Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Sunday, September 16, 2012

በሐሰት ወሬ ሕዝብን ለአመፅ አነሳሳ የተባለ ግለሰብ በአንድ ዓመት እስራት ተቀጣ

By reporter: የፌዴራል መጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አምስተኛ የወንጀል ችሎት፣ በመንግሥት ላይ ጥላቻን ለማስፋፋት በማሰብ ሕዝብን በሐሰት ወሬ አነሳስቷል የተባለውን ግለሰብ፣ በአንድ ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መስከረም 3 ቀን 2005 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ውሳኔ ሰጠ::


ተከሳሹ አቶ ጀማል ከድር በመንግሥት ላይ ጥላቻን ለማስፋፋት በማሰብ በራሱ ሞባይል ስልክ በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ ሰዎች 17 ጊዜ ‹‹አላህዋ አክበር፣ ‹‹ድምፃችን ይሰማ››፣ ‹‹የታሰሩት ይፈቱ››፣ ‹‹ሕዝቡ ወደ አንዋር መስጂድ እንዳይገባ ፖሊስ እየከለከለ ነው››፣ ‹‹ወንድሞቻችን እስኪፈቱ ተቋውሞአችንን በሥራ ማቆም አድማ እንቀጥላለን››፣ አወሊያ ያሉ ሙስሊም ወንድሞቻችን ስለቃሽ ጭስ ተለቆባቸው ግቢ እንዲለቁ እየተደረገ ነው፤ አደራ! አደራ! የታሰሩ ወንድሞቻችን ካልተፈቱ ምርጫ አንመርጥም›› የሚሉና ሌሎች ቀስቃሽ መልዕክቶችን በመላክ ለሕዝብ የሐሰት ወሬዎችን በመንዛት ወንጀል በፌደራል ዓቃቤ ሕግ ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም ክስ ተመሥርቶበት ነበር::

ዓቃቤ ሕግ ክሴን ያስረዱልኛል ያላቸውን የሰውና የጽሑፍ እንዲሁም የኤግዚቢት ማስረጃዎቸን ከክሱ ጋር አያይዞ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል:: ተከሳሹም ወንጀሉን ስለመፈጸሙ የእምነት ከህደት ቃሉን ሲጠየቅ ‹‹ወንጀሉን አልፈጸምኩም ጥፈተኛም አይደለሁም›› ያለ በመሆኑ የዓቃቤ ሕግ የሰው ምስክሮች ተሰምተዋል:: የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ክሱን በሚያስረዳ መልኩ  ምስክርነታቸውን ስለሰጡ ተከሳሹ መከላከያ ምስክሮች ካሉት እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል::

የተከሳሹ ጠበቃም የመከላከያ ምስክሮችን ለማሰማት በተቀጠረበት ቀን ምስክሮቹ ሊመሰክሩላቸው እንደማይችሉ በመግለጽ፣ በተሰሙት የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ቃልና በቀረበው ማስረጃ ብቻ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል:: ፍርድ ቤቱም ጳጉሜን 5 ቀን 2004 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ግልጽና አስተማማኝ በሆነ ሁኔታ ያስረዱ ስለሆነና ተከሳሹም ማስተባበል ስላልቻለ የጥፋተኝነት ውሳኔ ሰጥቷል::

ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው የቅጣት ማክበጃ ባይኖርም ተከሳሹ ሪከርድ የሌለበት መሆኑን፣ የጤና ችግር እንዳለበትና የቤተሰብ አስተዳዳሪ እንደሆነም በመግለጽ ቅጣቱ ቀለል ብሎ እንዲወሰንለት ለችሎቱ አሳስቧል:: ፍርድ ቤቱም የቀረበውን የቅጣት ማቅለያ ከግምት በማስገባት ተከሳሽ ጀማል በአንድ ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል::

No comments:

Post a Comment