Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Friday, May 3, 2013

! …… ከ ፍሰሓ ደስታ ጋር ማወዳደር ! ለምን? ……!



በተወሰኑ ካድሬዎች (በትግርኛ) ተፅፎ የኣብርሃን ፅሑፎች ይቃወማሉ ተብለው ለታመነባቸው ፌስቡከኞችና ለህወሓት ኣባላት የተበተነው ፅሑፍ ኣይቸዋለሁ። ፍሬ ሓሳቡኣብርሃ ደስታ ልክ እንደነ ፍሰሃ ደስታ የራሱን ክብር ኣሳልፎ ለመስጠት፣ ቤተሰቡና ሀገሩ ለመሸጥ ከትግራይ ጠላቶች ኣብሮ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ተጋሩ ግን ……” የሚል መልእክት ኣለው:: ይሄንንግብረ መልስየተሰጠው ሰው በተግባሩ (በሰራው ስራ) እንጂ በዘር ሀረጉ፣ በሃይማኖታዊ እምነቱና ፖለቲካዊ ኣመለካከቱ ሊመዘን ኣይገባምየሚል መልእክት ያለው ሓሳብ በመፃፌ ነው።

ይሄንን ታድያ የኣንድ ህዝብ ክብር ኣሳልፎ መስጠት ኣይደለም። የሰው ክብር ያለው ሰው በመሆኑ ላይ ነው። ሰው እንደሰው መከበር ኣለበት፤ ሌላው ሁሉ የግል ጉዳይ ነው። እኔ የመሰለኝን ሓሳብ ስለፃፍኩና ሌሎችን ሰዎች (ማናቸውም ከትግራይ ወይ ኢትዮዽያ ወይ ኣውሮፓ ወይ የትም) የኔን ሓሳብ ቢጋሩ እንዴትክብርን ለሌሎች ኣሳልፎ  መስጠትሊባል ይችላል? እኔ ሀገር ለመሸጥ ኣልተነሳሁም።  

በሀገር ኣንድነት ነው የማምነው። ከፍሰሃ ደስታ የሚያመሳስለን ይሄ ነጥብ ነው። እኔ ፍሰሃ ደስታን የምቃወመው ለሀገር ኣንድነት በመቆሙና ከሌሎች ኢትዮዽያን ወንድሞች ኣብሮ በመስራቱ ኣይደለም። እኔ ከሱ (ፍሰሃ ደስታ) ጋር የምለይበት ነጥብ (የማልስማማበት) የደርግን ጨቋኝ ስርዓት ኣካል ሁኖ ኢትዮዽያውያንን (ትግራይ ጨምሮ) በመበደሉ ነው።

ህዝብን በሃይል የሚገዛ፣ የሚያፍን፣ የሚጨቁን፣ የሚገድል ባለስልጣን ኣልወድም (እቃወማለሁ) ለዚህ ነው የህወሓትን ባለስልጣናት የምቃወማቸው። ስለዚ የጨቋኙ ደርግ ስርዓት ኣካል ስለነበር (ፍሰሃ ደስታ) ከህወሓት ባለስልጣናት እንጂ ከኔ ጋር የሚመሳሰልበት ኣጋጣሚ የለም። እኔ ጭቆናን የማልወድ ተራ ሰለማዊ ሰው ነኝ። ከጨቋኞች ጋር የሚተባበርም ኣልወድም። ለዚህ ነው የህወሓት ኣባላትና ደጋፊዎች ከድርጊታቸው (ገዢው ፓርቲ ከመደገፍ) እንዲቆጠቡ በሓሳብ ለማሳመን ጥረት የማደርገው (መደገፍ መብታቸው ቢሆንም)

ደሞኮ ፍሰሃ ደስታ ሀገር ለመሸጥ ኣልተንቀሳቀሰም። ስለ ኢትዮዽያ ኣንድነት ሲዋጋ ነበር። ኤርትራን (ላለማስገንጠል እንጂ) ለማስገንጠል ኣልታገለም። ሀገራችን ወደብ ኣልባ ለማድረግ ኣልታገለም። ሀገር ለመሸጥ የታገሉ ሌሎች ናቸው። እኔም የሀገር ኣንድነትና ልኣላዊነት እንዲከበር ጥረት የማደርግ ሰው ነኝ።

ከትግራይ ጠላቶች በማበርየሚል ነገር ኣለ። የትግራይ ጠላት ማነው? እንደኔ እምነት: የትግራይ ህዝብ ጠላት ጭቆና ነው። ጠላቶቹ ጨቋኞቹ ናቸው። ድሮ ደርግ ነበር ጨቋኝ፣ ኣሁን ደግሞ ህወሓት። ስለዚ የትግራይ ጠላቶች ጨቋኝ ገዢዎቹ እንጂ ሌሎች ብሄሮች ወይ ሌላ ሃይማኖት ተከታዮች ኣይደሉም። እኔም ከጨቋኞች ጋር ኣላበርኩም። 

 የኔ ጓዶች ነፃነት ፈላጊ ናቸው።ሓሳብን በነፃነት መግለፅ መቻል ከጠላቶች ጋር ማበር ያሰኛል እንዴ? ተጋሩ (የትግራይ ተወላጆች) የራሳቸው የፖለቲካ ኣቋም ይዘው ገዢውን መደብ ሲቃወሙከጠላቶቻችን ኣብረዋልበሚል ሴራ በመንግስት ደጋፊዎች ከተነቀፉኮ የትግራይ ተወላጆች የመቃወም መብት የላቸውም ማለት ነው።
 
(ወይም እንዲቃወሙ ኣይፈቀድላቸውም ማለት ነው)።በዚህ መልኩ (ተጋሩ የመቃወም መብታቸውን ከተገደበ) ‘ከትግራይ ወጥቼ ለትግራይ እቆማለሁየሚል የህወሓት ድርጅት ፀረ ተጋሩ እየሆነ ነው ማለት ነው። ህወሓት ለትግራይ ቢቆም ኑሮ እኛ ተጋሩ የፈለግነውን የፖለቲካ ኣመለካከት እንድነራመድ ለምን ኣይፈቅድልንም? ደርግ ኣፈነን። ህወሓትም እንዲህ ካፈነን፣ ህወሓት ከደርግ (ለትግራይ ህዝብ) በምን ይሻላል? በምንስ ይለያል???

ህወሓት የመናገር መብታችን ካላከበረ፣ ሁሉም የትግራይ ሰው በእኩል ዓይን ካልታየ፣ በተግባሩና በስራ ኣፈፃፀሙ መመዘን ሲገባው በጎጠኝነት (ከባቢያዊነት) ኣንተ ከኣድዋ ነህ፣ ዓጋሜ ነው፣ ሓውዜን፣ ተምቤን፣ እንደርታ፣ ራያወዘተ እየተባለ በስራው ግልፅ የሆነ ኣድልዎ ከተፈፀመበት፡ ከዚህ በላይ የህዝብ ጠላትነት ከየት ሊመጣ ነው? በተግባራችን (በምንሰራው ስራ) ከተመዘንን የትግራይ ጠላት (በኣሁኑ ግዜ) ህወሓት እንጂ እኔ ኣይደለሁም በኣባቶቻችን ላይ ኣድሎኣዊ በደልና ጭቆና እያደረሰ ያለው ህወሓት ነውና። 

ህይወቱ ሙሉ ከጭቆና ነፃ ለመውጣት ሲታገል የኖረ ህዝብ የእኩልነት መብቱ ሲነፈግ (እኔ ) እኛ ዝም ብለን ሳንቃወም ማየት ነበረብን? ብዙ መስዋእት የተከፈለበት 17 ዓመት የትጥቅ ትግል በተወሰኑ ሰዎች ተጠልፎ ለግል ስልጣንና ጥቅም ሲውል እኛ ዝም ብለን ተመካች እንድንሆን ነው የሚጠበቀው? ወይስ የርሳችን ሚና መጫወት ይኖርብናል!? ባጠቃላይ እኔ ማንም ሰው (ፍሰሃ ደስታን ጨምሮ) የምመዝነው በተግባሩ ነው። ህወሓትን የምቃወመው ከትግራይ ስለመጣ (ወይ ስላልመጣ) ኣይደለም፤ የሚሰራው ስራ ለህዝብ ስለማይጠቅምና ኣሁን ካለው ገዢ ፓርቲ በሁለመናው የተሻለ ኣማራጭ ፓርቲ እንደሚያስፈልገን በመረዳት ነው። ጥያቄው ቀላል ነው።
 
ኣሁን ባለው የህወሓት ኣስተዳደር ረክተናል? (ለውጥ እንዳይመጣ እየታገልን ነው?) ወይስ ለውጥ ያስፈልገናል? በህወሓት ጥላ ስር መኖር (መጠለል) ይሻለናል ወይስ ሌላ የተሻለ ስርዓት መመስረት እንደምንችልና ህዝባችንን ጥቀም እንደምንችል የራስ መተማመን ኣለን? ህዝቡ እነዚህ ሁለት ኣማራጮች ይሰጡት። የፖለቲካ ለውጥ የሚፈልጉና የማይፈልጉ ሃይሎች በነፃነትና በእኩልነት ሓሳባቸውን ለህዝብ ያቅርቡ። ህዝቡ ምርጫውን ያሳውቅ።  
የህዝቡን (የኣብዛኛው) ምርጫ ምን እንደሆነ በገለልተኛ ወገን (ምርጫ ቦርድና የፍትሕ ኣካላት) ይገለጥ። ዉሳኔውም ኣብዛሃ ህዝብ የመረጠውን ይሁን። የተመረጠውን ስልጣን ይያዝ። ዴሞክራሲ ይስፈን። ስልጣን ወደ ህዝብ ይውረድ። ሓሳቤ ይህ ነው። ለምፅፈው ሓሳብ የሓሳብ ግብረ መልስ ከመስጠት ይልቅ ወደ ህፀፅ (Fallacy) መግባት ኣያስፈልግም። በሓሳብ መከራከር ኣለብን። የተለያዩ የፖለቲካ ኣስተያየቶች ማንሸራሸር ለህዝቡ ይጠቅማል እንጂ ኣይጎዳም። ለህዝቡ ጥሩ ነገር ከመስራት በሚቃወሙ ሰዎች ላይ ስም የማጥፋት ዘመቻ ማካሄድ ተገቢ ኣይመስለኝም። 

 ዓላማዬ ዴሞክራሲን እንዲሰፍን ጥረት ማድረግ ነው። 

ከ አብርሃ ደስታ 
ከራሱ ፌስቡክ የተወሰደ

No comments:

Post a Comment