አገራችን በዓባይና በመጋቢ ወንዞች ላይ ግድብ ለመሥራት ሙከራ ስታደርግ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በ1959 ዓ/ም (እ.ኤ.አ) በግብፅና በሱዳን መሃል በተናጠል የተደረገውን ስምምነት በመቃወም አስር ሚሊዮን ዶላር በመመደብና በአሜሪካ ሙያተኞች አማካኝነት አያሌ ግድቦችን ለመገንባትና የውሃ ሃብቷን ለመስኖ አገልግሎት ለመጠቀም በ1964 ዓ/ም (እ.ኤ.አ) ጥናቶችን ማጠናቀቋን መጥቀስ ይቻላል።
የዚህን ዓይነት ብሔራዊ ጉዳይ ለማስፈጸም ወያኔ ብቻውን አመራሩን ጨብጦ በአገር ውስጥም ሆነ ውጪ ያለነውን ዜጎች በማስገደድም ይሁን በማታለል ገንዘባችንን ለመሰብሰብ ሲነሳሳ እኛም እንደ ዜጋ ይህ ወቅት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሙሉ መብቱ ከምን ጊዜውም በላይ ተጠብቆና ተከብሮ በአገሩ ኮርቶ በፈቃደኝነትና በደስታ የሚሳተፍበት እንዲሆን እንፈልጋለን።