Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Tuesday, June 5, 2012

በሰሜን ጎንደር ፍጥጫው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል

ሳት ዜና:-
ከዋልድባ ገዳም ጋር በተያያዘ በሰሜን ጎንደር ህዝብና በመንግስት መካከል ያለው ፍጥጫ፣ ሊፈነዳ መቃረቡን ዘጋቢዎች ከስፍራው ገልጠዋል።

የአካባቢው ህዝብ ስንቁን እየያዘ ወደጋዳሙ በመትመም ላይ ሲሆን፣ መንግስትም በደባርቅና አካባቢው በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የፌደራል ሰራዊቱን በትኖአል።

አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ሰው፣ በህዝቡና በመንግስት መካከል ያለው ፍጥጫ በመጨመሩ ምናልባትም ሰኔ 21 ግጭት ሊፈጠር ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ገልጠዋል። የአገር ሽማግሌዎች፣ ቀሳውስቱና ታዋቂ ሰዎች ችግሩን ለመፍታት በዛሬማ ወንዝ አካባቢ ውይይት እያደረጉ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ መፍትሄ ላይ ሊደርሱ አልቻሉም። 

የአካባቢው ሰዎች እንደሚሉት ከሆነ ግን ችግሩ በውይይት የሚፈታ አይሆንም። መንግስት ድርጊቱን እስካላቆመ ደረስ ተቃውሞው ይቀጥላል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ 5 ካህናት በደባርቅ መታሰራቸው ታውቋል። በቅርቡ ስለሺ ጥጋቤነህ የተባለ የደባርቅ ነዋሪ መታሰሩ ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment