Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Wednesday, June 20, 2012

በትላንትናው ምሽት መገናኛ አካባቢ ከሕገ-ወጥ ንግድ ጋር በተያያዘ ነጋዴዎችና ፖሊሶች ተጋጩ - የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል ተባለ

By Feteh newspaper, no. 192
በየካ ክ/ከተማ በቀድሞ ቀበሌ 16 መገናኛ ታክሲ ተራ በሚባለው አካባቢ መንግስት ሕገወጥ በሚላቸው የመንገድ ላይ ነጋዴዎችና ፖሊሶች መካከል በትናንትናው ምሽት በተፈጠረ ግጭት የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን የአይን እማኞች ለፍትሕ ገለፁ።

የታክሲና የእግረኛ ግርግር በማይለየው በየካ ክ/ከተማ ቀበሌ አስተዳደር የፍትሕ፣ የህግ ጉዳዮች፣ የትምህርት፣ የጤና ክትትል ግንባታ ጽ/ቤት አካባቢ ትናንት አመሻሽ 1፡30 ሰዓት ገደማ በተፈጠረው ግርግር፣ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ሲጮሁና ሕፃናት ሲያለቅሱ እንደነበረ በወቅቱ በስፍራው የነበሩ ሰዎች ለፍትሕ ተናግረዋል።

ሕገ-ወጥ በሚባሉት ነጋዴዎችና በፖሊሶቹ መካከል በተፈጠረው ግጭት ተኩስ መሰማቱን፣ እንዲሁም ወደ ፖሊሶች ድንጋይ መወርወሩን ምንጮቻችን ገልፀዋል። አንድ ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ ላይ በስፍራው የደረሰው የፍትህ ዘጋቢ እንደተመለከተው ከመገናኛ ወደ 22 መስመር በሚወስደው መንገድ መኪኖች በቀጥታ ማለፍ እንጂ መቆም አይችሉም ነበር። በስፍራው ቁጥራቸው በጣም የበዙ ፌዴራል ፖሊሶች አካባቢውን ከብበው የነበሩ ሲሆን በፖሊስ መኪኖች ላይ ተይዘው የተጫኑ ወጣቶችን መመልከት ችሏል።

ስለተከሰተው ጉዳይ በስፍራው የነበሩትን የፌዴራል ፖሊስ ኃላፊዎችን የፍትህ ዘጋቢ ለማነጋገር ሞክሮ የነበረ ቢሆንም የፖሊስ ኃላፊዎቹ በአካባቢው ምንም አለመፈጠሩን ደጋግመው በመግለጽ ‹‹ምንም የምናውቀው ነገር የለም›› በማለት ለማስተባበል ሞክረዋል።

No comments:

Post a Comment