Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Sunday, June 3, 2012

የመሬት ቅርምት ወደ ግጭት ሊያመራ እንደሚችል አንድ ታዋቂ ጋዜጣ ዘገበ

ኢሳት ዜና:-
በስዊዘርላንድ የሚታተም ታገስ አንዛይገር የተባለ ጋዜጣ  ፣ በመሬት እና ባካባቢው ከሚኖሩ ዜጎች ፍላጎት እና ስምምነት ውጭ የሚደረግ ማንኛውም ኢንቨስትመንት  በባለሃብቶች እና ባካባቢው በሚኖሩ ዜጎች መካከል በሚፈጠር  አለመግባባት ወደ ከፍተኛ ግጭት ሊያመራ እና   በሃገሪቷ ውስጥም አለመረጋጋት ሊፈጥር እንደሚችል አስጠንቅቋል።

ጋዜጣው የአቶ መለስ ዜናዊ አስተዳደር ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው የእርሻ መሬት 10% ወይም 3.6 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለውጭ ባለሀብቶች እንደተሰጠ ዘግቧል።

በኢትዮጵያ እና በሌሎች ደሀ አገሮች  የሚኖሩ አነስተኛ ገበሬዎች    ህይወታቸውን መሰረት ያደረጉበት መሬታቸው ለውጭ ባለሀብቶች በመቸብቸቡ እና ከቀዬአቸውም እየተፈናቀሉ መሆናቸው የወደፊት መጻኢ እድላቸው አደጋ የተጋረጠበት ነው ሲል አስፍሯል።

ታገስአንዛይገር በመቀጠል በአለም ዙሪያ በተለይ በታዳጊ ሀገሮችና ባላደጉ ሀገሮች ላይ እየተካሄደ ያለውን መሬት ነጠቃ በግንባር ቀደምትነት የምትመራው  ቻይና ናት ብሎአል።

ይህ መሬት ነጠቃም በዋናነት ያተኮረው ባላደጉ ሀገሮች ላይ እና ጠንካራ የመሰረተ ልማት አገልግሎት በሌለባቸው ረሀብና ድህነት በከፍተኛ ደረጃ በሚያጠቃቸው እንዲሁም መንግስት ለዜጎቹ መብት በማይጨነቅባቸው ሀገሮች ላይ እንደሆነ የጠቆመው ጋዜጣው፣ ባለሀብቶቹም በነዚህ ሀገሮች ላይ በከፍተኛ ደረጃ በማተኮር ገንዘባቸውን በማፍሰስ ላይ መሆናቸውን ከላንድ ማትሪክስ ጥናት ለመረዳት ተችሏል በማለት ገልጿል።

ጋዜጣው በአሁኑ ወቅት እየተስፋፋ ያለው የመሬት ቅርምት ካልተገታ በታዳጊ እና በማደግ ላይ ባሉ ሃገራት ውስጥ በሚገኙ አነስተኛ ገበሬዎች የወደፊት ህይወት ላይ ከፍተኛ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል አሳስቦአል።

No comments:

Post a Comment