዓይነት ዝርዝር ከሚስጥርና ከደኅንነት ጋር የተያያዙ ሰነዶችን አሳልፎ መስጠት አስቸጋሪ መሆኑን ገልጿል፡፡

በንብረት አያያዝና አስተዳደር ረገድ የታዩ የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት ድክመቶችም በሪፖርቱ የተጠቀሱ ሲሆን፣ በበርካታ መሥርያ ቤቶች መጋዘን ውስጥ አገልግሎት የሚሰጡ ዕቃዎች ከሚወገዱ ዕቃዎች ጋር ተቀላቅለው ተቀምጠው እንደሚገኙ፣ የተለያዩ ኬሚካሎች፣ ጎማዎችና ሌሎች ዕቃዎች በወለል ላይ ለብልሽት  በተጋለጠ ሁኔታ መቀመጣቸው ተገልጿል፡፡ በዚህ ረገድ ድክመት የታየበት ዋነኛው መሥርያ ቤት ግብርና ሚኒስቴር ነው፡፡

ለረጅም ዓመታት ግምጃ ቤት ገቢ የተደረጉ፣ በተለይም በ1996 ዓ.ም. የተለያዩ መሥርያ ቤቶች ሲዋሀዱ ተመላሽ የተደረጉ ንብረቶች በዓይነትና አገልግሎት የሚሰጡና የማይሰጡ ሳይለዩ ለቁጥጥር በሚያስቸግር ሁኔታ ምንም ዓይነት ምዝገባ ሳይከናወን በተለያዩ ዘጠኝ የግብርና ሚኒስቴር መጋዘኖች ለረጅም ጊዜ ተከማችተው መገኘታቸው፣ መሥርያ ቤቱ ለረጅም ጊዜ የንብረት ማስወገድ ሥራ ባለመሥራቱ ምክንያት ብዛት ያለው ንብረት፣ የአገልግሎት ዘመን ያለፈባቸው ኬሚካሎች፣ የእንስሳት መድኃኒቶችና ሰብሎች ተከማችው የሚገኙ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

 ቃሊቲ በሚገኘው የመሥርያ ቤቱ መጋዘን በክልሎች ስም የመጡ የተለያዩ ብዛት ያላቸው የግብርና መሣርያዎች፣ እንዲሁም በዕርዳታ የተገኙ ለግብርና ሥራ የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ያለአገልግሎት ተቀምጠው መገኘታቸው፣ በግብርና ሚኒስቴር ውስጥ የቁጥጥር ሥርዓት ድክመቶች መኖራቸውን የሚያሳዩ ዓይነተኛ ምሳሌዎች ተደርገው ተጠቅሰዋል፡፡

Tuesday, May 8, 2012

Eskinder Nega faces verdict on Friday

By Naomi Hunt, Press Freedom advisor for Africa & the Middle East | May 8, 2012
A verdict in the trial of critical journalist Eskinder Nega and opposition figures accused of terrorism-related crimes is expected on Friday, May 11. 

Ethiopia’s crackdown on the media and freedom of expression has received bad press around the world, with major international media covering the issue and newsmakers from all around the world speaking out against the jailing of journalists (and other government critics) on terrorism charges. 

By way of damage control, the authorities now appear to be tightening their hold on local media. Just days before a verdict is expected in the case against Ethiopian writer Eskinder Nega, another local editor was given a fine or prison sentence for his newspaper’s critical reporting of that trial, journalists told IPI. 

Further, new regulations will make printing presses responsible for pre-publication censorship to “remove any content which may be defined as “illegal” by the government,” according a report in the Daily Monitor. This is particularly bad news for local newspapers since, according to the same piece, “State-owned Birhanena Selam Printing Enterprise (BSPE) is the only printing house in Ethiopia equipped with the technological capacity to publish newspapers and has already circulated the new agreement for its customers to sign.”

Temesgen Desalegn, the chief editor of Feteh newspaper, was last week found guilty of biased reporting about the court and prosecution on the case of Nega and others, according to reports.  Desalegn was given the option of a prison sentence or a fine, and chose to pay the 2000 birr (approx. €88) fine, according to a translated news item sent to IPI by email. 

The charge against Desalegn came after Feteh ran an op-ed by opposition party member Kinfe-Michael Debebe, who is on trial along with Nega. Prosecutors claimed Debebe’s story portrayed the court proceedings as unfair and the charges against defendants as baseless, according to a report on the website of Ethiopian Satellite Television. Debebe was reportedly given an eight month sentence. 

“The authorities insist the recent cases against journalists are related to ‘terrorism’ and not to criticism, but the sentencing of Feteh editor Temesgen Desalegn and the imposition of restrictions on printing presses further undermines this argument and demonstrates the contempt Ethiopia holds for criticism and debate,” said IPI Executive Director Alison Bethel McKenzie. 

“All journalists currently jailed in the country should be freed at once, and restrictions on press freedom and access to information should be lifted.” Ethiopia has convicted and sentenced four journalists in Ethiopia to years-long prison terms within the past five months. Related News:

በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ባስነሱት ተቃውሞ በርካቶች ታስረዋል

ኢሳት ዜና:- ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም 
ተቃውሞው ምግብን ሰበብ አድርጎ እንደተፈጠረ ቢነገርም፣ የተማሪዎች ግን ከዚህ የዘለለ ነው ተብሎአል። ትናንት ከሰአት በሁዋላ የተነሳው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን ተቃውሞው ከዞኑ ፖሊስ አቅም በላይ በመሆኑ የፌደራል ፖሊስ ጣልቃ ገብቷል። 

ተማሪዎች በፖሊሶች ላይ የሚያወርዱት ድንጋይ  መምህራኑ ከግቢያቸው እንዳይወጡ አድርጓቸው እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የፌደራል ፖሊስ ግቢውን ለመቆጣጠር መሳሪያዎችን መተኮሱን አድማ በታኝ ጭስ መጠቀሙን ለማወቅ ተችሎአል።

 እስካሁን በግጭቱ ምን ያክል ሰዎች እንደሞቱ ለማወቅ ባይቻልም በርካታ ተማሪዎች ተይዘው መታሰራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። በተቃውሞውም በዩኒቨርስቲው ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። ይህን ዜና እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው።

 ከአዲስ አበባ ወደ 300 ኪሜ የሚርቀው ደብረማርቆስ የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና ከተማ ነው። በሌላ ዜና ደግሞ በምእራብ ጎጃም ዞን ከውሀ ጋር በተያያዘ በተነሳ ግጭት ሰዎች ተገደሉ ከውሀ ጠለፋ ጋር በተያያዘ በይስማላ እና ሊበን በሚባሉ ሁለት የምእራብ ጎጃም አካባቢዎች የተነሳው ብጥብጥ  የ 3 ሰዎችን ህይወት ሲቀጥፍ ፣ በርካቶች ደግሞ  ቆስለዋል።

ግጭቱ በነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ሲነገር ፣ ባህርዳር ከተማ የነበረው የፌደራል ፖሊስ ወደ አካባቢው በመሄድ ግጭቱን መቆጣጠሩን ለማወቅ ተችሎአል። ፈጥኖ ደራሽ ፖሊሶችም ግጭቱን ቀስቅሰዋል ያሏቸውን ከ40 በላይ ሰዎች ይዘው አስረዋል።

ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም እየመጣ ነው?

By Fetehe.com, ርእሰ አንቀፅ
በኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም ይመራ የነበረው አምባገነኑ የደርግ ስርዓት በኢህአዴግ መራሹ ጦር በሀይል ከተገረሰሰ እነሆ ከቀናቶች በኋላ ድፍን ሃያ አንድ አመት ይሞላዋል። ግንቦት ሃያ ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት አመተ ምህረት።

የኮሎኔል መንግስቱ መንግስት ከስልጣን መውረድን ተከትሎ አዲሱ የኢህአዴግ መንግስት የቀድሞ መንግስት በአዋጅ የሻራቸውን ህዝባዊ መብቶች በአዋጅ እንደተፈቀዱ ይፋ አደረገ። ከዚህ ባሻገር በ1987ዓ.ም. በፀደቀው ህገ-መንግስት አብዛኞቹ መብቶች (ሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች) ተካተቱና ዘላቂ ዋስትና አገኙ። ከእነዚህ ተፈቃጅ መብቶች አንዱ ኮሎኔል መንግስቱ በአዋጅ ደንግገውት የነበረው የሳንሱር /የቅድመ ምርመራ/ ስራን በአዋጅ መሻሩ መታወጁ ነው። 

ይህንንም ተከትሎ በርካታ የፕሬስ ውጤቶች በህትመት ላይ ውለው ለማየት ተቻለ። በእርግጥ በአሁኑ ወቅት በስራ ላይ ያሉት የህትመት ውጤቶች /በተለይም የጋዜጦች ቁጥር/ በእጅጉ አናሳ ነው። ይህ የሆነውም በራሱ ፍቃድ በሰጠው መንግስት የእጅ አዙር ጥቃት ነው። ነገር ግን የነበሩትን ነፃ ጋዜጦች እንዲዘጉ ሲያደርግ የተለያየ የመወንጀያ ህግ በማዘጋጀት እንጂ እንዲህ እንደዛሬው ጠራራ ፀሐይ ህገ- መንግስቱ መገርሰሱን ያረጋገጠውን ቅድመ ምርመራ /ሳንሱር/ በመመለስ አይደለም።
 
ይህ የህገ-መንግስት ጥሰት የተከሰተው በመንግስት የሚተዳደረው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ሰሞኑን ለአሳታሚዎች ‹‹የህትመት ስራ ስታንዳርድ ውል›› በሚል ርዕስ በበተነው ሰነድ ላይ ከአስቀመጠው አንቀፆች ውስጥ ህገ- መንግስቱን የሚፃረሩ በመኖራቸው ነው። በተለይ ደግሞ በአንቀጽ 10- ‹‹ህግን የተላለፈ ይዘትን አለማተም›› በሚል ርዕስ የሰፈረው ሀሳብ እንዲህ ይላል፡- 10.1 አሳታሚ በአሳታሚው እንዲታተም የቀረበለት የፅሁፍ ስክሪፕት ሕግን የሚተላለፍ ስለመሆኑ ለማመን በቂ ምክንያት ካለው አላትምም የማለት መብት አለው።

10.2 አታሚ አሳታሚው የህግ ተጠያቂነትን የሚያስከትል የህትመት ይዘት የማውጣት ዝንባሌ ያለው መሆኑን ለማመን በቂ ምክንያት ካለው በማናቸውም ጊዜ ውሉን ለማቋረጥ ወይም ለመሰረዝ ይችላል። እነዚህ አንቀፆች በግልፅ ህገ መንግስቱን የሚፃረሩ ቢሆኑም ከመንግስት በኩል እስከአሁን ድረስ ምንም የተባለ ነገር የለም። ሁላችንም እንደምናውቀው መንግስት ተቃዋሚዎቹን እና ተቺዎቹን እስር ቤት ሲያስገባ ሁልጊዜም የሚሰጠው ምክንያት ተመሳሳይ ነው ‹‹ህገ መንግስቱን ለማስከበር ነው›› የሚል። 

አሁን ደግሞ በስሩ የሚተዳደረው ተቋም በግልፅ ህገ- መንግስቱን ተፃርሮ አፋኝ ውል አቅርቦአል። ይህን እንድንል ያስቻለን በህገ-መንግስቱ አንቀፅ 21 ንዑስ አንቀፅ 3(ሀ) ‹‹የቅድሚያ ምርመራ በማንኛውም መልኩ የተከለለ መሆኑን›› በማስታወስ ነው። ከህገ-መንግስቱ በተጨማሪ ስለመገናኛ ብዙሃን ነፃነት የሚናገረው አዋጅም ተመሳሳይ አንቀፆች አሉት። 

ህዳር 25 ቀን 2001 ዓ.ም. የወጣው ነጋሪት ጋዜጣ በአዋጅ ቁጥር 590/2000 ‹‹የመገናኛ ብዙሃን እና የመረጃ ነፃነትን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ›› በሚል ርዕስ በገለፀው መሰረት በክፍል አንድ በቁጥር አራት ላይ ‹‹መገናኛ ብዙሃን ነፃ ስለመሆናቸው›› በሚለው ርዕስ ስር እንዲህ ይላል፡- 1. የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት በህገ መንግሥቱ ዕውቅና አግኝቷል። ቅድመ ምርመራ በማንኛውም መልኩ የተከለከለ ነው፡፡

እንግዲህ መንግስታዊው ተቋም ብርሃንና ሰላም ደግሞ ፅሁፉን አንብቤ ካልጣመኝ፣ ካልተመቸኝ ወይም ዝንባሌው ህግ የሚጥስ መስሎ ከታየኝ አላትምም፣ በማናቸውም ጊዜ ውሉን ለማቋረጥም የሚከለክለኝ የለም እያለ ነው። በአንድ ሳምንት ውስጥም ይህንን ውል ካልፈረማችሁ ጋዜጣችሁን አላትምም ሲል ከትላንት በስቲያ ለሁሉም ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ደብዳቤ ልኳል። ይሄኔም ነው እስከዛሬ ድረስ ‹‹ህገ-መንግስቱን አደጋ ላይ ሊጥሉ፣ ሊቃወሙ፣ ሊያፈርሱ….›› ሲያሴሩ ደረስኩባቸው እየተባለ የሚታሰሩ ተቃዋሚዎች እና ጋዜጠኞች ጉዳይ የእስራቸው ምክንያት ይበልጥ ግልፅ
የሚሆነው።

መቼም መንግስት ራሱን እንደ ጲላጦስ ነፃ አድርጎ ‹‹ጉዳዩ የአታሚውና የአሳታሚው ነው፣ እኔን አይመለከተኝም›› የሚል ቀልድ ይቀልዳል ብለን አናስብም። ምክንያቱም የሞያ አጋሮቻችንን ጨምሮ ፖለቲከኞችን ሲያስር ጆሮአችን እስኪደነቁር ድረስ የሚነገረን ‹‹ህገ መንግስቱን ለማስከበር ነው›› የሚል ምክንያት ነውና። ለዚህም ነው አሁን ብርሃንና ሰላም ከመንግስቱ ኃ/ማርያም የስልጣን እድሜ ጋር  አብሮ ያከተመውን ‹‹ቅድመ ምርመራ››፣ ህገ መንግስቱን ጥሶ በስራ ላይ ሊያውል ሲሞክር መንግስት ህገ-መንግስቱን የማስከበር ግዴታውን ይወጣል ብለን የምናስበው።
 
ይህ ሁኔታ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ በፍትህ እምነት የደርግን ሸንጎ የአንድ ፓርቲ ፓርላማን ጨምሮ የሚያስታውሰንን በብዙ ሺህ ኢትዮጵያውያን ሰማዕታቶች የወደቀው የኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም አገዛዝ በሌላ ባርኔጣ እየተመለሰ እንደሆነ ነው። ምንም እንኳን በኢህአዴግ እና በደርግ መካከል ያለው ልዩነት ጠባብ ቢሆንም ኢህአዴግን ከደርግ የተሻለ የሚያደርገው ብቸኛ ምክንያት ቅድመ ምርመራ /ሳንሱር/ በአዋጅ እንዲሻር መድረጉ ነው። 

ይኸውም ከ20 አመት የስልጣን ዘመኑ በላይ በማንም ሳይነካና ሳይሸረፍ ቆይቶአል። ዛሬ ግን ይህ መብት ቅርቃር ውስጥ ሊወድቅ ከአፋፍ ቆሟል። እናም በፍትህ ዕምነት የመንግስት አማራጭ ሁለት ብቻ ይሆናል። የመጀመሪያው  ህገ-መንግስቱን ለመገርሰስ ቆርጦ የተነሳውን ብርሃንና ሰላምን ህገ-መንግስቱን እንዲያከብር ማስገደድ፣ አሊያም በብርሃንና ሰላም በኩል ህገ-መንግስቱን በትብብር ንዶ ሙሉ በሙሉ የኮሎኔል መንግስቱን ኃ/ማርያም አገዛዝ መመለስ። መንግስት የሚወስደውን አማራጭ በቀናቶች ውስጥ የምናየው ይሆናል፡፡

ከሁመራ ከ50 በላይ ሰዎች በድጋሚ ታፍነው ተወሰዱ -አንድ ሰው ሞቷል

 Fetehe.com
በምዕራብ ትግራይ ክልል በቃፍታ ሁመራት ወረዳ ተከዜ ወንዝ ዳርቻ ‹‹ከርቸሊት›› ከምትባል አካባቢ ከትናንት በስትያ ከ50 በላይ የአካባቢው ነዋሪዎች ታፍነው ወደ ኤርትራ መወሰዳቸውን፣ አንድ ሰው መሞቱንና አራት ሰዎች ከተያዙ በኃላ ማምለጣቸውን የአካባቢው ምንጮች ለፍትሕ ገለፁ።

በአካባቢው በባህላዊ መንገድ ወርቅ በማውጣት ስራ ላይ ተሰማርተው ከነበሩት በርካታ ሰዎች መካከል ከትናንት በስትያ ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ገደማ በግምት 58 የሚሆኑ ሰዎች ባልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች ታፍነው ወደ ኤርትራ መወሰዳቸው ምንጮች ጨምረው ገልፀዋል። በወቅቱም የተኩስ ልውውጥ እንደነበረ የጠቀሱት ምንጮቻችን፣ አቶ ገ/መድህን ተክላይና አቶ ገ/መድህን ገ/ኢየሱስ የተባሉ ግለሰቦች ከተያዙ በኃላ ሮጠው ማምለጥ እንደቻሉ ተናግረዋል።

 ፍትሕም አቶ ገ/መድህን ተክላይን በስልክ ለማነጋገር ችላ ነበር፡ ፡ እንደተባለው ከአፈናው ሮጠው ማምለጣቸውን የጠቀሱት አቶ ገ/መድህን በድርጊቱም አንድ የኤርትራ ተቃዋሚ ሃይልን በተጠርጣሪነት ጠቁመዋል። መንግስት ስለጉዳይ ስላለው መረጃ ለመጠየቅ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ ቤት ሚኒስትር ዲኤታ ወደሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል ተንቀሳቃሽ ስልካቸው ላይ  ብንደውልም ስልካቸው ስለማይነሳ የመንግስትን ምላሽ ማካተት አልቻልንም።

በተመሳሳይ ሁኔታ ሚያዚያ 13 ቀን 2004 ዓ.ም. በዚሁ አካባቢ ‹‹ሀገረ ሰላም›› በሚባል አዲስ ሰፈር ከ140 በላይ ነዋሪዎች ባልታወቁ የታጠቁ ሃይሎች ታፍነው ወደ ኤርትራ መወሰዳቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ከደቡብ ክልል ቤንች ማጂ ዞን ከጉራፈርዳ ወረዳ ‹‹አረን ዳገት›› ከሚባለው አካባቢ የተፈናቀሉ 47 አባወራዎች ሰኞ ሚያዚያ 21 ቀን 2004 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ለሰዓታት ካረፉ በኋላ ወደ ትውልድ አካባቢያቸው ደብረብርሃን መጓዛቸው ታወቀ።

ከስድስት ዓመታት በላይ መኖሪያቸውን በዞኑ ማድረጋቸውን የሚናገሩት ተፈናቃዮቹ በዞኑ በሌሎች አካባቢዎች ሲካሄድ የነበረው የማፈናቀል ተግባር ቀደም ባሉት ጊዜያት እንዳልነበረ ገልፀው፣ ነገር ግን ከሚያዚያ 11 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ ‹‹ከዞኑ ጥላችሁ ውጡ›› ተብለው መገደዳቸውን ለፍትህ ገልጸዋል፡፡

‹‹ለምን ብለን በመጠየቃችን ታስረን ተደብድበናል›› የሚሉት ተፈናቃዮቹ  ‹ቤተሰቦቻችንን ወደከተማ በመሸሸግ እኛ እዛው ብንቆይም ከያለንበት በሦስት ቀናት ውስጥ ለቀን እንድንወጣና በአካባቢው ያፈራነውን ንብረት ለመሰብሰብ እንኳን ጊዜ ሳናገኝ እንድንባረር አስገድደውናል›› ብለዋል፡፡

የትውልድ አካባቢያቸው ሰሜን ሸዋ መሆኑን የሚናገሩት  እነዚህ ተፈናቃዮች ወደ ደብረብርሃን በመሄድ የዞኑ አስተዳደሩ በሌላ ቦታ እንዲያሰፋራቸው ለመጠየቅ ከላይ በተጠቀሰው እለት ተጉዘዋል፡፡

በመሀል ፒያሳ ራሱን ያቃጠለው ግለሰብ ሕይወቱ አለፈ

 Fetehe.com
ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ዕለት ፒያሳ- ዳግማዊ ሚኒልክ አደባባይ በሚገኘው የስራ ማስታወቂያ በሚለጠፍበት ጐዳና አካባቢ ሰውነቱ ላይ ቤንዚን አርከፍክፎ ራሱን በማቃጠሉ ወዲያውኑ ለሕክምና የካቲት 12 ሆስፒታል ገብቶ የነበረው ዳዊት ለንዳሞ በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ እሁድ ዕለት ሕይወቱ ማለፉ ታውቋል።

‹‹የፖሊስ አባል ነበረ›› የተባለው ዳዊት ለንዳሞ፣ ረቡዕ ዕለት ከድንገተኛ ክፍል ወደ ቃጠሎ ሕክምና መኝታ ኬዝ ቲም ተዘዋውሮ በሆስፒታሉ ሕክምና እየተከታተለ ነበር፡፡

ሆኖም ግለሰቡ የደረሰበት ቃጠሎ ጥልቀት ስለነበረው እሁድ እለት ከጠዋቱ 1፡ 30 ሰዓት ገደማ ሕይወቱ እንዳለፈ የሕክምና ክፍሉ ኃላፊ ሲስተር ታደለች በቀለ ለፍትሕ አስረድተዋል።

ወደ ሆስፒታሉ ከገባ ጊዜ ጀምሮ ከጓደኞቹ በስተቀር ዘመዱ ነኝ ያለ ማንም ሰው እንዳልነበረ  ስታወሱት ኃላፊዋ ለቀናቶች የሕክምና ወጪውን የቻለለት ሆስፒታሉ መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል። በቃጠሎው ምክንያት ህይወቱ ያለፈው የዳዊት ለንዳሞ አስከሬን ወደ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል መላኩን ሲስተር ታደለች ጨምረው ለፍትሕ ገልፀዋል።

ግለሰቡ በወቅቱ ራሱን ሲያቃጥል ‹‹የምበላው አጣሁ፣ ምን ልብላ?›› ሲል እንደነበረ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች በወቅቱ በቦታው ደርሶ ለነበረው የፍትሕ ዘጋቢ መግለፃቸውን በመጥቀስ ባለፈው ሳምንት እትማችን ዜናውን ማስነበባችን ይታወሳል።

አገር በምን ይፈርሳል?

ተመስገን ደሳለኝ, (www. Fetehe.com)
በእርግጥም ይህ ወቅት በዚህ ጉዳይ ላይ እንድንነጋገር የምንገደድበት ነው። ጉዳዩ የግራ-ዘመሞች ወይም የቀኝ መንገደኞች ፖለቲካ አይደለም። ጉዳዩ ኢህአዴግን የመጥላት ወይም የመውደድ አይደለም። ጉዳዩ መለስ ስልጣናቸውን ይለቃሉ ወይስ አይለቁም የሚል አይደለም። 

ጉዳዩ የገዥው ፓርቲ ወይም የተቃዋሚዎችም አይደለም… የሀገር ጉዳይ እንጂ። ስለዚህም የፖለቲካ ልዩነቶች እንደተጠበቁ ሆነው ስለሀገራችን መፃኢ ዕድል በግልፅ ተነጋግረንበት፣ ተወያይተንበት ማሰሪያ ካላበጀንለት ድንገት ከእጃችን ወጥቶ የፈሰሰ ውሃ… ሊሆን ይችላል። እናም ከድንገቴው ቀን በፊት እንወያየበት፡፡ 

አዎን! በኢህአዴግ አብዮታዊ ዴሞክራሲ አሊያም በመድረኩ ሌበራል ወይም ሶሻል ዴሞክራሲ መቻቻል እና መደራደር ይቻላል። ከፀሀይ በታች ምንም አይነት ድርድር የማይኖረው በሀገር ጉዳይ ብቻ ነው፡፡ በዚህ ከተስማማን ቀጣዩ ጥያቄ ሀገር ማለትስ ምን ማለት ነው? የሚል ይሆናል ማለት ነው። በእርግጥ ሀገር ማለት ፖለቲካ አይደለም። ስልጣንም አይደለም። ስርዓትም አይደለም። 

መንግስትም አይደለም። ኢህአዴግ ማለትም አይደለም፤ መድረክና የመሳሰሉት ተቃዋሚዎችም እንደማለት አይደለም። …እነዚህ ሁሉ ‹‹ከሀገር በእጃችን›› ፍልስፍና በኋላ የሚመጡ ጥቅማጥቅሞች ወይም ጥያቄዎች ናቸው። ለእዚህም ነው ‹‹ሀገር›› የእነዚህ ሁሉ ማዕቀፍ ነው እያልኩ ያለሁት።

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም በ1966 ዓ.ም. ‹‹ኢትዮጵያዊነት-ልማት በህብረት›› በሚል ርዕስ በፃፉት መጽሐፍ ላይ የሀገርን ትርጓሜ እንዲህ ይገልፁታል፡- ‹‹ አገር ማለት በአንድ አይነት ሕግና በአንድ መንግስት ጥላ ስር የሚተዳደሩ ሰዎች (ህዝብ) ባለመብት የሆኑበትና የኑሮአቸው መሰረት የሚያደርጉት በወሰን የተከለለና የማይደፈር መሬታቸውን ጨምሮ የሚገልፅ ህብረት ነው።››ደህና! ይህንን ትንታኔ ይዘን፣ ከሀገር ስለሚገኝ ማንነት አሁንም ፕሮፍ በ1986 ዓ.ም. ‹‹ኢትዮጵያ ከየት ወዴት?›› በሚል ርዕስ ስር ከፃፉት መጻፍ እንይ፡-

‹‹ኢትዮጵያዊነት ብዙ የተለያዩ ህብረተሰቦች የተዋሃዱበት አካል ክፍል መሆን ነው። ኢትዮጵያ ከጎሰኝነት በላይ እና ውጭ የሆነ አጠቃላይ ማንነት ነው። ኢትዮጵያዊነት የዚህች ውጥንቅጥ መሬት ባለቤትነት ነው፤ ኢትዮጵያዊነት የደጋው ብርድና የቆላው ሙቀት የሚገናኙበት የደጋው ዝናም ከቆላው ወንዝ ጋር የተዛመደበት ኃይል ነው። ኢትዮጵያዊነት ለሙሴ፣ ለክርስቶስና ለመሀመድ የሚጨሰው ዕጣን በእርገት መጥቶ የሚደባለቅበት እምነት ነው። 

ኢትዮጵያዊነት በቄጠማ ጓዝጓዝ ላይ የሚታየው መተሳሰብም መፈቃቀርም ነው። ኢትዮጵያዊነት የአስተዋይነት፣ የሚዛናዊነትና የጨዋነት ባሕርይ ነው። ኢትዮጵያዊነት ረዥምና ተጽፎ ያላለቀ ታሪክ ነው፤ ብዙ ሰዎችም የተሰዉለት ስሜት ነው…›› ይሉናል። በግሌ ከዚህ በታችም ሆነ ከዚህ በላይ በኢትዮጵያዊነታችን ላይ ትንተና ባይሰጥ እወዳለሁ። ምክንያቱም ለእኔ ኢትዮጵያዊነት ይህ ‹‹ህብር›› እንጂ ብሔር ብሔረሰብ… አይደለም። 

እንግዲህ ዛሬ ማዶ እና ማዶ ይዘን የምንናቆርበት ኢትዮጵያዊ ማንነታችን እና ኢትዮጵያ ሀገራችን በዚህ ቅፅር የተዋቀሩ ናቸው። ስለዚህም እውነት እውነት እላችኋለሁ ይህ ቅፅር ለየትኛውም የፖለቲካ አመለካከት ወይም ልዩነት ሲባል ሊፈርስ አይገባውም፡፡ ልዩነት ያልፋል፤ ሀገር ግን አያልፍም። እናም ‹‹አገር›› እና ‹‹ማንነት›› ብለን የተስማማንባት ‹‹ኢትዮጵያ›› ለፖለቲካዊ ጥቅም ሲባል ብቻ ለማፍረስ መሞከሩ አደገኛ መሆኑን ከሌሎች ተሞክሮ ልንማር ይገባል።

 ይህ ስጋት የቁም ቅዠት አይደለም፣ ይልቁንም ከበር እየደረሰ፣ ነገር ግን ልናስተውለው ያልቻልነው ግዙፍ አደጋ ሆኖብናል። በእርግጥ ቀናነቱ ካለ አደጋውን መከላከል ይችላል። ዋናው ከቀድሞ አምባገነኖች መሪዎቻችንን የመጨረሻ ሰአት ‹‹አርቆ አሳቢነት›› መማር ነው። በተለይም ከአፄ ኃይለስላሴ እና ከኮለኔል መንግስቱ ኃይለማርያም። አፄው ስልጣናቸውን በሀይል ሊነጥቁ የተነሱ ወታደሮች ግራና ቀኝ እንደብራና በወጠሯቸው ጊዜ ምን ነበር ያሉት? …‹‹ለህዝባችን የሚጠቅም ከሆነ ሁሉንም ነገር ፈቅደናል።

 ነገር ግን አደራ ይችን ሀገር በችኩልነት እንዳታፈርሷት›› ነው ያሉት። ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማሪያምም መጨረሻቸው በደረስ ጊዜ በአቅራቢያቸው የነበሩትን ወታደሮች አሰባስበው የሞት የሽረት ትግል አላካሄዱም፣ ይልቁንም ‹‹ሀገርም ህዝብም ከሚጠፋ እኔ ልጥፋ›› ብለው ነው የኮበለሉት፡፡ ይህንን ነው ሀገር ከፖለቲካ ድልና ሽንፈት በላይ ነው እያልኩ ያለሁት፡፡ አፄውና ኮለኔሉ ‹‹በስልጣናችን የመጣውን ገለን እንሞታለን›› ቢሉ ኖሮ ዛሬ ሀገራችን በተለያዩ የዘውግ አንጃዎች የምትመራ ብጥቅጣቂ በሆነችም ነበር፡፡

የሆነ ሆኖ ባለፉት 20 አመታት በኢትዮጵያ በመሬት ያለው ፖለቲካ ሀገር ሊያፈርስ የሚችል እንደሆነ በቂ ምልክቶች እየታዩ ነው። ይህን ማለቴን የፖለቲካው የሀሳብ መሀንዲስ የሆነውን ኢህአዴግን ከመጥላት እና ከመውደድ ጋር በፍፁም መገናኘት የለበትም። ስለአምባገነንነትም አይደለም እያወራሁ ያለሁት። ለአምባገነንነት፣ ለአምባገነንነትማ ከኢህአዴግ በፊት ሀገራችንን የመሩት በሙሉ አምባገነኖች ናቸው። ስለምርጫ ማጭበርበርም አይደለም።

 የቀድሞዎቹ ጭራሹንም ምርጫ የሚባል ፖለቲካ መኖሩን አያውቁም፡፡ እያልኩ ያለሁት እነዚህ ሁሉ ሀገር ሲኖር የሚኖሩ ናቸው ነው። ይህንን በግልፅ መነጋገር ይኖርብናል። የኒኮላስ ማኪያቬሊ ‹‹ለሉዑላኑ እውነትን መንገር አንገት ያስቀነጥሳል›› የሚለውን ሰንካላ ምክር ሰምተን በፍርሃት መታጀል የለብንም። አሊያ ደግሞ ከአንገት መቀንጠስ እና ከሀገር መቀንጠስ አንዱን መምረጥ ይኖርብናል። …እንደኔ እንደኔ ከሆነ የአንገት መቀንጠሱን መርጠን ስለሀገራችንእንነጋገር፡፡ 

ኢህአዴግ የሚከተለው የዘውግ ፖለቲካ አደጋ ላይ መውደቅ የጀመረው ገና ከጠዋቱ ነው። ከሽግግር መንግስቱ ውስጥ ሰፋ ያለ ውክልና ይዞ የነበረው የአሁኑ ‹‹ሽብርተኛ›› የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) ከኢህአዴግ ጋር የነበረውን በርካታ ልዩነት ተከትሎ ‹‹ከክልሌ ውጡ›› ወደሚል የፖለቲካ አቋም የመጋፋት አዝማሚያ ያሳይ ነበር። ይህም በርካታ ዋጋ አስከፍሏአል። በእርግጥ ለኦነግም ሆነ ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች ይህንን መሰል ፅንፍ ላይ ይቆሙ ዘንድ መደላደል የሆነላቸው ኢህአዴግ የቆመበት የዘውግ ፖለቲካ መሆኑ አያከራክርም። 

የህወሓት የርዕዮተ-ዓለም መሀንዲሶች ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታም ሆነ የረዥም ዘውግ ታሪክ በተቃርኖ የሚቆም ንድፈ ሀሳብን እንደ ፖለቲካ ፕሮግራማቸው ሲወስዱት ከ90 በመቶ በላይ የሆኑት ተከታዮቻቸው (ተዋጊዎቻቸው) ጉዳዩን ለመረዳት ያላቸው አቅም ውስን በመሆኑ የትጥቅ ትግሉን በበላይነት ከመወጣት አልፈው የመንግስት ስልጣን ይዘው እስኪተገብሩት እና ችግሮች እስኪከሰቱ ድርስ የሞቱለት አላማ ይህ መሆኑን በሚገባ አልተረዱም።

 ስለዚህም ‹‹ሀገሬ››ን ብለው ‹‹ዱር ቤቴ›› ያሉ ታጋዮችን በጅምላ መውቀሱ በራሱ ስህተት ነው። ይህ ኃላፊነት / ተጠያቂነት/ የአመራሩ ነው ሊሆን የሚችለው። ሆኖም የዚህ ፅሁፍ አላማ አመራሩን መውቀስ አይደለም። አላማው ዛሬም ቢሆን አረፈደምና ከድጋፍና ከተቃውሞ ክልል ባሻገር ርዕዮት አለሙን በየትኛውም ወገን ያለ ካድሬ እንዲፈትሸው ግፊት ማድረግ ነው፡፡

በነገራችን ላይ ኢህአዴግ የሚከተለውን አይነት የፖለቲካ ፕሮግራም ተከትሎ ሀገር ያስተዳድረ ወይም አያስተዳድረ ያለ /የተሳካለትም ያልተሳካለትም/ መንግስት ለማግኘት ብትፈልጉ ደክማችሁ ትተዉታላችሁ እንጂ አታገኙም። ምክንያቱም ይህ ንድፈ ሃሳብ በሌሎች ሀገራት በታሪክም ሆነ በህይወት የለምና፡፡ ምንአልባት በሙዚየሞቻቸው ልታገኙት ትችሉ ይሆናል፤ በተቀረ... ተቀበልነውም አልተቀበልነውም በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ በአለማችን በብቸኝነት ቆሞ ያለው ኢህአዴግ ብቻ ነው፡፡ 

ስለዚህም ንድፈ ሃሳቡን ራሱ ልናየው የምንችለው ያለማነፃፀሪያ ነው ማለት ነው። ልክ ‹‹የተዘጋች ቤተ መቅደስ›› ትባል እንደነበረው የኤኒቨር ሆጃ አልባኒያ።… ለነገሩ የአልባኒያ መንፈስ በዚህም ቤት ያለ ይመስለኛል። ዘውገኝነቱ ግን እዚህ ይብሳል። ጉዳቱም የከፋ ነው፡፡ለዚህም መሰለኝ የ‹‹ዘውግ ፖለቲካ››ን ‹‹አፍራሽ›› ሲሉ የፖለቲካ ተንታኞች የሚተቹት። ይህ እውነት ቢሆንም አምባገነኖች ብዙውን ጊዜ አገዛዙን ከአደጋ ለመጠበቅ ሲሉ ብቻ የዘውግ ፖለቲካን እንደሚከተሉ ምሁራኖች ይናገራሉ። ይህ ደግሞ ለNational security (ለሀገር ደህንነት) ፍፁም አደገኛ በመሆኑ ውሎ አድሮ ሀገር ከማፍረስ አይመለስም።

ከሀገሪቱ የረዥም ዘመን ታሪክ ዘውገኝነትን እንፈልግ ብንል በ‹‹ወንዝ›› የተከፈለ አስተዳደር የምናገኘው ምናአልባት “The Era of princes” /ዘመነ መሳፍንት/ እየተባለ በታሪካችን በሚጠቀሰው ጊዜ ነው። በዚያ ወቅት የነበረው የሀገሪቱ አስተዳደር በጎበዝ አለቃ (በራስ፣ ደጃዝማች፣ ፊታውራሪ…) ከመከፋፈሉ ውጭ በኢትዮጵያ የነበረው “Power struggle” (የስልጣን ትግል) እንጂ የ‹‹ወንዝ›› (የክልል) ፖለቲካ አልነበረም። በ‹‹ፊውዳል››ነቱ የሚወቀሰው የነገስታቱ አገዛዝ ከፈረሰ በኋላ የተተካው የደርግ ስርዓት የለየለት አምባገነን ነው። 

 ሁሉንም ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶችን በድብቅ ሳይሆን በይፋ ገርስሶአል። ነገር ግን ርዕዮተ አለሙ የተቀኘው በሀገር አንድነት ላይ ነው። እንዲያውም ስርዓቱ መላውን የስልጣን ዘመኑን የጨረሰው ‹‹እንገንጠል›› እና ‹‹እንከለል›› ከሚሉ ብሔርተኛ ቡድኖች ጋር ‹‹አንድ ሀገር አንድ ህዝብ›› በሚል አቋም በጦር መሳሪያ ሲፋለም ነው። ‹‹አብዮታዊ እናት ሀገር ወይም ሞት›› የሚለው መፈክርም ቢሆን የፖለቲካው ፍልስፍና መገለጫ ከመሆኑም ባሻገር ሀገራዊ ብሔርተኝነትን ለመፍጠር የነበረው አስተዋፅኦ በቀላል የሚታይ አይደለም። ነገር ግን ይህ ‹‹የአንድ ሀገር አንድ ህዝብ›› ፖለቲካ በኃይል ከተሸነፈ በኋላ በዘውግ ፖለቲካ ተተክቶአል፤ መፈክሩም ከ‹‹እናት ሀገር…›› ወደ ‹‹ብሔር ብሔረሰቦች…›› ተቀይሯል።

በእርግጥ ይህን ንድፈ ሀሳብ እስታሊናዊ ትንታኔ የሚሰጡት ቢኖሩም፣ ከማኪያቬሊ Divided and Rule (ከፋፍለ ግዛ) ፍልስፍና ጋር የሚያቆራኙት ይልቃሉ። ይህ ፍልስፍና ለ‹‹ቅኝ አገዛዝ›› አስተዳደር ተግዳሮቶችን መሻገሪያ ይሆን ዘንድ እንግሊዝ ወደ መሬት በማውረዱ ግንባር ቀደም ነች። በቅኝ ግዛት ዘመን እንግሊዞች ይከተሉት የነበረው አስተዳደር Indirect Rule (የዘወርዋራ አስተዳደር) ሲሆን ይህንንም ለመተግበር የግድ በኃይል የያዙትን ሀገር በዘውግ ወይም በሃይማኖት ይከፋፈሉታል። እንደምሳሌ የቀድሞዋን ‹‹ሮዲዥያ›› ዛምቢያ እና ዙምባቤ ሲሉ በዘውግ የከፈሉበትን ወይም ህንድና ፓኪስታንን በሃይማኖት ከፈለው ሁለት ሀገር ያደረጉበትን ታሪክ ማየት እንችላለን።

ጉዳዩን ወደ ኢትዮጵያ ስናመጣው ደግሞ የዘውግ አስተዳደሩ ሀገሪቱን ከአንድ ሀገር ወደ ዘጠኝ ክልሎች የሸነሸነበትን ፖለቲካ እናገኛለን። ይህ ሁኔታ በወቅቱ ብዙ የተተቸ እና ተቃውሞ የደረሰበት ቢሆንም ኢህአዴግ በበኩሉ ትችቱን ‹‹የነፍጠኛ ተቃውሞ›› እያለ ሲያጣጥለው ቆይቶአል። ሆኖም በብዙ ምሁራኖች ‹‹የከፋፍለ ግዛ እስትራቴጂ ነው›› በሚል ይቀርብ የነበረው አሳማኝ ትንተና ዛሬ ላይ ሲታይ ለእውነታው በእጅጉ የቀረበ እየሆነ ነው። አደጋው ምን ያህል እየቀረበ እንደሆነ ለማወቅ ሁለት ምሳሌዎችን ብቻ እንይ፡፡ የጋምቤላን እና የጉራፈርዳን።

እንደሚታወቀው ከ1983 ዓ.ም. በፊት የዛሬው ጋምቤላ ክልል በኢሊባቡር ክፍለ ሀገር ስር የሚገኝ አንድ የሀገሪቱ ክፍል ነው። ነዋሪዎቹም የአካባቢው ተወላጆች የሆኑትን ኑዌር፣ አኝዋክ፣ ኢታንግን… ጨምሮ በደርግ Resettlement program (የሰፈራ ፕሮግራም) ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የመጡ ኢትዮጵያውያኖች ናቸው። ደርግ ሰፈራውን ሲያካሂድ እንደምክንያት የአስቀመጠው ሁለት ነገሮችን ነው። የመጀመሪያው በአካባቢው የነበረው የእርሻ ስራ ኋላ ቀር በመሆኑ አዲስ መጤዎቹ ያስተምሯቸዋል፣ የባህል ልውውጥ ይኖራል፣ ሀገራዊ አንድነት ይጠናከራል፣ ከዘውግ ይልቅ ኢትዮጵያዊ ማንነት ይጎለብታል የሚል ሲሆን ሁለተኛው በድርቅ የተጠቁ አካባቢ ነዋሪዎች ሰፋፊና ለም ሆና ነገር ግን ስራ ላይ ያልዋለ መሬት ወዳለበት አካባቢ የማስፈር እቅድ ድርቅን ለመከላከል ፋይዳ አለው በሚል ነው። 

እንግዲህ ወደ ኢሊባቡር /ጋምቤላ/ የተካሄደው ሰፈራ ከእዚህ አንፃር ነበር። ሆኖም በ1983 የመንግስት ለውጥ ሲመጣ የርዕዮተ- ዓለም ለውጥም አብሮ መጣ። ያ ርዕዮተ-ዓለም የሚያበረታታው ደግሞ ሀገራዊነትን ሳይሆን አውራጃዊነትን ሆነ። እናም ትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሞና ጋምቤላ… እየተባለ በዘውግ መከለል ሲጀመር ቀድሞ የነበረው ‹‹ኢትዮጵያዊነት›› ብዥታ ውስጥ ገባ። ለምሳሌ በጋምቤላ የአካባቢው ተወላጆች ከሌላ አካባቢ ከመጡት ይልቅ ንፁህ ጋምቤላዊነትን ያንፀባርቁ ጀመር፤ ከዚህም አልፎ ከአማራ አሊያም ከትግራይ የመጣው ኢትዮጵያዊ የሁለት ዕድል ተጠቃሚ ተደርጎ በጋምቤላ ተወላጆች ዘንድ ተወሰደ። 

ይህም ብቻ አይደለም ጋምቤላ ያልተወለደ በጋምቤላ እንደሁለተኛ ዜጋ የመታየቱ አዝማሚያ ለ‹‹መጤው›› የመጀመሪያ ዜጋ ሊሆን የሚችልበትን የተወለደበትን ክልል እንዲያልም አስገድዶታል። ይህ ደግሞ ሀገሬ የሚለው ኢትዮጵያን ሳይሆን የተወለደበትን አካባቢ እንዲሆን ገፍቶታል። ዛሬ በጋምቤላ ያለው ያለመግባባትም ኢህአዴግ እየተከተለ ካለው የዘውግ ፖለቲካ ፍልስፍና የሰረፀ እንጂ ከሰማይ እንደመብረቅ የወረደ ዱብ ዕዳ አይደለም። 

ከዚህ በተቃራኒ የሚቆም ተሞክሮ እንደ ምሳሌ ማየት ካስፈለገ ደግሞ አሜሪካንን እና ጣሊያንን ማየት እንችላለን። መቼም የአሜሪካን ቀዳማይ መስራች አባቶች ታሪክ እንደሚነግረን ታላቂቷን አሜሪካ የገነቡት ተወላጆቹ ሳይሆኑ፤ መጤዎቹ ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ ለረዥም አመት ራሳቸውን ‹‹አሜሪካዊ›› አድርገው በሚቆጥሩ ዜጎች መካከል ከፍተኛ ክፍተት ተፈጥሮ ነበር፡፡

 ይህን ጊዜም ነው አሜሪካኖች ‹‹ምንጊዜም አሜሪካ›› የሚለው መንፍስ ይቀድም ዘንድ በተወላጆቹ (ሬድ ኢንዲያን) እና በመጤዎቹ (አንግሎሳክሰን፣ ኤዢያ፣ አፍሪካውያን…) መካከል ልዩነት ይጠፋ ዘንድ ቀን ከለሌሊት የሰሩት፡፡ ለዚህ ፍልስፍናም በዋናነት የተጠቀሙት የሰፈራ ፕሮግራምን ነው። በእርግጥ የአሜሪካኖቹ የሰፈራ ፕሮግራም በአንድ አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎችን ከቦታቸው በማስነሳት ወደሌላ ቦታ በመውሰድ አይደለም፡፡ የእነሱ የሰፈራ ፕሮግራም የተተገበረው ተቋምንና ሪሶርስን በማንቀሳቀስ የተከናወነ ነው። ለምሳሌ አንድ ግዙፍ ተቋም ከነበረበት ቦታ ተነስቶ ‹‹ተገለልን›› የሚሉ ዜጎቸ ወደሚበዙበት አካባቢ እንዲሄድ ይደረጋል።

 ይህንንም ተከትሎ ከተቋሙ ጋር ግንኙነት ያላቸው በርካታ ሰዎች አብረው ይሄዳሉ። በዚህም የባህል እና የልምድ ልውውጥ ያደርጋሉ። ይህ ሁኔታም ውሎ አድሮ ልዩነታቸውን እያጠበበው አንድነታቸውን እያጠናከረው ዛሬ የደረሱበት ታሪክ ላይ አድርሶአቸዋል። በጣሊያንም ያለው ይህ ነው። የጣሊያን ትርክት እንደሚያስነብበን ደቡብ ኢጣሊያ (ሲሲሊ) እና ሰሜኑ በስልጣኔ በእጅጉ የተራራቁ ከመሆናቸውም ባሻገር አብዛኛው የሲሲሊ ተወላጅ እራሱን እንዲሲሲሊያውያን እንጂ እንደ ጣሊያናዊ አይቆጥርም። ይህ ችግርም ይቀረፍ ዘንድ መንግስት የአሜሪካኖቹን አይነት የሰፈራ ፕሮግራም በስራ ላይ እያዋለ ነው።

 በዚህም መሰረት የሮም መንግስት ግዙፍ ተቋማትን ከሮም ወይም ከሚላንእና ከመሳሰሉት የአደጉ ከተሞች ነቅሎ ሲሲሊ ላይ ይተከላል። ይህን ጊዜም በርካታ የተቋሙ ሰዎች አብረው ወደ ሲሲሊ ይሄዳሉ። የሲሲሊ ተወላጆችም በተቋሙ ምክንያት የስራ እድልን ጨምሮ የባህል፣ የልምድ…ልውውጥ የሚያደርጉበትን አጋጣሚ ያገኛሉ። ከዚህ ሌላ ከሲሲሊም ወደ ሰሜን ጣሊያን የሚሄዱበትን የተለያዩ ስልቶች ጣሊያን ትጠቀማለች። በዚህም በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሲሲሊ ተንሰራፍቶ የነበረውን የማፊያ መዋቅር ብቻ ሳይሆን ሲሲሊያዊነትንም ሰባብረው ጣሊያናዊነትን እየገነቡ ነው። ይህ ሁኔታም ውሎ አድሮ ንፁህ ሲሲሊያዊ የሚል ስሜትን አዳክሞ አንድነትን ያጎለብታል።

ወደኢትዮጵያ ስንመጣ የምናገኘው የዚህን ግልባጭ ነው፡፡ ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ አማራዊነት፣ ትግሬያዊነት፣ ኦሮሞአዊነት፣ ጉራጌያዊነት…፤ ከአንድነት ይልቅ መከፋፈል ላይ፣ ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ አውራጃዊነት ጥሰው እንዲወጡ እየተመቻቸላቸው ነው፡፡ የጉራፈርዳ ቀውስም ከዚሁ የመነጨ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ እንዳሉት በጉራፈርዳ የሰፈሩት የምስራቅ ጎጃም ተወላጆች ናቸው።

 ሆኖም እነዚህ ሰዎች ወደጉራፈርዳ እንዴት መጡ የሚለውን እንይ፡ ፡ ኢህአዴግ በሚከተለው የፖለቲካ ፍልስፍና ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ ክልላዊነት ጎልቶ ወጥቶአል። ክልላዊነት ብቻም አይደለም ዞናዊነትም እንዲሁ እየጎለበተ ነው። ከዚህ ቀደም ስልጤ በዞን ደረጃ ይዋቀር ዘንድ የአካባቢው ተወላጆች ያደረጉትን የፖለቲካ ትግልና የተሳካላቸውን ተሞክሮ ማስታወስ ያስፈልጋል።

 እናም የጉራፈርዳ እና የምስራቅ ጎጃም ትስስር እንዲህ የጀመረ ነበር። …ከለታት በአንዱ ቀን ቤንች ማጂ ዞን ውስጥ የሚኖሩ የሚንጥ ተወላጆች ‹‹በዞን ደረጃ እንዋቀር›› ሲሉ ለክልሉ መንግስት ጥያቄ ያቀርባሉ። በወቅቱ የሚንጥ ተወላጆች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ የክልሉ መንግስትም ቁጥራቸው በዞን ደረጃ ለመዋቀር የሚያስችል እንዳልሆነ ይነግራቸዋል። ይህን ጊዜም ምስራቅ ጎጃም አካባቢ ያሉ ሰዎች ወደ አካባቢያቸው መጥተው እንዲሰፍሩ እና ለም የሆነ የእርሻ መሬት እንዲወስዱ የሚንጥ ኤሊቶች ያስተባብራሉ።

 ከዚህ በኋላም የምስራቅ ጎጃም ነዋሪዎች ቤንች ማጂ ዞን መጡ። የሚንጥ ተወላጆችም በዞን ደረጃ የመዋቀር ጥያቄያቸውን ድጋሚ አቀረቡ። አዲስ ሰፋሪዎቹም (ከምስራቅ ጎጃም የመጡት) ተቆጥረው በዞን ደረጃ ለመዋቀር ስላስቻላቸው ‹‹ጉራፈርዳ›› የሚባል ዞን ተዋቀረ። ይህ ከሆነም ከአመታት በኋላ ነው የ‹‹ውጡልን›› ፖለቲካ የመጣው።ይህ አይነቱ ፖለቲካ ነው ሀገር የሚያፈርሰው፡፡ ውጡልን፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በፓርላማ ባቀረቡት ንግግር ‹‹ውጡልን››ን የደገፉት ይመስላሉ። ልክ ምስራቅ ጎጃም ከኢትዮጵያ ውጭ ወይም አፍጋኒስታን አካባቢ ያለ ይመስል ደጋግመው በጎ ባልሆነ መንፈስ ሲያነሱት ነበር። 
 
መቼም ይህ ጨዋታ አደገኛ መሆኑን የእድሜያቸውን አብዛኛውን ክፍል በፖለቲካ ውስጥ ላሳለፉት ጠቅላይ ሚንስትር ይጠፋቸዋል ማለት ይከብዳል፡፡ ምክንያቱም ነገ አማራው ተነስቶ ‹‹ውጡልኝ›› ቢል ወይም ሌላው ብሔር የብሄሩ ተወላጅ ያለሆነውን ‹‹ከክልሌ ውጣልኝ›› ቢል ሊከሰት የሚችለው አደጋ የፖለቲካ ለውጥ ወይም የመንግስት ለውጥ ብቻ አምጥቶ የሚያባራ አይደለም፡፡ ይልቁንም ሀገርን ነው የሚያፈርሰው፡፡ እናም እስከዛሬ ስንነታረክበት እንደነበረው ‹‹በጆንያ ውስጥ ማን የበላይ ይሁን?›› ከሚለው የፖለቲካ ቁማር በዘለለ ጆንያውን ቀዶ ለመውጣት ባንሞክር ይሻላል፡፡

 የዘውግ ፖለቲካ ቀዳሚው መዘዝን ተንታኞች ‹‹አስበልጦ የመጫረት አባዜ›› /Ethnic Outbidding effect/ ሲሉ የሚጠሩት ‹‹ፖለቲካዊ ዕዳ›› ነው። የተንታኞቹ ድምዳሜ የዘውግ ፖለቲካ የአደባባዩ ብቸኛ ተዋስኦ ሲሆን የየብሔሮቹ ልሂቃን የተሻለ የፖለቲካ ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ የየብሔሮቻቸውን ጥያቄዎች አጎነው እና አክርረው ያቀርቡታል። በዚህ አካሄዳቸውም በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የትኞቹም ብሔሮች እርስ በርስ የሚኖራቸውን ግንኙነት በእጅጉ ያሳሳዋል። እናም የዘውግ ፖለቲካ በበለጠ ሲፋፋ በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙት ፖለቲከኞችም በሀገራዊ ጥያቄ ላይ አብረው ከመቆም ይልቅ በየብሔሮቻቸው ሼል ውስጥ ይቀረቀራሉ። የዚህ ተራዛሚ ተፅዕኖ ሀገራዊ የጋራ የማንነት ጥያቄን ማደብዘዝ ይሆናል እንደተንታኞች አረዳድ።

ለዚህም ነው ኢህአዴግ አምባገነን ነው፣ የለም ዴሞክራት ነው፤ ምርጫ ያጭበረብራል፣ በፍፁም ህዝቡ ነው የመረጠው፤ በሰላማዊ ትግል ይለቃል፣ አይለቅም… በመሳሰሉት የፖለቲካ ጨዋታዎች ከመቆመር በዘለለ ስልጣንን ለመጠበቅ ሲባል መከፋፈልን እና አንዱ ሌላውን ‹‹ከክልሌ ውጣ›› ሲል በማይታይ እጅ ማጨብጨብና መገፋፋቱ ፖለቲካ ሳይሆን ሀገር ማፍረስ ነው የምለው። ፖላንድ እ.ኤ.አ. በ1919ዓ.ም እስከተፈረመው የቫርሳይለስ ስምምነት ድረስ ከ200 አመት በላይ ከአለም ካርታ ላይ ጠፍታ ነበር።

 አርማኒያም በሌኒን ሩሲያና በከማል አታ ቱርኪ ወረራ ከምድረ ገፅ ጠፍታ እንደነበረ ማስታወሱ ጠቃሚ ነው። በእርግጥ ለፖላንድ እና ለአርመኒያ መጥፋት የውጭ ተፅዕኖን እንደዋነኛ ምክንያት ልናነሳው እንችል ይሆናል። ነገር ግን የዚያድባሬን ታላቂቷ ሶማሊያ ለአራት መበጣጠስ ከውጭ ተፅዕኖ ጋ በፍፁም አናገናኘውም። እናም 50 እና 60 አመት በስልጣን ለመቆየት ይህን አይነቱን የፖለቲካ ሴራ ባናሴር የተሻለ ነው። ትውልድ በትውልድ ይተካል፤ ሀገር ግን...ከላይ በማሳያነት የጠቀስኳቸው የጋምቤላ እና የጉራፈርዳ ሁነቶች በግሪክ ስነ- ተረት /Mythology/ ላይ የሚተረከውን የ‹‹ፓንዶራ ሳጥን›› /Pandora’s box/ ወግ ያስታውሰኛል።

 ሲነገራት አልሰማ ያለችው ፓንዶራ የህይወት መከራዎችን ያጨቀውን ሳጥን ገፍታ ጣለችው። ሳጥኑን በፍጥነት ወደነበረበት ለመመለስ የሞከረው አባቷ /ባሏ/ ሳጥኑን ሲዘጋ በውስጥ የቀረው ተስፋ ብቻ ነበር ይላል የግሪኩ ተረት። እናም የሰው ልጅ በተስፋ ብቻ ይኖር ዘንድ ግድ ሆነ። የዘውግ ፖለቲካን አሁን ባለው መልክ እንዲቀጥል መፍቀድ ሀገራችንን ሊያፈራርሱ የሚችሉ የግጭት መስመሮችን ወደአደባባዩ ማምጣት እንደሆነ የሃያ ዓመቱ የፖለቲካው ጉዞ እያሳየን ነው። እነዚህ መከራዎች አንዴ ከሳጥናቸው ከወጡ በምን እንመልሳቸዋለን? እንዴትስ መልሰን ኢትዮጵያን ልናገኛት እንችላለን?

Sunday, May 6, 2012

 By Yuunus Hajji Mul’ataa in Addis Ababa
ADDIS ABABA - Ethiopian Muslim protests spread across the country on May 4 when hundreds of thousands in the Ethiopian capital defied government threats and went on protesting against the “Ahbashism Campaign” instigated by the government and “Majlis”.
       
Observers agree the brutal killing of innocent people in Assasa town has fueled tension between the government and the Muslim community which has now drawn more towns into the strikes.Meanwhile, the Ethiopian Government said on Friday night that it has expelled two Arabs who came to call for “Jihad” and incite violence at the grand Anwar Mosque of Addis Ababa. However, the report is dismissed by many Muslims as “a fabricated story”.

Protests and Silencing  

Shocked by the mass uprising after the recent killing of seven innocent Muslims in Assasa town (Arsi province), government authorities were busy on defending the massacre and threatening the public through state-owned media. They were also mobilizing Ahbash adherents to deter the protests in the upcoming days. The imams of mosques have been told to take all actions to stop Muslims chanting “takbira (i.e saying “Allahu Akbar!”) and marching for protests after Friday prayer. On the other hand, more than 300 people have been reportedly arrested in Assasa and other towns of Arsi Province over the week.

On May 4 beginning early in the morning, thousands of police  and civil security forces were deployed in Addis Ababa and other towns to scare off the people. But at midday, all of the preventive methods applied by the government were proved to be ineffective. And immediately after the completion of Friday prayer, hundreds of thousands of Muslims in Addis Ababa and other towns filled the sky with defeafening chants of: “Stop Ahbashism campaign! The people want to step down Majlis! Allahu Akbar!!” 

Sheikh Mohammed Adem, a Muslim religious scholar living in Addis Ababa says, “The people are asking their basic right. We are asking for freedom of worship. We tolerated many repressive measures for more than 17 years. But this time, we say ‘enough’ to oppression. We won’t turn back until we attain our goal”.The protest at the Anwar Mosque (the grand mosque of Addis Ababa) and over the nearby streets was so intense that Mercato - one of the largest open air markets in Africa - came to a standstill for hours. 

Witnesses say there have been similar protests in Dessie, Jimma, Assela, Agaro, DireDawa, Alaba, Assasa, Warabe, Jijiga, Robe and Shashemene. The current tension between government and Muslim Ethiopians started in July 2011 when the government-backed “Majlis” launched a campaign to indoctrinate Muslims in the ideology of a newly arriving controversial sect called “Ahbash”. 

But Muslims came to direct protest at the beginning of this year when the leaders of “Majlis” sacked 50 teachers of Aweliya Islamic institute and tried to substitute them with “Ahbash” scholars. The government supported the action taken by “Majlis” and said “Aweliya had been a training center of terror ideology. ‘Wahhabis’ were arming the youth with fundamentals of extremism. So the Majlis has taken the appropriate measure”.
In spite of its open support for “Majlis”, the government continues to deny any interference in religious affairs. Through state owned media, it says “We are training Muslim scholars on the constitution and legal framework of the country. Apart from this, the government hasn’t interfered in spiritual affairs of the Muslims”.
Free viewers say “The government is highly terrorized by a continuing wave of protests. This week’s intensive media coverage about the Assasa massacre and the Muslim uprising are indications of government’s fear. In some occasions, some government authorities were expressing their worry about the ongoing condition”. These viewers point to what happened recently on a meeting conducted at Addis Ababa city hall where only selective pro-government imams and “Majlis” leaders have participated. 

On that meeting, sources say, the head of Addis Ababa Bureau of Justice and Security spoke to the attendants “The mass has turned against us. We couldn’t control the people. You have taken a mission to convince the people. But you did nothing. What were you doing until now? Our government is highly troubled by the Friday protests.” He also ordered the imams to stop any protests in and around mosques. Muslim scholars say “The authorities are disturbing themselves. We are asking for freedom of worship. 

We are asking them to stop imposing the ideology of ‘Ahbash’ on our people. We are asking them to apply what they have written on the constitution of the country. We didn’t ask them to share us political power.” They also say that the current media campaign can’t silence the people and add “Our faith is the only hope we have. It is the only rope that ties us to our God. They are going to cut out this rope. But that will never happen as long as we are alive”.

The two Arabs 

On Friday night, The Ethiopian Television reported that two Arabs who came from the Middle East to incite violence in the main mosques was caught red handed and immediately expelled from the country. The government said that the two people were found while they make inflammatory statements and distribute materials calling for “jihad”. The two Arab came to Addis Ababa on Friday morning, says the government. Their name and nationality was not disclosed even though they were shown on TV screen.

The Muslims who attended the Friday prayer at Anwar mosque say “The government’s statement is completely false. It is fabricated to defame our peaceful struggle. No one has distributed inflammatory material at Anwar Mosque. If they caught two Arab “Jihadists”, why didn’t they disclose their name and nationality? How do people caught on such illegal activity expelled without being investigated and tried?”

One scholar rejects government’s statement and asks “How can a person that came to Ethiopia on Friday morning directly goes to Anwar mosque and distribute “Jihadi” papers in the midday? Why did the Ethiopian government authorities contented only in expelling them to their country? Why didn’t they bring the two Arabs to the court? They have to answer these questions”. To paraphrase his statement, this scholar mentions what happened to two Swedish journalists when they were caught in the remote region of Ogaden together with some fighters of Ogaden National Liberation Front.

After the “Assasa Killing”

After the deadly incident happened at Assasa, in the last week, many top leaders of the ruling party were undertaking a “silencing meeting” all over the country. In one of such meetings undertaken at Assasa town on Wednesday, Mr. Abdul-Aziz Ahmed, the Vice President of Oromiya regional state was heard in public media saying “In the name of asking for freedom of worship, some politically motivated groups have planned to overthrow the government. They have caused the death of civilians in this town. They have plotted similar deadly riots in all of the country. They government won’t allow them to continue in this way. We will stop them in all possible ways”. 

Sheikh Aman Nure, an elderly scholar living in Adama town (originally from Assela town, Arsi province) rejects the official’s accusation and says “Last week, they said they have arrested a man calling for ‘Jihad’ and they killed his ‘Jihadi’ supporters. Now they say ‘political groups have plotted the massacre’. This has been their behavior for two decades. They can’t repeat what they speak today. Our country is governed by such liars who don’t care about the tradition and ethics of our people”. 

The Assasa massacre was highly condemned by many religious scholars of the country. Ethiopian Diaspora communities of Europe, North America and the Middle East have sent strong statements to the government asking to investigate the actual cause of the massacre through an independent commission. Rebel political groups like Ogaden National Liberation Front and the Oromo Liberation Front have condemned the massacre and released statements in support of the peaceful struggle of Ethiopian Muslim Society.