Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Sunday, June 3, 2012

የሰሜን ጎንደር የመኢኣድ ምክር ቤት የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ ታሰሩ

ኢሳት ዜና:-
በጎንደር ከተማ አደባባይ እየሱስ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ታድሎ ተፈራ የታሰሩት ትናንት ሲሆን፣ ከ10 ያላነሱ ፖሊሶች ወደ ቤታቸው በመሄድ እና ከፍተኛ ፍተሻ በማካሄድ አፍነው ወስደውታል። የበለሳ ተወላጅ የሆነው አቶ ታደሎ ተፈራ  ጎንደር ከተማ ውስጥ ከአክስቱ ጋር ይኖር ነበር።

 አክስቱ  ወ/ሮ ዘርጊባቸው ሀይሉ ለኢሳት እንደገለጡት ግለሰቡን በርካታ ፖሊሶች ስራ ይሰራበት ከነበረው ደልጊ ከተማ ይዘው በመምጣት ቤቱን ፈትሸዋል:: በደባርቅ አቶ ስለሺ ጥጋቤነህ ፣ በጭልጋ ደግሞ አቶ መለሰ አስሬ  ከትናንት በስቲያ ታፍነው መወሰዳቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ግለሰቦቹ ታፍነው ስለተወሰዱበት ምክንያት እና የት እንዳሉ የታወቀ ነገር የለም። ይሁን እንጅ ዛሬ ከአቶ መለሰ ቤተሰቦች ባገኘነው መረጃ ግለሰቡ ቤታቸው ሲፈተሽ ምንም ነገር አልተገኘባቸውም። የጭልጋ ነዋሪዎች ድርጊቱን ለመቃወም ሙከራ ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም።  መንግስት በግለሰቦቹ መታሰር ዙሪያ የሰጡት አስተያየት የለም።

አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ግለሰቦቹ የታሰሩት ከዋልድባ ገዳም እና ከራስ ዳሸን  ጋር በተያያዘ በአካባቢው ከሚታየው ውጥረት ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል። የደባርቅ ወረዳ ወጣቶች ከዋልድባ፣ ከራስ ደጀን እንዲሁም ከመልካም አስተዳዳርና ፍትህ እጦት ጋር በተያያዘ ከአካባቢው ባለስልጣናት ጋር በተደጋጋሚ እንደሚላተሙ ይታወቃል።

 የደባርቅ መምህራን የደሞዝ ጭማሪ ይደረግልን በማለት ተቃውሞ ካሰሙ መምህራን መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው። በጭልጋ ወረዳም እንዲሁም መምህራን የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment