Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Thursday, May 3, 2012

ብአዴን አማርኛ ተናጋሪ የሕወሓት ክንፍ ወይስ የአማራው ወኪል?

 አንዳርጌ መስፍን ሽፈራው
እንደሚታወቀው ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ የአማራ ህዝብ ላይ እጅግ ዘግናኝና አሣፋሪ የሆኑ የጅምላ ግድያዎች ተካሂደውበታል፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ አማራዎች እጆቻቸውና እግሮቻቸው የፊጥኝ እየታሰሩ እስከነ ሕይወታቸው በገደል ተጥለዋል፡፡ አሶሳ ላይ ስብሰባ ተብለው ተጠርተው ባንድ መጋዘን ውስጥ ከታጎሩ በኋላ በውጭ ተዘግቶባቸው በእሳት ተቃጥለዋል፡፡ በዚህ ሥልጡን ዘመን እንዲህ ዓይነት ዘግናኝ ግድያ በንፁሐን ዜጎች ላይ ይፈፀማል ተብሎ አይታሰብም፡፡ 

የአሰቦት ገዳም ደካማ መነኮሳት ሳይቀሩ ተገድለዋል፡፡ ጥቅምት 5 ቀን 1999 ዓ.ም የአቦ በአልን ለማክበር ከጅማ ከተማ 60 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ባሻሽ አቦ በተባለ አካባቢ በአሮጊቶችና በሴቶች ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ(እርድ) ኃይማኖትን ሽፋን ያደረገ ቢመስልም የሥርዓቱን አስከፊነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሣይ ነው፡፡ ካለፈው የካቲት ወር መገባደጃ ጀምሮ ከቤንች ማጂ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ በሺዎች የሚቆጠሩ አማራዎች ተባረው ርቃናቸውን አዲስ አበባ ሲገቡ አይተን አንጀታችን በሐዘን ተላውሷል፡፡ መጠጊያ አጥተው ላይ ታች ሲንከራተቱ ማየት ደግሞ ሌላው አሣዛኝ ገፅታ ነው፡፡ 

ከዚህ ሁሉ የከፋው ቤተክርስቲያን እንኳን ‹‹ከሞቀው ዘፋኝ›› ሆና ወይም በጎሳ አስተሳሰብ ታጥራ አላስጠጋም ማለቷ የእምነቱን አባቶች ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ተግባር ሆኖ አልፏል፡፡ ይህንን በተመለከተ አንድ አዛውንት፡- “ድሮ ድሮ ቤተክርስቲያን እንኳንስ መጠጊያላጡ ዜጎች ይቅርና ወንጀል የፈፀሙ ወንጀለኞች ቤተክርስቲያን ገብተው ደውል በመደወል መንግሥት ምህረት እንዲያደርግላቸው ሲጠይቁ የሃይማኖት አባቶችም ያማልዱ ነበር፡፡ የዛሬዎቹ አባቶች ግን ደጀሰላምን ለመጠለያነትም እንኳ ከለከሉ” በማለት ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡ 

አዛውንቱ እንዳሉት እነዚህ የዘመኑ የሃይማኖት አባቶች ዜጎችን በጭንቅ ጊዜ ቤተክርስቲያን እንዳይጠለሉ ሲከለክሉ ይህ የመጀመሪያ ጊዜያቸው አይደለም፡፡ በ1993 ዓ.ም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመብት ጥያቄ ባነሱበት ወቅት የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ከግቢ አስወጥተው ሲያሳድዷቸው ቅድስት ማርያም ወርደው አባቶች ካሣዳጆቻቸው እንዲታደጓቸው ሲማፀኗቸው አሳልፈው መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡ ከጉራፈርዳ የተሰደዱት ዜጎች እንዳረጋገጡት ድብደባና እንግልት ደርሶባቸዋል፡፡ ለምሳሌ አንድ ወጣት እየተደበደበ መኪና ላይ ቢጫንም በደረሰበት ድብደባ ተበሳጭቶ ከመኪናው ላይ ተወርውሮ ራሱን ፈጥፍጦ ገሏል፡፡

ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ፍትሕ ከመጥፋቱ የተነሳ ራሳቸውን በገመድ እያነቁ የሚገሉና ከላያቸው ላይ ቤንዚን እያርከፈከፉ ክብሪት እየጫሩ ተቃጥለው የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየተበራከተ መጥቷል፡፡ መምህር የኔሰው ገብሬ እስከ ጠ/ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ድረስ አቤት ቢልም ሰሚ በማጣቱ ተበሳጭቶ ራሱንአቃጥሎ ሰማዕት ሆኗል፡፡ ካድሬዎችና ባለሥልጣናት ግን “አእምሮው ንክ ነበር” ሲሉ በከፈለው ዋጋ ተሳልቀውበታል፡፡ ጎንደርም አንድ መምህር እንዲሁ ፍትሕ አጥቶ ራሱን በገመድ ሰቅሎ ሲሞት “አእምሮ በሽተኛ ነበር” አሉት፡፡ ይህንን በተመለከተ አንዳንድ የስርአቱ ተቺዎች “ኢሕአዴግ አንድ ጊዜ ብቻ አይገልም፡፡ ከገደለ በኋላም የሟቾችን ታሪክ ጥላሸት ይቀባል” በማለት ይነቅፋሉ፡፡

አቶ ሽፈራው ሽጉጤም ዜጎችን ማፈናቀላቸው ሳያንስ ሚያዝያ 2 ቀን 2004 ዓ.ም በቴሌቪዥን ቀርበው፡- “አንድም አማራ አልተባረረም፡፡ 33 የሚሆኑ ብቻ ደን ስላቃጠሉ ተባረዋል” በማለት የሰጡት ማስተባበያ ራሱ ሕሊናን የሚያቆስል ነው፡፡ ይህንን ፕሮግራም የተከታተሉ አንድ የደቡብ ኢትዮጵያ ተወላጅ ግርምታቸውን እንዲህ ሲሉ ገልፀዋል ፡- “እነዚህን አማራዎች ለማባረር ሲባል ደኑ ላይ እሳት ለቀቁና እነሱ እንዳቃጠሉት ተቆጥሮ ለቴሌቪዥን እይታ አበቁት፡፡ ምነው እንግዲያው የእነሱ ቤት ሲቃጠል አላሳዩን? እሺ ይሁን እነሱ አቃጠሉት እንበል፤መቸም እነዚህ ዜጎች ሆነ ብለው ለጥፋት አያቃጥሉትም፡፡ በቆሎ ወይንም ማሽላ ለመዝራት ነው፡፡

 ታዲያ ለልማት ከሆነ ወንጀሉ ምኑ ላይ ነው?” በማለት ይጠይቁና “የደኑ መቃጠል ያየር መዛባትን የሚያስከትል ከሆነ የሕንድ፣የቻይናና የቱርክ ቱጃሮች የምዕራብ ኢትዮጵያን ደን በዘመናዊ ቡልዶዘር እየመነገሉ ምድረበዳ ሲያደርጉት ለምን ዝም ተባሉ? ታሪክ ይፍረደው!” ሲሉ በምሬት ተናግረዋል፡፡ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ “አንድም አማራ አልተባረረም” ይበሉ እንጂ አማራን ከደቡብ ክልል ጠራርጎ ለማስወጣት በወጣው እቅድ መሠረት እስከ 2006 ዓ.ም ድረስ 78 ሺ አማራዎች እንደሚባረሩ መረጃ አለ የሚሉ ወገኖችም አሉ፡፡

ሌላው አሳፋሪ ጉዳይ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በጻፉት ደብዳቤ ላይ አባሪ ተደርጎ የተገኘዉ  ወረቀት “ወደ ሀገራችሁ ሂዱ” የሚል ሀይለ ቃል መገኘቱ ነው፡፡ ለመሆኑ ሰውየው እንዲህ ሲሉ ምን ማለታቸው ነው? መቼም ቢሆን አቶ ሽፈራውን የሚያህል ሰው የሀገርን ትርጉም አያውቅም ለማለት ይከብዳል፡፡ እሳቸውን ጨምሮ በኢህአዴግ ቋንቋ ሁላችንም ያለችን የብሔር ብሔረሰቦች አገር የሆነችው አንዲት ኢትዮጵያ ነች፡፡ ርግጥ ነው እያንዳንዱ ብሔር ብሔረሰብ፣የተወለደበት ቀዬ ወይንም እትብቱ የተቀበረበት የትውልድ ሥፍራ አለው፡፡ ችግሩ ግን አማራ በዚህ 20 ዓመት ውስጥ የሀገርም፣የክልልም፣የቀየም ባለቤት አለመሆኑ ነው፡፡ 

ስማቸውን እንዳልጠቅስ ያስጠነቁቁኝ አንድ ጎንደሬ፡- “አማራ በኢህአዴግ ዘመን ከማርስ እንደመጣ
ፍጡር መብረጃና መቋጫ በሌለው ሁኔታ ላይ ታች እየተዋከበ ማረፊያ ዛፍ ያጣ አሞራ ሆኗል፡፡ ተከዜን የሚያህል ዓለም አቀፍ ወንዝ ወሰን ሆኖ እያለ ጊዜ አገኘን ብለው ሰቲት  መራን፣ወልቃይት ጠገዴንና ማይፀምሪን ወደ ትግራይ ከለሏቸው፡፡ አማራውን ግን ከቀየው እያፈለሱት ነው፡፡ ይህም ሆኖ እንደ ሀገር አብረን እስከኖርን ድረስ ችግር የለውም፡፡ ችግሩ የሚመጣው የትግራይ ሪፐብሊክ የመሠረቱ እለት ነው፡፡ ያኔ ሆዱን ሞልቶ ተኝቶ የሚያድር አማራ አይኖርም፡፡

ሌላው አማራንና የኢትዮጵያን ሕዝብ የናቁበት ሁኔታ ነው፡፡ ለባህሪ መግዣ (ማባበያ) የመተማን ለም መሬት ለሱዳኖች እንደ አንባሻ እየቆረሱ መስጠታቸው ነው፡፡ ይህንን ውል የፈፀሙት ሚንስቴር ደረጃ ደርሰዋል” በማለት በቁጭት ተናግረዋል፡፡ ለመሆኑ በአማራ ላይ የበቀሉ ሁኔታ መነሻ ምክንያቱ ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ አንዳንድ አማራዎች በግልጽ እንደሚናገሩት ከሆነ “ሕወሓት ገና ከመነሻው ጀምሮ ትግራይን ከኢትዮጵያ ገንጥሎ የትግራይን ሪፐብሊክ ለመመስረት ሲነሳ አማራን ቀንደኛ ጠላቱ አድርጎ ነው፡፡ ይህንንም በፋኖነት ዘመኑ ‘አማራ ገዳይ’ እያለ ተግብሮታል፡፡” ይላሉ፡፡ 

እኒሁ የአማራ ተቆርቋሪዎች “የሚገርመው ግን ዛሬም መንግሥት ሆኖ ከ21 ዓመት በኋላ እንኳን አማራን እየተከታተለ ከማሳደድ አለመቆጠቡ ነው፡፡ አማራ የጭንቅላት ካንሰር ሆኖበታል” ይላሉ፡፡
አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች በበኩላቸው “ሕወሓት ወደ ሥልጣን ከመምጣቱ በፊትም ሆነ ከመጣ በኋላ በፈፀማቸው ጥፋቶችና በሚፈፅማቸው ስህተቶች ሁሉ የታሪክ ተጠያቂና ተወቃሽ ላለመሆን በአማራ ላይ ጣቱን ከመቀሰር ተቆጥቦ አያውቅም፡፡ ማባሪያ በሌለው የፕሮፖጋንዳ ዘመቻና የማፈናቀል ተግባር ተጠምዷል” ይላሉ፡፡ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ የማይፈልጉ ግለሰብ ደግሞ “ሕወሓት በሽብር ተፀንሶ በሽብር ተወልዶ፣የባሩድ ጪስ እያሻተተ ያደገ ፋኖ ድርጅት በመሆኑ በአእምሮው ውስጥ ሠላም አልተቀረፀበትም፡፡

 የተጠናወተው ጀብደኝነትና ማንአህሎኝነት ነው፡፡ በመሆኑም በማኅበረሰቡ ውስጥ የተረጋጋ ሠላም የለም፡፡ ሕወሓት የፋብሪካ ጭስ ከማየት ይልቅ የባሩድ ጭስ ማሽተትን ይናፍቀዋል፡፡ በዚህ 21 ዓመታት ውስጥ ሕዝቡ የሰቀቀን ኑሮ ነው የሚኖረው፡፡ ከሥራ መባረር፣ከመኖሪያ ቀዬ መፈናቀል በየእለቱ የምናያቸው ክስተቶች ናቸው፡፡ ሕወሓት/ኢህአዴግ ሥልጣን ላይ እስከ ቆየ ድረስም እነዚህ ሁኔታዎች ይቀጥላሉ” በማለት ቁጭታቸውን ይገልፃሉ፡፡ ሌላው አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው፡- “ሕወሓት ኢትዮጵያን የባሕር በር ማሳጣቱንና ኤርትራን ተዋግቶ ማስገንጠሉን ሕጋዊና ፍትሐዊ ለማድረግ አንቀጽ 39ኝን በሕገ መንግሥት ቢቀርጽም የኢትዮጵያን ሕዝብ ይሁንታ ግን ማግኘት አልቻለም፡፡ 

በዚህ ምክንያትም አምባገንን ሆኗል፡፡ ሥልጣን አያያዙ በሕገወጥና በትጥቅ ትግል ነው፡፡ በኃይልና በመፈንቅለ መንግሥት የተያዘ ሥልጣን ደግሞ ሕጋዊነት ስለሌለው የተረጋጋ ሠላም የለውም፡፡ ሕወሓት/ኢህአዴግም ወይ የንጉሣውያን ደም አለኝ ብሎ ዙፋኑን አልወረሰ ወይ ዴሞክራት ነኝ ብሎ በመድበለ ፓርቲ ሥርዓት በምርጫ አሸንፎ ሥልጣን አልያዘ ወይ ለይቶለት ኮሚንስት ነኝ ብሎ የአንድ አምባገነን ፓርቲ ሥርዓት አልመሠረተ፤ እስከ መቼ እያምታታና ኮርጆ እየገለበጠ ይኖራል?” በማለት በትዝብት ይጠይቃሉ፡፡ እውነትም ኢህአዴግ እያምታታና እያተራመሰ የሚገዛበት ጊዜ ያበቃለት ይመስላል፡፡

 ሕጋዊነትን ለመላበስ ግን ሁለት ምርጫዎች ይኖሩታል፡፡አንደኛው የጭፍን የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ እየነዛ አገሪቱን ቀውስ ውስጥ ከቶ መሞት፡፡ ሁለተኛው ነፃ ምርጫ አካሂዶ ካሸነፈ ሕጋዊ መንግሥት መሥርቶ በሥርዓት ማስተዳደር፤ ከተሸነፈም በሥርዓት ለአሸናፊው አካል አስረክቦ የታሪክ ባለቤት መሆን ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ግን የሚፈጠረው አንዳንዶች “ሕወሓት ውሉ የጠፋበት ገና ከውጥኑ ‘የትግራይ ነፃ አውጭ ነኝ’ ብሎ በረሃ የገባ ጊዜ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ከድቷታል፡፡ እንዴት ብሎ ነው የካዳትን ሀገር ሕጋዊ ሆኖ የሚገዛት? ዛሬ እንኳን ከዚህ አዙሪት ውስጥ አለመውጣቱ እንዳሸመቀ መሆኑ ይታወቅበታል” እንደሚሉት ነው፡፡

ሰሞኑን ከጉራፋርዳ የተባረሩትን አማራዎች በተመለከተ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች አፅንኦት ሰጥተው እንደሚናገሩት ከሆነ “ኢሕአዴግ በዘር ማፅዳት ወንጀል (ethnic cleansing) በዓለም አቀፍ ፍ/ቤት መከሰስ አለበት” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ የመኢአድ ፕሬዚዴንት ኢንጅነር ኃይሉ ሻወል ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ 2ኛ ዓመት ቁጥር 38 እትም በሰጡት ቃለምልልስ “ከደቡብ ክልል ስለተፈናቀሉት ሰዎች የሚሉት ይኖራል?” ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፡- ጉዳዩ የዘር ማጥፋት ዓላማ ያለው ነው፡፡በመሆኑም ከዓለም ዓቀፍ የሕግ ባለ ሙያዎች ጋር እየመከርንበት ነው” ብለዋል፡፡ 

አንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በበኩሉ፡- “በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው የማፈናቀል በደልን በማስመሰል ፕሮፓጋንዳ መደበቅ አይቻልም” በሚል ርእስ በሰጠው መግለጫ “የኢሕአዴግ የከፋፍለህ ግዛው የጎሳ ፖለቲካ ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት 1983 ዓ.ም ጀምሮ በሀገራችን ተደጋጋሚ የሆኑ በደሎች ተፈጽመዋል፤ በበደኖ፣ በአርባጉጉ፣ በጉጂ፣ በወለጋ፣ በጋምቤላ፣ በሲዳማ፣ በተለይ በጌዲኦና በጉጂ ዞን የተፈፀሙ ግጭቶች የቅርብ ጊዜ አስከፊ ትዝታዎቻችን ናቸው” ይልና መግለጫው በመቀጠል “የደቡብ ክልል አስተዳደር በወሰደው ዜጎችን በኃይል የማፈናቀል ተግባር የሰው ሕይወት ጠፍቷል፣ ዜጎች በጦር ተወግተዋል፣ ለዓመታት የደከሙበትን ንብረት አጥተዋል. .. በዜጎች መፈናቀልና መሰቃየት ምክንያት የሆኑና መመሪያዎችን የሰጡ ባለሥልጣናት በሕግ መጠየቅ አለባቸው . . .” ብሏል፡፡ 

በመጨረሻም “ለመሆኑ ‹ለአማራ ሕዝብ መብትና ጥቅም የቆምኩ ነኝ› የሚለው ብአዴንስ ምን ይላል?” በማለት አንድነት ጠይቋል፡፡ አንድነት እንዳለው ለመሆኑ “የአማራው ሕዝብ ወኪል ነኝ” የሚለው ብአዴን ምን እየሠራ ነው? ብአዴንስ ማነው? የብዙዎች ጥያቄ ነው፡፡ ብአዴን ማነው? አልታደልንም እንጂ ሕዝብ የመሪዎቹን ማንነትና ምንነት የማወቅ መብት ነበረው፡፡ የኛ መሪዎች ግን እንኳንስ ማንነታቸውን ለሕዝብ ሊያስተዋውቁ ይቅርና ስማቸውን ሳይቀር ቀይረው ያሸመቁ ናቸው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም የመጡበትን የዘር ግንድ ሳይቀር የደበቁና የቀየሩ ናቸው፡፡ ለማንኛውም የብአዴን ቁንጮ መሪዎች የሚከተሉት ናቸው፡-

1. አዲሱ ለገሠ (ኦቦ) የአሰበ ተፈሪ ልጅ ወይንም ተወላጅ
2. በረከት ስምዖን (መብራቱ) ጎንደር ተወልዶ ያደገ በእናቱም በአባቱም ኤርትራዊ
3. ተፈራ ዋልዋ የሀገር ማርያም ልጅ ወይንም ተወላጅ በአባቱ አማራ በናቱ ሲዳማ 
4. ታደሰ ካሣ (ጥንቅሹ) ኮረም ተወልዶ ያደገ በግማሽ ትግሬ በግማሽ አገው 
5. ካሳ ተክለ ብርሃን (ሸሪፎ) ሠቆጣ ተወልዶ ያደገ ትግሬና አገው
6. ሕላዊ ዮሴፍ (ቦግን) የአ.አ ልጅ ትግሬ ምናልባትም የኤርትራ ዘር ያለበት
7. ዮሴፍ ረታ (ገይድ ወይንም ዶሪ) የናዝሬት ልጅ ቤተሰቦቹ አርሲ
8. ተሠማ ገ/ሕይወት (የጎንደር ልጅ) ሙሉ በሙሉ ትግሬ (አድዋ)
9. ከበደ ጫኔ (ጣሣ) የራያ (ዋጃ) ልጅ ትግሬና አማራ
10. መለሠ ጥላሁን አርሲ ተወልዶ ያደገ ኦሮሞ
11. ኃይሌ ጥላሁን (ዘሪሁን) ሰሜን ሸዋ

እነዚህ ናቸው የብሔር አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) መሪዎች የነበሩት፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ዜጎች ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ እንደ ኢትዮጵያዉያንነታቸው የአማራን ሕዝብ የመምራትም ሆነ የማስተዳደር መብት አላቸው፡፡ ጥያቄው የሚነሳው ‹‹ሁልህም ወደ ወገንህ ሲባል አክንባሎም ወደ በረት፤ርኮት ወደ ቁርበት ተጠጉ›› እንደሚባለው ሁልህም በየክልልህ በገዛ ብሔረሰብህ ተዳደር ከተባለ መብቱን ለብሔሩ ተወላጅ መተው ነበረበት ነው ነቀፋው፡፡ ‹‹በቅሎ አባትሽ ማነው ቢሏት ፈረስ አጎቴ ነው አለች›› እንደሚባለው በአንድ ወቅት አቶ ታምራት ላይኔ (ጌታቸው ማሞ) ‹‹በእናቴ ወሎዬ በአባቴ ጎንደሬነኝ›› ብለው ነበር፡፡

 ኡጋዴን ወርደው ግን ‹‹ሽርጣም ይሏችሁ የነበሩትን ነፍጠኛ አማራዎችን አሳዩዋቸው. ..›› በማለት ንፁሀን ዜጎችን አስጨፍጭፈዋል ፡፡ ሌላው የብአዴን ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ተፈራ ዋለዋ በአንድ ወቅት ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ወደ ዩኒቨርሲቲ ስለሚገቡ ተማሪዎች የኮታ አደላደል ጉዳይ ለሕዝቡ ለማስረዳት፣ እግረ መንገዳቸውንም ፖለቲካቸውን ‹‹ለመስራት›› ሰብስበው ‹‹ከክልሉ ብሔረሰቦች ተወላጅ ልጆች 2 ነጥብ ባልሞላ መግባት ይችላሉ. ..›› በማለት ሲናገሩ ‹‹እዚህ ተወልደው ያደጉት የአማራ ልጆችስ?›› ተብለው በሕዝቡ ሲጠየቁ ‹‹አማራውማ ድሮ ተምሯል›› በማለት የፌዝ መልስ ነበር የሰጡት፡ ፡ በተጨማሪም ‹‹ብአዴኖች›› የጎንደር መሬት ተቆርሶ ወደ ትግራይ ሲከለልም ትንፍሽ አላሉም፡፡ ለነገሩ ሊሉም አይችሉም፣ አማርኛ ተናጋሪ የሕወሓት ክንፍ ናቸውና፡፡

አንዳንድ የዋሀን “ብአዴን ምን እየሰራ ነው?” ብለው ለጠየቁት ጥያቄ ከበቂ በላይ መልስ የሚሆን ይመስለኛል፡፡ እውነት እንነጋገር ከተባለም ብአዴን አማርኛ ተናጋሪ የሕወሓት ክንፍ እንጂ አማራን አይወክልም፡፡ በ1983 ዓ.ም የሽግግር መንግሥቱ ጊዮን ሆቴል ላይ ሲመሠረት የሀገሪቱ ዜጎች ወኪሎቻቸውን ሲልኩ አማራ ወኪል አልነበረውም፡፡ እንዲልክም እድሉ አልተሰጠውም፡፡ በወቅቱ አቶ መለስ ዜናዊ “አማራ ወኪል የለውም፤ወደ ፊት ግን ተደራጅቶ እንደሚልክ ተስፋ አለን” ማለታቸው አይዘነጋም፡፡

በዚህ መሠረት በ1984 ዓ.ም መጋቢት ወር ላይ የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መአሕድ) ሲመሰረት እንደተለመደው ነበር ሕወሓት በቆረጣ የገባው፡፡ አዲስ ድርጅት እስከ ሚመሰርት ድረስ አላቆይ ብሎት ወደ አማራ ክልል እንደ መሸጋገሪያ ድልድይ የተጠቀመበት ሕብረ-ብሔራዊውን ድርጅት ሕዴንን አፍርሶ “ብአዴን” ብሎ በመሰየም ባሕርዳር ላይ አምባሻ ቆርሶ፣ፈንድሻ ረጭቶ “ከዛሬ ጀምሮ የአማራ ሕዝብ ወኪል ነህ” ብሎ መርቆ ለቀቀው፡፡ እንግዲህ ባጭሩ ብአዴን ማለት ይሄ ነው፡፡

Source: ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ ሚያዚያ 16 ቀን 2004 ዓ.ም

Wednesday, May 2, 2012

የሰሜን ጐንደር ሕዝብ የቁም እስረኛ ሆኗል

By Finnote Netsanet News paper
ኢህአዴግ በአማራ ብሔር ላይ ጣቱን ቀስሯል” ሲሉ አንዳንድ የሰሜን ጐንደር አርሶአደሮች ለዝግጅት ክፍላችን ገለፁ፡፡ የዜና ምንጮቻችን እንደሚሉት “ኢህአዴግ የአማራውን ህዝብ ከመኖሪያውና ከሥፍራው ለማፈናቀልና የሃይማኖት ብጥብጥ ለማስነሳት እቅድ ይዞ እየሰራ ነው፡፡
ደቡብ የሚገኙ አማሮችን በመመሪያ እያፈናቀለ ይገኛል፡፡ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ያለውን ቀጥሎአል፡፡ ተፈናቅለው የሚመለሱትም እንዲቋቋሙ ምንም ዓይነት ድጋፍ አይደረግም” ብለዋል፡፡ እነዚህ ጉዳዩን በቅርብ እየተከታተልን ነው የሚሉት አርሶ አደሮች እንደሚሉት ሰሞኑን ደግሞ በሰሜን ጐንደር ሱዳን ድንበር አካባቢ በምትገኝ ምዕራብ አርማጭሆ / ኢብርሃጂራ/ በምትባል ወረዳ በእርሻ ሥራ ተሰማርተው የሚኖሩ አርሶአደሮች የእርሻ መሬታቸውን ተነጥቀው ተባረዋል፡፡ 

ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በአካባቢው በእርሻ ሥራ ላይ ያሉትን አርሶ አደሮች መሬቱ “በብሎክ”  ስለሚደለደል ያለሰለስኩቱ ማሣዬ ነው፤ ለኔ ይገባኛል የሚል ጥያቄ እንዳያነሱ ማስጠንቀቂያም ተሰጥቷቸዋል፡፡ አንዳንድ ታዛቢዎች “የኢትዮጵያን መሬት ቆርሶ ለሱዳን በመሰጠት በሥፍራው ያሉትን አርሶአደሮች አፈናቅሏል” ይላሉ፡፡ የዜና ምንጮቻችን እንደሚሉት “ታች አርማጭሆወረዳ /ሣንጀ/ ለረጂም ዓመታት ኪዳነምህረት ቅዱስ ሚካኤል ጽላት ማደሪያ ሥፍራ ለልማት በሚል ስልታዊ አባባል ለአንድ ባለሀብት መወሰኑ በአካባቢው ህብረተሰብ ላይ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሮአል፡፡ 

ውሳኔው የአካባቢው ህብረተሰብ ባለመቀበሉ የወረዳው ኃላፊዎች ህብረተሰቡን ሰብስበው ለማግባባት ቢሞክሩም ህዝቡ አንቀበልም በማለቱ በአካባቢው ውጥረት ነግሷል፡፡ በምርጫ 97 ኢህአዴግ ምንም አይነት ድምጽ ያጣበት አካባቢ በመሆኑ የአካባቢውን ህብረተሰብ እንደጠላት እያየ ከፍተኛ የሆነ አስተዳደራዊ በደል ሲፈጽምበት የቆየ አካባቢ ነው፡፡” ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ምንጮች እንደሚሉት “በአሁኑ ጊዜ የአካባቢውን ህብረተሰብ ነፃነቱ ሙሉ በሙሉ ተገፏል፡ ፡ ሁሉም ዜጋ የቁም እስረኛ ተደርጓል፡፡ ከሚኖርበት ቀበሌ ወደየትኛውም ቀበሌ ለመሄድ ቢፈልግ ለአካባቢው ኃላፊዎች አሳውቆ የይለፍ ወረቀት መያዝ ይጠበቅበታል፡፡ የፍቃድ ወረቀት ሳይኖረው ከሚኖርበት ቀበሌ ተነስቶ ወደ ሌላ ቀበሌ ቢሄድ ይታሰራል” ብለዋል፡፡

Gambella rebels repulse government army attack, says GDM

 Ethiomedia | May 2, 2012
GAMBELLA, Southwestern Ethiopia - Ethiopian rebels in Gambella repulsed an attack by government soldiers who gave up the fight after about half an hour, rebel sources said on May 1st. Government soldiers launched the attack on a travelling contingent of Ngeli O. Opiew, commander-in-chief of the Gambella Democratic Movement (GDM). The heavy fighting lasted about half an honor when the soldiers fled the area, leaving their dead behind, GDM said, whose full statement follows here:

GDM fighters repulse government army attack

Gambella - On April 29, 2012, in Akobo District of Gambella, Meles Zenawi’s soldiers attacked the Military Wing of Gambellan Democratic Movement (GDM) force. The attack was repulsed by the Commander-in-Chief of GDM, Ngeli O. Opiew, and his small contingent troops who were traveling with him. Within 30 minutes of heavy engagement, the attackers ran away leaving their dead behind.

 GDM wants to announce that unless the terms of land grab in Gambella region are reversed in favor of Gambella people, there won’t be peace in the region. GDM will fight to stop the sale of Anyuaks’ land to foreigners and for the return of displaced Anyuaks to their ancestral lands from concentration camps. GDM will not sit by ideally and allow the likes of Karuturi Global, Saudi star, and others exploit Gambellan people.
In 1991, the EPRDF regime promised Ethiopia’s ethnic groups that they could exercise their rights to self-determination in new Ethiopia. Ethiopia was divided into nine ethnically based federal states. But the EPRDF regime changed its mind overnight. It created ethnically based surrogate parties through which it could project the illusion of a multi-ethnic federal state. Those parties who wanted to assert their states’ right to “self-determination up to and including secession” were forced out. And through it puppets and surrogate parties, EPRDF managed to preserve its dominance in the political arena. 

On December 13, 2003, Meles Zenawi’s regime and its puppets in Gambella killed 426 Anyuak men in front of their wives and children in broad daylight. More than 10,000 left their ancestral land and became refugees in countries such as Sudan, Kenya, Uganda, South Africa, England, Norway, Holland, Australia, Canada, and the United states. Since 2003 massacre, according to 2012 human right report, more than 5000 anyuaks were either killed or imprisoned.

Again, in 2010, more than 70,000 Anyuaks were forcibly removed from their ancestral land and put to 18 concentration camps to make way for investors. Those who refused to leave were either killed or imprisoned. The government leased the land to investors for 99 years without compensations.GDM, therefore, was formed by sons and daughters of Gambella to fight for the right of indigenous people of Gambella.

Long live GDM!
GDM Central committee!




መንግስት ሶስት በአንድ አዘዘ! ጎንደር አለ ነገር… መርካቶ አለ ነገር… ጋምቤላ አለ ነገር!

 አቤ ቶኪቻው
ይህንን ጨዋታ ስፅፍ ፋሲል ደሞዜ የተባለ አቀንቃኝ “አለ ነገር…” እያለ የሚያንጎራጉረውን ሙዚቃ እየሰማሁ ነው! ልብ አድርጉልኝ ይህ ስጋት ነው እንጂ ቅስቀሳ አይደለም! ምክር ነው እንጂ ቁጣም አይደለም! አክብራቹሁ ብሎጋችንን የምትዘጉ ሰዎች ምክራችንንም ስሙ…! አስቲ ሰሞኑን የሰማኋቸውን አጫጭር ዜናዎች ልንገራችሁ።
አንድ
በአርሲ ዞን አሳሳ ከተማ “መንግስት በሀይማኖታችን ጣልቃ አይግባብን” ያሉ ሙስሊሞች ከመንግስት ታጣቂ ሃይሎች በተከፈተባቸው ተኩስ አምስት ሰዎች ተገደለው በርካቶች ቆስለዋል። መንግስትም “አስር ፖሊሶቼ ተጎድተውብኛል ብሏል።” ይህ እንግዲህ የመርካቶው አንዋር መስጊድ እንቅስቃሴ አካል ነው። ይህንን መንግስት በሰላም እንዲፈታ ሁላችንም መክረናል ለምነናል ሰሚ ግን አላገኘንም እናም፤ መርካቶ አለ ነገር አትሉልኝም!
ሁለት
ጋምቤላ ከመሬታቸው የተፈናቀሉ የህብረተሰቡ አካላት በሼኩ እና በፓኪስታኖቹ የሩዝ አምራቾች ላይ እያሰሙ ያሉት ተቃውሞ ከእለት እለት እየተባባሰ፤ ወደ ተቀናጀ ጥቃት ተለውጦ አሁን በቅርቡ በሩዝ እርሻው ላይ ሲሰሩ የነበሩ የውጪ ዜጎች እና ኢትዮጵያውያን ላይ እስከ ሞት የደረሰ ጉዳት አድርሰውባቸዋል። ይህንንም አቤት እያሉ ሲጮሁ የነበሩ ብዙ ናቸው ግን ማን ይስማ…? በዚህም የተነሳ ጋምቤላ አለ ነገር! ያስብላል።
ሶስት
የዋልድባ ገዳምን ህልውና በሚፈታተን መልኩ የስኳር ምርት ሊያመርት መንግስት ደፋ ቀና እያለ ነው። የገዳሙ ሰዎችም “ተዉ ስለ እግዚአብሄር ብላችሁ አትንኩን” ብለው ቢለምኑ ቢማፀኑ የሚሰማ አላገኙም። መንግስት ነብሴ በቴሌቪዥኑ “ዋልድባ ሳይነኩት ጮኸ” አይነት ይዘት ያለው ዘገባ አሰራ! ቄሱም ዲያቆኑም መከረ ዘከረ “መንግስት ሆይ እባክህን ነገርህን በልኩ አድርገው!” አሉ።

 ነገር ግን አልሰማም። ልክ በአሁኑ ሰዓት የጎንደር ህዝብ ነብስ ወከፍ መሳሪያውን ይዞ በአስፈሪ ሁኔታ ወደ ዋልድባ ገዳም እየተመመ እንደሆነ ሰማን… ጎንደር አለ ነገር ማለት ይሄኔ ነው! “ሶስት በአንድ” ይሄ እነ “ማዘር ቤት” የመሳሰሉ ምግብ ቤቶች ገብተን ምግብ የምናዝበት ቋንቋ ነው።  ብዙ ግዜ እንደዚህ የምናዘው ለአራት ሆነን ነበር። አሁን ግን መንግስታችን ብቻውን ሆኖ ሶስት በአንድ አዟል። ደሞ ሌሎች ተከታዮችም አያጣም…!

ታድያልዎ ምን አስጨነቀኝ መሰልዎ… መንግስት ምን ያህል ቢርበው ነው ሶስት በአንድ  ያዘዘው? የሚለው ጥያቄ ያሳስበኛል። በአዲስ መስመር እንደተለመደው መንግስቴን እመክራለሁ… አረ ተዉ ግድ የላችሁም…! አንድ ግዜ ሰዉ ምን እያለ እንደሆነ ቆም ብላችሁ አዳምጡ! እየተጠየቁ ያሉት እጅግ በጣም ቀላል ቀላል ጥያቄዎች ናቸው። ነገር ግን እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ ከከበደን የምንከፍለው ዋጋ ይወደድብናል! እባካችሁ!!! ሶስት ለአንድ አያልቅም ትዕዛዝም ልክ አለው! ተዉ!

Tuesday, May 1, 2012

Ethiopian refugees in Sana'a seek 3rd country resettlement

 By Muaad Al-Maqtari, Yemen Times | May 1, 2012
Looking for a safe place to raise her demands, Seble Yohanes went to the Ministry of Human Rights in the Yemeni capital of Sana'a on Saturday.  Yohanes, along with other refugees from Ethiopia, decided to sleep on the pavement next to the Ministry.

During the daytime, this exposed place becomes a sit-in rally to demand protection of their rights from the United Nations Higher Commissioner for Refugees (UNHCR) and the Yemeni government. "The police forces arrested us in front of the Human Rights Ministry," Yohanes said, with fear evident in her pallid face at the thought of police, who have repeatedly raided illegal refugees in Yemen and arrested as many as they can.

Ethiopian refugees contacted Yohanes and her compatriots in an attempt to relay details of the inhuman conditions inside the police detention center, intensifying her fear of ending up like them. Yohanes handed her mobile over to a Yemen Times reporter while Hathem, Yohanes' friend speaking on the phone while being held in a crowded detention center in Sana'a, tried to paint a vivid picture of his brutal conditions and suffering, in the hopes that the whole world might know about those in the detention centers. 

More than 220 imprisoned Ethiopians are kept inside a single room. The prisoners are subjected to beating and only given one meal a day, according to Hathem. "Diseases are spreading due to the unhealthy environment and we are not allowed to receive medical treatment," added Hathem, who speaks limited Arabic.

The words of Hathem stoked Yohanes' and her friends' fear of having to face a similar fate. Unfortunately, their fears did not take long to materialize. On Saturday afternoon, police forces arrested Yohanes along with seven other Ethiopian refugees, including two women and a 5 year-old girl, Sara. They were taken from behind the Ministry of Human Rights, according to eyewitnesses.

While in a police patrol car, Yohanes managed to make a brief call to the Yemen Times. She spoke with difficulty, as it was clear she was crying."We were supposed to meet with Horia Mashhor, the Yemeni Minister of Human Rights, later today," she said. "After several days of continued attempts and great efforts to get to Mashhor, who was passing us for days going in and out of the Ministry, looking very busy, she agreed to meet us and set an appointment to discuss our situation."

She said that they had short conversations with Mashhor in front of the Ministry of Human Rights, and after talking to them for a few moments she was interrupted with several calls from governmental officials who told her to leave, not taking into consideration her conversation with the refugees.

Two days prior to her arrest, police managed to detain most of the refugees who had created a protest encampment in front of the United Nation High Commissioner for Refugees for eleven months, she noted. According to Yohanes, some refugees were held in a prison in Sana'a, while some others were moved to the camp for African refugees located in the Kharaz coastal area near the strait of Bab Al-Mandab, a key shipping lane through which more than three million barrels of oil pass daily.

Useless asylum ID  

There is nothing that can protect Yohanes and the other refugees from police pursuit and relentless raids except for asylum IDs issued by UNHCR. The first provision of the ID, however, states that the UNHCR's ability to interfere and protect the refugees is still limited.

The UNHCR office recognizes only the official refugees carrying IDs. But according to the UNHCR, holders of these IDs are not necessarily guaranteed any financial assistance nor the right to resettle in a third country. This draws the ire of African refugees, particularly Ethiopians.

The IDs terms are based on Articles no.17 and 22 of the 1951 United Nations convention relating to the status of refugees, which was ratified by Yemen. The convention only ensures refugees the right to work and public education. The ID has to be renewed every year. Some minority groups from the Ethiopian political opposition have managed to resettle in the United States and EU countries after staying in Yemen for a while.

Yohanes, like most of the African refugees who continue flowing into Yemen, do not want to settle down in Yemen. They consider it a transition point for their resettlement in rich countries like the Gulf states, the US, or EU countries. Imam Hussein Edrees, a 60-year-old Ethiopian refugee, was standing among refugees at the protest encampment in front of the Ministry of Human Rights, holding his old refugee documents in his hands.

On November 16, 1992, Edrees obtained his asylum in Yemen from the UNHCR, and had been renewing his ID every year, until 2006, when the UN agency began to refuse to continue renewing his asylum card. Although he has had five official appointments with UNHCR representatives in Yemen, Edrees said he has not been able to meet any officials of the UN Refugee Agency. 

Khadija Nassr Al-Din, another Ethiopian refugee, who has been in Yemen for more than fifteen years, said her husband Kaidani Mariam Asfa died in 2001 after a long struggle with intestinal cancer. However, neither the UNHCR nor the Yemeni government offered her or her husband any assistance. With her eyes full of tears, Kadija said, " my husband died while hugging our son."

While Kadija is Muslim, her husband was Christian. Their son, Ibrahim, was given a common name to both religions. They embodied a unique coexistence between people with different religious backgrounds.  Thousands of African refugees risk their lives when they cross the Red Sea on board small boats run by human traffickers. Smugglers dump them into the sea two kilometers from the Yemeni shore, forcing them to swim the rest of the way.

Yohanes said that in the boats belonging to traffickers, the refugees are mercilessly beaten if they attempt to move or raise heads or hands. In a separate event, last month the Interior Ministry found an armed gang in Haradh area, in the northern governorate of Hajjah located along the borders with Saudi Arabia. The gang was holding dozens of illegal African refugees prisoner, mostly Ethiopians.

In a statement, the ministry said more than 170 African refugee were kidnapped, including ten women, 50 children, and 19 old men. The refugees were subjected to beating and torture by the armed gang. "Due to beating that targeted the face and other sensitive areas, some refugees now suffer from sight and hearing problems," added the statement.

The ministry also revealed that in February, police forces had managed to arrest two members of the armed gang. The two members had been detaining 128 illegal refugees from whom they were trying to extort money. More than 65,000 Ethiopian immigrants arrived to Yemen in 2011, compared to 34,422 in 2010, according to the UNHCR. The UN refuge agency further pointed out that 37, 333 Ethiopians arrived in Yemen  illegally, revealing that 616 are either dead or still missing.

መንግስት ድምጻችን ይሰማ የሚሉ ወጣቶችን ማሰር ጀመረ

ኢሳት ዜና:-
ከወራት በፊት በአወልያ የተነሳው የእምነት ነጻነት ይከበር ጥያቄ እየተስፋፋ ሄዶ መላው አገሪቱን እያዳረሰ ባለበት ሰአት መንግስት በአንዳንድ አካባቢዎች የሀይል እርምጃ መውሰድ ጀምሮአል። በምእራብ አርሲ ዞን አሳሳ ወረዳ 4 የእስልምና እምነት ተከታዮች በፌደራል ፖሊስ አባላት ከተገደሉ በሁዋላ ፣ ጥያቄውን አነሱ ሙስሊሞችን ማዋከብና ማሰሩ ቀጥሎአል።

በአወልያ በተነሳው ተቃውሞ ወቅት የተመረጡ የሙስሊሙ አመራሮች፣ ከአቶ መለስ ዜናዊ ጋር ለመነጋገር ቀነ ቀጥሮ ጠይቀው እስካሁን ምንም መልስ ባለማግኘታቸው እያዘኑም ቢሆን በሰላማዊ ትግሉ ለመግፋት በወሰኑበት ወቅት፣ መንግስት ሆን ብሎ ተቃውሞውን በሀይል ለመጨፍለቅ እንቅስቃሴ መጀመሩ ፣ ሙስሊሙን ማህበረሰብ እያስቆጣ ነው።

በነገው እለት በአዲስ አበባ ለቡ ኢምራን መስጂድ ውስጥ እረብሻ አስነስተዋል የተባሉ በእስር ላይ የሚገኙ 10 ወጣቶች በፌደራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ላይ ይቀርባሉ። ወጣቶቹ የቀረበባቸው ክስ የእስልምና መንግስት እስኪቋቋም እንታገላለን በማለታቸው እና የመጅሊስ አባላትን “እናንተ የቆማችሁት ለመንግስት ፖለቲካ ነው፣ የመንግስት አጫፋሪዎች ናችሁ” በማለት ተናግረዋቸዋል ተብሎ ነው።  በሌላ ዜና ደግሞ በአሳሳ ወረዳ በ4 ሙስሊሞች ላይ የተፈጸመው ግድያ፣ ሙስሊሞቹ በፖሊስ ጣባያው ላይ ጥቃት ለመፈጸም በመሞከራቸው ነው ሲል መንግስት አስታውቋል።

ብሉምበርግ የመንግስትን ቃል አቀባይ የሆኑትን አቶ ሽመልስ ከማልን ጠቅሶ እንደዘገበው እርምጃው የተወሰደው ህዝቡ አንድ በእስር ላይ የሚገኙ የሀይማኖቱን መሪ ለማስፈታት ሙከራ በማድረጉ ነው። 10 ፖሊሶች መቁሰላቸውን፣ የፖሊስ ጣቢያውና የፖስታ ቤቱ መቃጠላቸውን ፣ እንዲሁም ድርጊቱን ፈጽመዋል ተብለው የተጠረጠሩ 24 ሰዎች መታሰራቸውን አቶ ሽመልስ ተናግረዋል።

 አንድ አክራሪ ኢማም ጂሀድ ለማስነሳት ሲቀሰቅሱ መገኘታቸውን ተከትሎ ፣ ፖሊስ በቁጥጥሩ ስራ ካወላቻው በሁዋላ፣ ደጋፊዎቻቸው እንዲፈቱ በመጠየቃቸው የተፈጠረ መሆኑን አቶ ሽመልስ ለብሉምበርግ ዘጋቢ ተናግረዋል። ሌሎች ወገኖች ግን የመንግስት ታጣቂዎች እርምጃውን የወሰዱት አቶ መለስ በቅርቡ የአልቃይዳ ኔት ወርክ አርሲ ውስጥ ተገኝቷል ብለው መናገራቸውን ተከትሎ ነው ይላሉ።

ከ70 በላይ የፓኪስታን ዜጎች ጋምቤላን ለቀው ወጡ

ኢሳት ዜና:-
ባለፈው ቅዳሜ በጋምቤላ በፓኪስታንና በኢትዮጵያውያን ላይ በተፈጸመው ጥቃት አራት ኢትዮጵያውያን እና አንድ ፓኪስታናዊ መገደላቸውን እንዲሁም አራት ፓኪስታናውያንና 5 ኢትዮጵያውያን መቁሰላቸውን ተከትሎ፣ በሼክ ሙሀመድ ሁሴን አል አሙዲን ሳውዲ ስታር ኩባንያ ውስጥ በከፍተኛ አመራርነት ይሰሩ የነበሩ ከ70 በላይ የፓኪስታን ዜጎች አካባቢውን ለቀው ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘዋል።

 ፓኪስታናውያኑ አካባቢውን የለቀቁት የፓኪስታን ኢምባሲ ባለስልጣናት ጋምቤላ መግባታቸው ከተነገረ በሁዋላ ነው። ኢንጂነሮች፣ የተለያዩ ማሽኖች ላይ ሲሰሩ የነበሩ ፓኪስታናዊያን አካባቢውን ለቀው የሚወጡት በዚህ ሁኔታ ለመስራት እንደማይችሉ ካስታወቁ በሁዋላ ነው። አንድ ፓኪስታናዊ እንደተናገረው ” መቼ እንደምንመለስ አናውቅም፣ ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ ወደ ዚህ አካባቢ ተመልሰን እንመጣለን የሚል እምነት የለንም፣ ሁኔታው አስፈሪ ነው” ብሎአል።

የፓኪስታናዊያኑ ስራ አቋርጦ መሄድ የሳውዲ ስታር መዘጋትን ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት ማሳደሩም ታውቋል። በአሁኑ ጊዜ የኩባንያው ሰራተኞች ስራቸውን ሙሉ በሙሉ ያቆሙ ሲሆን፣ ትናንት ጋምቤላ የተገኙት የሳውዲ ስታርና የሚድሮክ  ባለስልጣኖች ለፓኪስታናዊያኑ በቂ የደህንነት ዋስትና ሊሰጡዋቸው ባለመቻላቸው ፣ ፓኪስታናዊያኑ ለመልቀቅ ሳይገደዱ እንዳልቀረ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

 ከትናንት ጀምሮ ደግሞ የመከላከያና የክልሉ ባለስልጣናት ህዝቡን ሲያነጋግሩ መዋላቸው ታውቋል። የመካለከያ ባለስልጣናቱ ለነዋሪዎች ” የእኛ እዚህ መኖር የእናንተ ድጋፍ ካልታከለበት ዋጋ የለውም፣ አጥፊዎችን አጋልጣችሁ ካልሰጣችሁን እኛ በራሳችን የደህንነታችሁን ዋስትናችሁን ለማረጋገጥ አንችልም።” በማለት ሲቀስቀሱ እንደነበር ታውቋል።

 በዛሬው እለትም የክልሉ ፕሬዚዳንት ሳይቀር በቅስቀሳው ስራ ላይ በመሰማራት ” ታጣቂዎቹ ከእኛ አልፈው በውጭ አገር ዜጎች ላይ ጥቃት መፈጸም በመጀመራቸው ህዝቡ ማንነታቸውን አጋልጦ ለመንግስት አሳልፎ ሊሰጥ ይገባዋል።” በማለት ሲናገር ተደምጧል። የህዝቡ ዝምታ ያስፈራው የክልሉ መንግስት ትናንት ባደረገው ዝግ ስብሰባ ” ነዋሪው የፊታችን ሀሙስ ወደ አደባባይ በሰልፍ በመውጣት ድርጊቱን እንዲያወግዝ እንዲሁም የልማት እንቅስቃሴው በፈቃዳችን የሚካሄድ እንጅ ያለፍላጎታችን የሚካሄድ አይደለም በማለት የአገሪቱ ዋና ዋና የመገናኛ ብዙሀን ባሉበት እንዲገልጥ ይህም በመገናኛ ብዙሀን በስፋት እንዲሰራጭ” ውሳኔ አሳልፎአል።

 በሌላ በኩል ደግሞ  10 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፕሬዚዳንት ተናግረዋል። በክልሉ የሚፈጸሙት ጥቃቶች በክልሉ የሚካሄደውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ ያለመ መሆኑን ርእሰ መስተዳድሩ አቶ ኦቦንግ ኦሞድ አረጋግጠዋል።  ጥቃት አድራሾቹ የክልሉ ልማት የማይዋጥላቸው ልማቱን ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀሱ የጸረ ሰላም ሃይሎች ናቸው ያሉት ኦሞድ  በርካታ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውንም ተናግረዋል።

 ሌሎችን የድርጊቱን ፈጻሚዎች ተከታትሎ ለመያዝም የፌዴራልና የክልሉ ፖሊስ ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን እየተንቀሳቀ እንደሚገኝ ነው አቶ ኦሞድ የገለጡት። ከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃ በሚካሄድባት ጋምቤላ የሚፈጸመው ጥቃት ፣ የመለስ መንግስት በአገሪቱ ውስጥ እየደፈረ የመጣውን ሰላም ለማስቆም አለመቻሉን እንደሚያሳይ ምሁራን ይናገራሉ። የመከላከያ ሰራዊት አባላት እስካሁን ድረስ ችግሩን ለመቆጣጠር ያልቻሉት ጸቡ ከህዝቡ ጋር በመሆኑ ነው በማለት የሚገልጡ ወገኖችም አሉ። 

እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት በጋምቤላ የሚካሄደውን የመሬት መቀራመት መላው ህዝብ እያወገዘው እና እየተወጋው የሚገኝ በመሆኑ፣ ሰላም ማስከበር የሚቻለው መላውን ህዝብ መጨፍለቅ ሲቻል ብቻ ነው በማለት መንግስት የጀመረው የሀይል እርምጃ እንደማያዋጣው ይገልጣሉ። የሼክ ሙሀመድ አላሙዲ ድርጅት ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ሰራተኞች ላይ ለደረሰው ጉዳት እንዲሁም ባለፈው ቅዳሜ በፓኪስታናዊያኑ እና በኢትዮጵያውያኑ ላይ በደረሰው ሞት ከፍተኛ ካሳ ሊከፍል እንደሚችል የውስጥ ምንጮች ይናገራሉ።

Monday, April 30, 2012

በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ ተመሙ፣ ሁለት ነጮች ተገድለዋል ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል

ኢሳት ዜና:-
በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ ተመሙ፣  ሁለት ነጮች ተገድለዋል ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል የገዳሙ አባቶች ለሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ባቀረቡት ጥሪ መሰረት እስከ 200 ኪሎሜትር ርቀት የሚገኙ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ አካባቢው መትመማቸውን ተከትሎ ሁለት ነጮች መሞታቸውን፣ ሌሎች ሰራተኞች ደግሞ እኛ ከህዝብ ጋር አንጣላም በማለት አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል። 

የሟቾቹ እና አካባቢውን ለቀው የወጡት ነጮች ምእርባዊያን ይሁኑ የቻይና ዜጎች አልታወቀም። ከ5ሺ ያላነሱ የአካባቢው ነዋሪዎች በዋልድባ ተገኝተው ተቃውሞ እያሰሙ ሲሆን፣ የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ አባላትም እርምጃ ለመውሰድ ፈርተዋል። ሁኔታው እጅግ አስፈሪ ነው፣ መንግስትና ህዝቡ ተፋጠዋል፣ የአካባቢው ወጣቶችም ወደ አካባቢው ለመጓዝ እየተመካከሩ ነው ሲል አንድ ጉዳዩን በቅርብ ሆኖ የሚከታተል ሰው ለኢሳት ገልጧል።

“ሰራተኞቹ እኛ ለህዝብ ልማት ይውላል ተብሎ ነው የመጣነው፣ እናንተማ ካልፈለጋችሁት እኛ እዚህ ምን እናደርጋለን?” በማለት አካባቢውን ለቀው በመውጣታቸው፣ በአሁኑ ጊዜ ስራው ሙሉ በሙሉ ቆሟል። መንግስት ስራው ተቋርጧል በማለት ለአካባቢው ነዋሪዎች ቢናገርም፣ ህዝቡ ግን ሚጢቆ በሚባል ቦታ ላይ የተተከሉት ሁለቱ የኤሌክትሪክ ጄኔሬተሮች ካልተነሱ ስራው መቋረጡን ከልብ አምነን ለመቀበል  አንችልም የሚል መልስ ሰጥቷል።

የአካባቢው ህዝብ አሁንም ጄኔሬተሮቹ እስኪነሱ ድረስ በትእግስት በአካባቢው ተገኝቶ እየጠበቀ ነው። ህዝቡ በስንቅ እጦት እንዳይቸገር እርስ በርሱ  እየተተካካ እንደሚጠብቅ ለማወቅ ተችሎአል። የገዳሙ አባቶች ” ከሀይማኖት ወዲያ ምን አለ፣ ለሀይማኖት መሞት ጽድቅ ነው።” በማለት ሰሞኑን ህዝቡን እየዞሩ ሲያስተምሩ ነበር። መንግስት የተወሰኑ መነኮሳትን አፍኖ መውሰዱም ታውቋል።

አሁን በሚታየው ስሜት የዋልድባ የስኳር ግንባታ ተፈጻሚ ሊሆን እንደማይችል አንድ የአካባቢው ሰው ለኢሳት ተናግረዋል። የህዝቡ ቁጣ ከመጠን እያለፈ ነው ያሉት እኝህ ሰው ፣ መንግስት ከህዝቡ ጋር እልህ ውስጥ የሚጋባ ከሆነ ከፍተኛ ጉዳት ሊደርስ ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የመንግስት ባለስልጣናት በግንባታው ዙሪያ የሀይማኖት አባቶች ስምምነታቸውን ሰጥተዋል ቢሉም፣ ህዝቡ ግን የሚቀበለው አልሆነም።

በጋምቤላው በደረሰው ጥቃት የሞቱት የሳውዲ ስታር ሰራተኞች ተሸኙ

ኢሳት ዜና:-
ከጋምቤላ በምስል ተደግፎ ለኢሳት የተላከው ዘገባ እንዳመለከተው ባለፈው ቅዳሜ በአበቦ ወረዳ በሳውዲ ስታርና በሳውዲ ስታር ሰብ ኮንትራክተር በሆነው CRBC ኩባንያ ሰራተኞች ላይ ቅዳሜ እለት በተፈጸመው ጥቃት የሞቱት ዛሬ በአንድ የመከላከያ ሰራዊት ሄሊኮፕተር እና በአንድ አውሮፕላን ተጭነው ወደ አዲስ አበባ ተሸኝተዋል።

ድርጊቱ የተፈጸመው ሰራተኞቹ ከአሌሮ ግድብ የሚወጣውን ውሀ ለሩዝ እርሻው ለማቅረብ የቧንቧ መስመር ዘርግተው እንደጨረሱ ወደ ሰርቪሳቸው በመመለስ ላይ እያሉ ነው። አንድ የአይን እማኝ ለኢሳት እንደገለጠው ሰራተኞቹ ወደ  ሰርቪሳቸው እየተመለሱ በነበረበት ጊዜ የሳውዲ ስታር ጠባቂ የሆኑት የአካባቢው ተወላጆች በሞባይል ስልክ መልእክቶችን ተለዋውጠው ተኩስ ከፍተዋል። በተኩሱም አንድ ፓኪስታናዊ ጨምሮ 5 ሰዎች ሲገደሉ፣ 4 ፓኪስታናዊያንና 5 ኢትዮጵያውያን ቆስለዋል።

ጥቃቱን የፈጸሙት የሳውዲ ስታር ዘበኞች ናቸው ያለው ይህ ግለሰብ፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከአካባቢው ራቅ ብለው በመገኘታቸው ጥቃቱን ለማስቆም እንዳልቻሉ ተናግሯል። ይሁን እንጅ በአቶ ኦባንግ ሜቶ የሚመራው ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በመህጻረ ቃሉ አኢጋን ዛሬ ባወጣው ዘገባ ጥቃቱን የፈጸሙት ታጣቂዎች ናቸው ብሎአል። መንግስትም ጥቃቱን የፈጸሙት ታጣቂዎች መሆናቸውን አምኗል።

ሽፍታ በሚል ስያሜ የሚጠሩት ታጣቂዎች ንብረትነቱ የሼክ መሀመድ ሁሴን አላሙዲ የሖነውን የሳውዲ ስታር እርሻ ሁለገብ ካምፕ ያለአንዳች ችግር ዘልቀው ከገቡ በሁዋላ የኮማንዶ ስልት በተሞላበት ቅልጥፍና እና ፍጥነት በመከፋፈል የእርሻውን ስራ ማከናወኛ ቢሮ፣ የዋና ዋና ስራተኞች መኖሪያ ካፍቴሪያና የተመረጡ ቦታዎችን በመቆጣጠር ተግባራቸውን አከናውነዋል ሲል ኢጋን ዘግቧል።

ታጣቂዎቹ አራት ከፍተኛ የእርሻ ኤክስፐርት የሆኑ የፓኪስታን ዜጎችን ገድለው ሶስቱን ማቁሰላቸውን እንዲሁም አራት ኢትዮጵያዊ ሰራተኞችና አንድ የአኝዋክ ተወላጅ የጥበቃ ፖሊስ መገደላቸውንና ስድስት የሚሆኑት መቁሰላቸውን ዘገባው ጨምሮ ያስረዳል።

የኢሳት ዘጋቢ በላከው ዘገባ እንደሚለው ድርጊቱን ፈጽመዋል ተብለው ከሚጠረጠሩ 10 የአካባቢው ተወላጆች መካከል የተወሰኑት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ ነው። በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱት ሰራተኞች ገሚሶቹ ወደ መቱ ሆስፒታል ሲወሰዱ፣ ሌሎች ደግሞ ወደ አዲስ አበባ ወደ ቤተሰቦቻቸው ተልከዋል።

በዛሬው እለት የሳውዲ ስታር እና የሚድሮክ  ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ ጋምቤላ ያቀኑ ሲሆን ፣ ሰራተኞች ከግቢያቸው እንዳይወጡ፣ ስራም እንዲያቆሙ ትእዛዝ ተሰጥቷቸዋል። በአካባቢው ያለ ማንኛውም እንቅስቃሴም እንዲቆም ተደርጓል። በጋምቤላ   ቀደም ሲል በተካሄደ ተመሳሳይ ድንገተኛ ጥቃት ሰው መገደሉና ሳውዲ ስታር” ተብሎ  የሚጠራው የ አል አሙዲ እርሻ ድርጅት ገንዘብ ያዥ የነበረ ግለሰብ ክፉኛ ቆስሎ ለህክምና ወደ አዲስ አበባ መወሰዱ  ይታወሳል።

እንዲሁም ሌላ  በሰፊ መሬት ላይ በእርሻ ሥራ ላይ ተሰማርቶ የነበረ ኢትዮጵያዊ ወጣት ድንገት በታጣቂዎች ተገድሎ አስከሬኑ ቤተሰቦቹ ወደሚገኙበት ወደ መቀሌ ከተማ እንደተወሰደ ኢሳት መዘገቡ አይዘነጋም። ከዚህም ባሻገር የደህንነት ሀላፊ የነበሩትን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ባለስልጣናት ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በከፈቱባቸው ተኩስ ህይወታቸውን ማጣታቸው በተደጋጋሚ ሢዘገብ ቆይቷል።

ከአንድ ወር በፊት ደግሞ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 19 ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጋምቤላ እየተባባሰ ለመጣው እና የመንግስት ራስ ምታት እስከ መሆን ለደረሰው  ለዚህ ተደጋጋሚ ጥቃት ዋነኛ ምክንያቱ ፤ መንግስት የ አካባቢውን ተወላጆች ከይዞታቸውና ከቀያቸው እያፈናቀለ መሬታቸውን  በውዳቂ ዋጋ ለውጪ ባለሀብቶችና ለራሱ ካድሬዎች መስጠቱ ያስከተለው ቁጣ እንደሆነ ይነገራል።

መንግስት ታጣቂዎቹን ለማደንና  ለባለሀብቶቹ ዋስትና ለመስጠት የከተማዋን ዙሪያ በሜካናይዝድ ጦር ማስጠበቅ ከጀመረ ቢሰነብትም፤ እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት ሊቆጣጠረው አልቻለም። በተለይ መንግሰት ፦’የተሟላ ጥበቃ እያደረግኩ ነው”በሚልበት በአሁኑ ጊዜ የተፈመው ጥቃት፤ በአካባቢው በእርሻ ሥራ ላይ የተሰማሩትን  ቀሪ  ባለሀብቶች ስለ ቀጣዩ ቆይታቸው ደጋግመው እንዲያስቡ ፤ በአካባቢው  እንደ አዲስ  ለመሰማራት አስበው የነበሩ ሌሎች ባለሀብቶችንም እግራቸውን እንዲሰበስቡ የሚያደርግ ነው ተብሏል።
__________________________________________________________________________________________________________

Four People Die After Ethiopian Muslims Attack Police Station

Four people were killed in southeastern Ethiopia when Muslim protesters attacked a police station following the arrest of a preacher, said State Minister of Communications Shimeles Kemal. 

The deaths occurred on April 27 in Asasa, in the Arsi Zone of Oromia region, after a crowd tried to free the imam, Shimeles said in a phone interview today from Addis Ababa, the capital. Ten policemen were injured, the police station and post office burned down and 24 people arrested, he said. 

“A certain imam, an Islamic fundamentalist, had been trying to instigate jihad,” said Shimeles. “When police arrested him, his supporters tried to get him released forcefully.” 

Incidents of religious strife in Ethiopia are rare, though there have been fatal sectarian clashes in the southwest of the country in recent years. Ethiopia is Africa’s second-most populous nation, after Nigeria. Its people are 44 percent Ethiopian Orthodox Christian, 34 percent Muslim and 19 percent Protestant, according to the CIA World Factbook. 

An al-Qaeda cell containing a “few Salafist extremists” was captured in Arsi, Prime Minister Meles Zenawi told lawmakers on April 17, without providing further details, according to the Foreign Ministry. To contact the reporter on this story: 

William Davison in Addis Ababa via Nairobi at pmrichardson@bloomberg.net. To contact the editor responsible for this story: Paul Richardson in Nairobi at pmrichardson@bloomberg.net.