Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Tuesday, June 5, 2012

ግንቦት 20ን ለማክበር 120 ሚሊዮን ብር መውጣቱ ተጠቆመ

By finote Netsanet news, second years, no. 45
ኢህአዴግ 21ኛውን የግንቦት 20 በዓል ለማክበር ከፍተኛ ገንዘብ ማውጣቱን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን ገለጹ፡፡ ምንጮቹ እንደሚሉት ኢህአዴግ በዓሉን ለማክበር ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ አውጥቷል፡፡ ምንጮቻችን አክለውም “በዓሉ በየአባል ድርጅቶቹና በየመሠረታዊ ድርጅቶች እንዲከበር ተደርጓል፡፡

በዝግጅት ላይም የጋባዥና ተጋባዥ ኮሚቴ ተዋቅሮ በጀት ተመድቦ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በዚሁ መሠረት በዓሉ በገንዘብ ብዛትና ለጥቅም ሲባል በተሰበሰቡ ሰዎች እንጂ በዓሉን በእምነት አላከበሩም፡፡” ብለዋል፡፡ 

አያይዘውም በተለይ የኦሮሚያ የግንቦት 20 በዓል የተከበረው በከፍተኛ የገንዘብ ወጪ እንደሆነ ይገልፃሉ፡፡ እነዚህ ታማኝ የዜና ምንጮች እንደሚሉት “ሰዎችን ጋብዞ ላመጣ አንድ ሺ ብር፣ ለፎረም አባል 600 ብር፣ ለቀበሌ ቀስቃሽ 300 ብር፣ ለሰልፈተኛ መቶ ብር እየተከፈለ የተሰበሰበ ነው፡፡

 ለዚሁ ማስፈፀሚያ የሚውል ለኦሮሚያ ብቻ 30 ሚሊዮን ብር መመደቡን” ያስረዳሉ፡፡ እነዚህ የውስጥ አዋቂዎች እንደሚሉት “ግንቦት 20 እንዲከበር ከፍተኛ ገንዘብ ቢወጣበትም ተሰብሳቢዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ሥርዓት እየሆነ በመጣው ሙስና፣ የመልካም  አስተዳደር እጦትና ኦሮሚያ ከሞግዚት አስተዳደር አለመውጣት ቅሬታ ሲያሰሙ ተደምጧል፡፡ እንዲያውም ለሥራ ነው እንጂ ኦሮሚያ መኖሬ፣ የከፋኝ ዕለት እማ ትግራይ ነው አገሬ” የሚል ግጥም ሲነገር መደመጡን በሥፍራው የነበሩት ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡

 በሌላ በኩል ግንቦት 20 በዓል ማለዳ ላይ በመስቀል አደባባይ ለማክበር የተደረገው ጥረት ለመሳካቱን ሪፖርተራችን ዘግቧል፡፡ በዕለቱ እስከ ሦስት ሰዓት ድረስ በመስቀል አደባባይ የነበረው ህዝብ ከ300 ሰው የማይበልጥ ሲሆን እነሱም “አቶ መለስ ይመጣሉ ውጡ ተብለን መተን በፀሐይ ያስደበድቡናል” በማለት ተበሳጭተው ተበትነዋል ሲል ዘግቧል፡፡ መንግስት ለቦንድ ግዢ የሰራተኞችን አቅም ያላገናዘበ የግዳጅ ሽያጭ እያደረገ ባለበት ወቅት ስልጣን የያዘበትን ቀን ለማክበር ለአንድ ቀን ይህን የሚያክል ወጪ ማውጣቱ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

No comments:

Post a Comment