Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Sunday, June 3, 2012

በአፋር ክልል ያለው ችግር ተባብሶ መቀጠሉ ታወቀ

ኢሳት ዜና:-
የአፋር ተወላጆች ለኢሳት እንደገለጡት በክልሉ ያለው ችግር መባባስ ህዝቡ ሰላማዊ ኑሮውን እንዳይገፋ አድርጎታል።  በዞን አንድ እና ዞን 3 በተባሉት አካባቢዎች መንግስት ነዋሪዎችን በጉልበት እያፈናቀለ መቀጠሉን  በዞን ሁለት ደግሞ የማእድን ዘረፋው የችግሩ ምንጭ መሆኑን  የአፋር ህዝብ ጋድሌ ሰራዊት ዋና አዛዥ የሆኑት ኮሎኔል ሙሀመድ አህመድ ለኢሳት ገልጠዋል::

ኮሎኔል ሙሀመድ እንዳሉት ለስኳር ፋብሪካ በሚል አካባቢው እንዲራቆት እየተደረገ በመሆኑ ህዝቡ ተቃውሞውን እያሰማ ነው:: የአፋር ክልል መንግስት ለህዝቡ ምንም ሊፈይድ እንዳልቻለ ኮሎኔሉ ይናገራሉ::

በዛሬው እለት ተፈጠረ ስለተባለው ግጭት ለማረጋጋጥ ወደ አካባቢው በተደጋጋሚ ብንደውልም የስልክ መስመር ለማግኘት አልተቻለም። መንግስትም በጉዳዩ ዙሪያ የሰጠው አስተያየት የለም።

No comments:

Post a Comment