Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Friday, June 8, 2012

በዋልድባ ገዳም አካባቢ ማይጋባ በሚባል ቦታ ላይ በፌደራል ፖሊስና እና በአርሶ አደሩ መካከል በተነሳ ግጭት 15 ሰዎች ተገደሉ


ኢሳት ዜና:- ሰኔ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
 የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ግጭቱ የተነሳው ግንቦት25 ሲሆን፣ የፖሊስ አባላቱ የአካባቢው አርሶአደሮች ቤቶቻቸውን እንዲያፈርሱ ሲጠይቁ አርሶአደሮች ለማፍረስ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተከትሎ በተነሳ ግጭት ነው ፖሊሶችና አርሶአደሮች የተገደሉት።

በተመሳሳይ ዜና ደግሞ በዋልድባ አካባቢ በምትገኘዋ የዛሬማ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች በትናንትናው እለት በርካታ መኪኖችን አግተው ውለዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ከወታቶች ጋር በፈጠሩት ግጭት በርካታ ወጣቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከ60 በላይ ወጣቶች መታሰራቸውንም ለማወቅ ተችሎአል።

በሌላ በኩል ደግሞ የኢህአዴግ በዋልድባ ጉዳት ከአባላቱ ጋር ሳይቀር ውዝግብ ውስጥ ገብቷል። ግንባሩ ያስታጠቃቸው ሚሊሺያዎች ሳይቀሩ በዋልድባ ገዳም ላይ የሚፈጸመውን በደል በመቃወማቸው፣ ግንባሩ ታጣቂ ሚሊሻዎች ትጥቅ እንዲፈቱ አዟል።  በጫራዱቃ  ቀበሌ  8 ታጣቂ ሚሊሺያዎች ብቻ ትጥቅ ሲፈቱ ሌሎች አንፈታም በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል።

 ከዋልድባ ጋር በተያያዘ በአካባቢው ያለው ውጥረት እንዳለ ነው። ሰኔ 21 በሚከበረው የቅድስት ማርያም በአል ላይ ግጭት ሊፈጠር ይችላል በሚል የፌደራል ፖሊስ አባላት በአካባቢው ከፍተኛ ቅኝት እያደረጉ ነው።

No comments:

Post a Comment