Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Tuesday, April 24, 2012

“አሁንስ መንግስቱን መንግስቱን መሰልከኝ!”

አቤ ቶኪቻው 
በወዳጃችን ዳንኤል ተፈራ የተሰናዳው “ዳንዲ የነጋሶ መንገድ” የተሰኘው መፅሀፍ ላይ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በአንድ ስብሰባ ላይ አቶ መለስ ዜናዊ እነ ስዬን አጓጉል ሲዘልፏቸው ይሰማሉ። (ምን እያሉ…? ይበሉ እንጂ…) ምን የማይሉት አለ ብዬ እቀጥላለሁ፤  “አፈንጋጮቹን ጃኬታቸውን አስወልቀን ሸኝተናቸዋል።” በማለት ይናገሩ ነበር። ይሄኔ ዶክተር ነጋሶ ሆዬ መንጌ በአንድ ወቅት ጀነራሎቹን “ማዕረጋቸውን አስወልቀን ቂጣቸውን በሳንጃ ወግተናቸዋል” ያለው ትዝ አላቸው… ትዝ ብሏቸውም ዝም አላሉም አቶ መለስን ትኩር ብለው እያዩ “አሁንስ መንግስቱን መንግስቱን መሰልከኝ!” ብለው እርፍ።

እዝች ጋ ከሁሉ ያሳቀኝ ምን እንደሆነ ያውቃሉ የወ/ሮ ገነት ዘውዴ ነገር፤ “እንዴት መለስን ከመንግስቱ ጋር ታመሳስለዋለህ” ብለው እዛው ስብሰባ መሃል ስቅስቅ ብለው አላለቀሱም መሰልዎ…? ያኔ ወ/ሮ አዜብ በስብሰባው ላይ መኖራቸውን እንጃ፤ ቢኖሩ ግን ወ/ሮ ገነትን ዝም የሚሏቸው አይመስለኝም።

ሳስበው ወደ ዶክተር ነጋሶ ዞር ብለው “እርስዎ ቆይ እንነጋገራለን… አንቺ ግን ምን ቤት ነሽ እንዲህ የምትነፋረቂብኝ…” ካሉ በኋላ፤ ወደ አቶ መለስ ደግሞ ዞረው፤ “ስማ እንጂ አንተ የጀመራችሁት ነገር አለ እንዴ…? እዛች ቤት እንገናኛታለን!” ብለው ሲያመናጭቋቸው አሁንም ያው ወ/ሮ ገነት መቼም አያስችላቸውም እንባ ሳይተናነቃቸው አይቀርም። ይሄኔ… “አላበዛሽውም እንዴ…!?” እየተባባሉ በስሊፐር ሲጠፋጠፉ ይታየኝ ነበር።

እኔ የምለው ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ግን የት ጠፉ? በነገራችን ላይ ከባለቤታቸው ጋር እንዴት እንደተፋቱ ሰምተዋል…? ቆይ ልንገርዎትማ… ባለቤታቸው ከኢህአዴግ አመራር አባላት መካከል ነበሩ። ታድያ ሲያስቡት ሲያስቡት የኢህአዴግ ነገረ ስራው ምንም አልጥም አላቸው። እናም “በቃኝ ከእንግዲህ አባልነቱ ይቅርብኝ እና በባልነቱ እንቀጥላለን” ብለው አማከሯቸው። ታድያ ወ/ሮ ገነት ሆዬ ምን አሉ መሰልዎ… “ከኢህዴግ ጋር ተፋቶ ከእኔ ጋር መኖር አይቻልም ልጅነቴን የሰጠሁት ባሌ ድርጅቴ ነው። ከድርጅቱ ከወጣህ ከቤቴም ትወጣልኛለህ… መንገዱንጨርቅ ያድርግልህ” ብለው አሰናበቷቸው። (እውነትም ወ/ሮ አዜብ መጠራጠር አለባቸው… ብለው ግፍ እንዳይናገሩ ወዳጄ…!)
እናልዎ አንዳንድ ተናግሮ አናገሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ዛሬ ዶክተር ነጋሶ አቶ መለስን “አሁንስ መንግስቱን መንግስቱን መሰልከኝ” ብለው ቢናገሩ እንደዛን ግዜ ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ብቻ ሳይሆኑ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ስቅስቅ ብሎ ያለቅስ ነበር ይሎታል። 

እንዴት ያላችሁ እንደሆነ “መንጌ ምን በደለን እና ከመለስ ጋር ያመሳስሉታል?” ብለው ይመልሳሉ።
ለነገሩ ይሄም ተጋኗል። እኔ ይቅርታ አድርጉልኝና መለስ ከመንግስቱ የበለጡ እርኩስ ናቸው ብዬ አላምንም። ይልቅስ መቼለታ አየር ሃይል ሰልጣኞቹን ሲያስመርቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር አድርገው ነበር። ታድያ ወደመድረክ የጋበዛቸው ሰውዬ ምን ብሎ እንደጠራቸው ያውቃሉ…? “የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ አቶመለስ ዜናዊ…” በእውነት ክው ነው ያልኩት ቁርጥ መንግስቱን መሰሉኝ። ለነገሩ ባለፈው ግዜ ተመስገን ደሳለኝ እንደዘረዘረልን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የያዙት ስልጣን መንጌ ይዘውት ከነበረው ይበልጥ እንደሁ እንጂ አይተናነስም።

ከሁሉ ከሁሉ ግን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን አሁን በተለይ ኮሎኔር መንግስቱን ስናብጠለጥልባቸው የነበሩ ነገሮችን በሙሉ እያሟሉ ይገኛሉ። እንደ እግዜር ፈቃድ በቅርቡ ሚኒማውን በሙሉ አሟልተው ቁርጥ መንግስቱን የሚሆኑ ይመስለኛል። በየእስር ቤቱ ያለውን ገረፋ እና ስቃይ አናነሳም… ገብስ ገብሱን ለማንሳት ያህል፤ ለምሳሌ ነፃ ፕሬሱ ላይ የተጋረጠው ነገር፣ ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ላይ እደረሰ ያለው፣ የሙያ ማኅበራት እየሆኑ ያሉትን በሙሉ ስናይ “አሁንስ መንግስቱን መንግስቱን መሰልከኝ” የሚባሉበት ትክክለኛው ግዜ ላይ እየደረሱ ይመስላሉ። ቀለል ያለ ቋንቋ መጣችልኝ… እንደውም ከአይን ያውጣቸው እንጂ አቶ መለስ ዜናዊ ለአቅመ መንግስቱ ኃይለ ማርያም ደርሰዋል! ብንል የተሻለ ሳይሆን አይቀርም።

የምር ግን ወዳጄ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይ አሁን አሁን ጥያቄ ሲጠየቁ ቆጣ ቆጣ ማለታቸውን ስታዩ “ይሄንን ቁጣ የት ነበር የማውቀው?” ብላችሁ ድንገት መንጌ ትውስ አይሏችሁም። የምሬን እኮ ነው… እውነቱን ለመናገር አቶ መለስ ከመንጌ የሚለዩት “ኢትዮጵያ የኛ መመኪያ” ሲባል ልባቸው ድንድጥ አለማለቱ፣ ባንዲራ ገልብጠው በየ ሰዉ አገር መታየታቸው እና የአክሱም ሀውልት ለደቡብ ምኑ ነው በሚለው ፍልስፍናቸው ካልሆነ በስተቀር ከመንጌ ምንም አይተናነሱም። እሰይ የኔ አንበሳ! አይሏቸውም እንዴ!?

ምስጋና
ለፌስ ቡክ ወዳጄ ቤዚ ቢል ይህንን ፎቶ “ታግ” አድርገህ ለዚህች ጨዋታ አነሰሳስተኸኛልና! ምስጋና ይገባሃል።

Massive Theft of Developing World’s Farmland


By Julio Godoy, Source: IPS
The mass acquisition or lease of arable Farmland in developing countries, especially in Africa, by foreign investors – a practice aggravated by the outbreak of the financial crisis in 2007 – has reached record highs, according to several new studies. 

A study by the Spain-based group Genetic Resources Action International (GRAIN), released late February, estimates that some 35 million hectares of land have been sold or leased in 416 recent, large-scale land grabbing deals in 66 countries, mostly in Africa.
Another analysis of land grabs, carried out by the International Land Coalition (ILC), released last January, found that between 2000 and 2010 some 203 million hectares were leased or sold in developing countries, mainly in Africa, but also in Latin America, Asia, and even Eastern Europe, to foreign investors.
“This land area is equivalent to over eight times the size of the United Kingdom,” the ILC said in its report ‘Land Rights and the Rush for Land – Findings of the Global Commercial Pressures on Land Research Project.’
Most land is used to produce inputs for so called biofuels, ILC pointed out. In his new book on the subject, award-winning Italian journalist Stefano Liberti says that this massive global land grab is the direct consequence of the privatisation and liberalisation policies imposed for years upon developing countries by international financial institutions such as the World Bank (WB) and the International Monetary Fund (IMF), and investment in agricultural policies promoted by United Nations agencies such as the Food and Agricultural Organisation (FAO).

The book, published originally in Italian under the title ‘Land Grabbing: How the market for land is creating a new colonialism’, was released in German on Apr 18, with English and Spanish editions under way.
Liberti told IPS that most governments in developing countries affected by land grabbing are also accomplices in the process.

“In many African countries in particular, land belongs to the state,” Liberti said. “Governments are dealing secretly with investors, to lease or sell enormous areas of the best arable land. Local farmers who don’t own the land they work are informed of these deals at the very last moment, when they are told to leave,” Liberti said.
During the preparation of his book, Liberti travelled across Africa, and attended numerous seminars and sessions of international institutions, such as the FAO and the WB, and participated in workshops organised by small farmers’ organisations around the world.

Liberti said that the most spectacular cases of land grabbing he came across were in Ethiopia. “This country has been suffering from famine for decades, due to armed conflicts and droughts. And yet, it has been leasing or selling its best land to foreign investors for almost nothing at all to produce food or inputs for biofuels to be consumed abroad,” Liberti said.

In his book, Liberti illustrates the case of an Indian company, which leases 300,000 hectares of Ethiopia’s best arable land for one dollar per year per hectare, to produce wheat, palm oil, and sugar for mostly Indian consumption. “Ethiopians have almost nothing from this deal,” Liberti said. “The company pays extreme low salaries to its Ethiopian workers, almost nothing for the land, enjoys tax breaks for the import of technology, and on top of that uses the country’s water for free.” 

Indeed, the Ethiopian Investment Agency, the state office administering foreign direct investment (FDI), praises the country’s labour costs as “relatively low compared to the African average.” According to Liberti, foreign agricultural industries in Ethiopia pay their workers less than a dollar a day. The Ethiopian case is typical of the land grabbing phenomenon across the developing world. In a recent case in Algeria, the Abu Dhabi-based Al Qudra Holding obtained concessions for 31,000 hectares of agricultural land, on which it intends to produce potatoes, olives and dairy products, all for export.

The company is also planning similar land leasing investments in Morocco, Pakistan, Syria, Vietnam, Sudan and India to increase its land holdings to 400,000 hectares. Liberti said that holdings such as Al Qudra, and investment funds, including pension funds, are the main actors in the global land grab. “The international financial sector discovered some five years ago that it can earn substantial amounts of money by speculating with food stuffs,” he said.

Holdings and sovereign wealth funds, which manage the currency reserves of many Arab and other strong, emerging economies also invest massively in land grabbing, to guarantee food supply in their home markets.
According to estimations by GRAIN, “Pension funds currently juggle 23 trillion dollars in assets, of which some 100 billion are believed to be invested in commodities.”

Of this money in commodities, five to 15 billion are reportedly going into farmland acquisitions. “By 2015, these commodity and farmland investments are expected to double,” GRAIN estimated last year. Liberti said that international institutions such as the WB and the FAO are accomplices in the land grab. “The FAO used to say that agriculture needed massive private investment to improve efficiency. The WB and the (IMF), for their part, promoted privatisation and liberalisation of food markets, and gave impulse to land grabbing.”

“The WB has even lent money and provided insurance to investment funds taking part in land grabbing,” Liberti added. Yet another driver of the land grab is an explosion in the use of so-called biofuels. As the ILC report points out that of all the many deals resulting in land theft, “Seventy-eight percent are for agricultural production, of which three-quarters are for biofuels.” Mineral extraction, industry, tourism, and forest conversions are also significant contributors, adding up to the remaining 22 percent.

ILC Director Madiodio Niasse told IPS that governments in developing countries must “understand that there are alternative investment models that do not necessarily involve them giving away their land.” Niasse, a Senegalese national, has been the director of ILC since 2005. He told IPS that it is essential for African governments to conceive “their own rural development strategies to serve their national priorities and the interests of their people.”

“During my research trips in Africa, I came across posters against the land grab deals,” Liberti told IPS. “One said: ‘Future generations will damn your graves, because you did not leave them any land.’” To avoid this future, Liberti stressed, “An efficient agricultural model, an alternative to the agro- industrial (framework) in practice now, must be developed for Africa, Latin America, and Asia.”

Foreign investment in agriculture was invited based on the misguided assumption that it would help local communities; now, “the opposite is actually happening.”“The alternative is to support local farmers by teaching them modern methods of sustainable agriculture, and providing infrastructure for irrigation, storage, transportation, and technical inputs,” Liberti concluded.

Monday, April 23, 2012

ሰማያዊ ፓርቲ እስከ አሁን ፈቃድ አላገኘም

ኢሳት ዜና:-
በወጣቶችና በምሁራን የተገነባው አዲሱ ሰማያዊ ፓርቲ እስከ ዛሬ ፈቃድ ሊያገኝ አልቻለም። ከምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የፓርቲው መስራቾች በቦርዱ የታዘዙትን መስፈርቶች ሁሉ ቢያሙዋሉም፣ የቦርዱ አባላት ግን ፈቃዱን ሊሰጡዋቸው አልቻሉም።

አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የድርጅቱ ሰራተኛ ለኢሳት እንዳሉት፣ ፓርቲው በመላ አገሪቱ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ፊርማዎችን አሰባስቦ ለህዝብ ይፋ ማድረጉ ቢረጋገጥም፣ የቦርድ አባላት ግን ከመንግስት አቅጣጫ አልመጣልንም የሚል ምክንያት በማቅረብ ፣ ፈቃዱን ሊሰጡዋቸው አልቻሉም። የመንግስት አቅጣጫየሚባለው ፣ ከኢህአዴግ ጽህፈት ቤት የሚሰጠው ይሁንታ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ታዋቂ ምሁራን ለፓርቲው አባላት ትምህርቶችን እየሰጡ ነው። በቅርቡ ረዳት ፕሬፌሰር ዝናቡ አበራ በኢትዮጵያ ውስጥ በየ14 አመቱ የልውጥ እንቅስቃሴ እንደሚኖር ለፓርቲው አባላት ትምህርት ሰጥዋል። በሚቀጥለው ሳምንት ደግሞ ኢኮኖሚስቱ ዶ/ር በፈቃዱ ደገፌ ለወጣቶች ትምህርት እንደሚሰጡ ለማወቅ ተችሎአል። የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ፈቃድ በመከልከላቸው ዙሪያ ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።

የኢትዮጵያ መንግስት መጠላቱን የሚያሳብቁ ምልክቶች



እንደግለሰብየምንጠላቸውን እንጂ የሚጠሉንን የማወቅ ዕድላችን ጠባብ ነው፡፡ እንደመንግስት ግን ጠባብ አይደለም፤ ሆኖም መንግስታቱ አምባገነንከሆኑ በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች ጥላቻቸውን የሚገልጹበት ድፍረት አያገኙም ስለዚህ እንደተጠሉ ላያውቁ ይችላሉ የሚል የግል ስጋት አለኝ፡፡ፊደል ካስትሮ በስልጣናቸው ዘመን፣ በሕይወት ታሪካቸው ላይ የተሰራውን ፊልም ሕዝቡ በምን ዓይነት የፍቅር ስሜት እንደሚመለከተውለማየት ራሳቸውን ቀይረው ሲኒማ ቤት ገቡ አሉ፡፡ 
 
እናም ገና ፊልሙ እንደጀመረ የፊደል ካስትሮ ፊት መታየት ሲጀምር ተመልካቹ በሙሉቆሞ አጨበጨበ፡፡ እርሳቸው በደስታ እየፈነደቁ ፀጥ አሉ፡፡ ታዲያ ከጎናቸው ተቀምጦ የነበረው፣ ‹‹አንተ፤ እየተነሳህ አጨብጭብ እንጂ!ካድሬዎቹ ያዩሃል’ኮ›› አላቸው ይባላል፡፡ ስለዚህ የኛዎቹም ይህ ዓይነት ቅዠት ውስጥ ሊሆኑ ስለሚችሉ÷ ሕዝብ እንደጠላቸው የሚያሳብቁአንዳንድ ነገሮችን እናስታውሳቸው፡፡

1. የጋዜጦች አቋምና የስርጭት ብዛታቸው ጉዳይ
አገራችን በሕገመንግስቷ‹ሐሳብን በነፃ የመግለፅ› መብት እንዳስቀመጠች ቢነገርላትም ‹‹ነፃ›› የሚለው እስከምን ድረስ እንደሆነ አጠራጣሪ እውነታዎች እየተከሰቱነው፡፡ መንግስትን የሚነቅፉ ጋዜጦች እና ጋዜጠኞች ወይ ይታሰራሉ አሊያም በስደት አሳራቸውን ያያሉ፡፡ በዚህ ሁሉ መሃል ግን ‹የሚነቀፈውንለመንቀፍ› በሚል የተቋቋሙት ጋዜጦች ቀርቶ ለወትሮው በውበት፣ ፋሽን፣ ፍቅር እና ጤና ጉዳዮች ላይ ብቻ ያጠነጥኑ የነበሩ መጽሄቶችሳይቀሩ ፖለቲካ እንደቅመም ይዘው መውጣት ጀምረዋል፡፡

አንድ ሰሞንቴዲ አፍሮን የሽፋን ገጽ ላይ ይዞ መውጣት የመጽሄቶች ሕልውና እንደነበር ይታወሳል፡፡ አሁን ደግሞ መንግስትን የሚነቅፍ ጽሁፍ ይዞመውጣት ለተነባቢነት ሁነኛ መፍትሄ ሆኗል፡፡ የፍትሕ ጋዜጣ ኮፒ መመንደግ ከዚሁ ከመንግስት መጠላት እና የፍትሕ ጋዜጠኞችም መንግስትንየመንቀፍ ድፍረት ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነት አለው፡፡

2. ፌስቡክ እና ጦማሮች
አግኝተውትየማያውቁትን ወዳጅ ፍለጋ ፌስቡክ ውስጥ ከሚገቡ ኢትዮጵያውያን ይልቅ ስለወቅታዊ ጉዳዮች ‹ማን ምን አለ?› የሚለውን ፍለጋ የሚገቡትብዙ ናቸው፡፡ በተለይም ከዓረቡ ዓለም የፌስቡክ አብዮት ወዲህ የአገር ልጆች ፌስቡክም በአብዮት ናፍቆት እየተናጠ ነው፡፡ ፌስቡክውስጥ መሪዎቻችንን መሳቂያ፣ መሳለቂያ የሚያደርጉ ምስሎችን ማየት፣ እያንዳንዷን የመንግስት እርምጃ የሚተቹ ጽሁፎችን ማንበብ የተለመደነው፡፡

በተጨማሪምበርካታ ጦማሪዎች የግል ጦማር (blog) እየከፈቱ የግል አስተያየታቸውን መሰንዘር ጀምረዋል፡፡ በዙዎቹ ጦማሪዎች በአገራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ሲሆኑ÷ መንግስትን በአለንጋ ትችቶቻቸው ከመሽንቆጥ የማይመለሱ ናቸው፤ ለማወደስየተቋቋሙ ጥቂት ጦማሮች ቢኖሩም ባብዛኛው በአንባቢ ድርቅ የሚሰቃዩ ናቸው፡፡

3. የቴዲ አፍሮ ክብረወሰን
በኢትዮጵያሕዝብ ልቦና ውስጥ ቴዎድሮስ ካሣሁን ያለው ቦታ የዘፋኝነት ብቻ ሳይሆን የአርበኝትም ጭምር ነው፡፡ ቴዲ አፍሮ በአጋጣሚ የሚናገራትምሆነ በግጥሙ ውስጥ የሚያስቀምጣት ሐረግ ፖለቲካዊ ፍቺ ይሰጣታል፡፡ የዘንድሮው አልበም ገበያም የደራው እና 10 ሚሊዮን ብር በመሸጥየሃገር ውስጥ ክብረወሰን ለመስበር የበቃው÷ ሕዝብና አጋጣሚ በቸረው የመንግስት ተፃራሪ አቋሙ ነው፡፡

የቴዲ አፍሮ‹ጥቁር ሰው› የተሰኘ አልበም ጥሩ እንደሆነ ሊያስረዱኝ ይሞክሩ ከነበሩ ሰዎች መካከል ይጠቅሱልኝ የነበረው ‹ጥቁር ሰው› እና‹ስለ ፍቅር› የተባሉትን ዘፈኖች ነው፡፡ ስለፊተኛው ‹‹ምኒልክ መወደሳቸው የኅወሓት ሰዎችን አንጀት ያሳርራል›› በሚል፣ ስለኋለኛውደግሞ፡-
‹‹… አፈር ይዞ ውስጡ አረንጓዴ
     ለምን ይሆንየራበው ሆዴ?....›› የሚለውን ግጥም ይጠቅሱልኛል፡፡

እንግዲህ የቴዲአፍሮ ተወዳጅነትም የሚያረጋግጠው የመንግስትን መጠላት እንደሆነ መፍረድ ቀላል ነው ማለት ነው፡፡

4. የጀማሪ አባሎች ስጋት
ኢሕአዴግ ሰባትሚሊዮን አባላት እንዳሉት ይናገራል፡፡ በርግጥ የአባላት ብዛት የተደጋፊነትን ብዛት እንደማያረጋግጥ (በምርጫ 97) ያረጋገጠው ብቸኛየዓለማችን ፓርቲ ኢሕአዴግ ራሱ ይመስለኛል፡፡ ሆኖም በአባሎቹ ቁጥር ብዛት ሲቪውንና ደረቱን ለማሳበጥ ከመሞከር አልተቆጠበም፡፡ይህ በእንዲህ እናዳለ ምናልባት ሥራ ከተገኘ፣ ምናልባት ሹመት ከተገኘ፣ ምናልባት ነፃነት ከተገኝ፣ ምናልባት ምናምን ከተገኘ ብለውበየወሩ የአባልነት መዋጯቸውን በምናልባት የሚገፈግፉ አባላት÷ አባልነታቸውን በምስጢር መያዝ ይወዳሉ፡፡ መረጃ አፈትልኮ የታወቀባቸውዕለት እንኳን የሚዘባርቁት ምክንያት የገዢው ፓርቲ አባልነት ማሕበራዊ ነውር የሆነ ያስመስለዋል፡፡

ይሄ ሁሉ የሆነውየሆድ ነገር አባል ያደረጋቸው ዜጎች ከተጠላው መንግስት ተርታ ተሰልፈው ከወገናቸው ወዲያ እንዳይመደቡ በመስጋታቸው ነው፡፡

5. ኢቴቪዮጵያ
የኢሕአዴግመንግስት ሁሉንም የመንግስት ሚዲያዎች የፓርቲ ልሳን ቢያደርጋቸውም እንደኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ግን በየቤቱ እያንኳኳ የሚገባ ደፋርየለም፡፡ ምን አስቦ እንደሆነ ባይታወቅም (በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ) ከነጋዴው፣ ከመምህሩ፣ ከክርስቲያኑ፣ ከሙስሊሙ… ከተገኘውሁሉ ጋር በመቀያየም ላይ አትኩሮ እየተንቀሳቀሰ ያለው ኢሕአዴግ በኢቴቪ የሚያቀርባቸው የፕሮፓጋንዳ ዶኩመንተሪዎች የታለመላቸውንያህል ውጤት በማስመዝገብ ፈንታ ለቴሌቪዥኑ ቅጽል ስሞችን አፍርተውለታል፡፡

በኢቴቪ በኩልመንግስት ‹እንዲህ አደረግኩላች› ሲል÷ ‹እንዲህ አደረግኳችሁ› እንደማለት፣ ‹እንዲህ አደረጓችሁ› ሲል ደግሞ ‹እንዲህ አደረጉላችሁ›ያለ ይመስል በተቃኒው ይተረጎምበታል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ነገርን ጠምዝዞ የመተርጎም ልምድ ያፈራው ከኢሕአዴግ ቴሌቪዥን(ኢቴቪ) ወዲህ ነው፡፡ የዚህ ሁሉ አንድምታ ከጠሉት መንግስት እውነት የራስ ውሸት ይሻላል የሚል ነው፡፡

መደምደሚያ፡- የኢትዮጵያመንግስት ተጠልቷል፡፡ በርግጥ ይህንን መንግስት እያወቀ ችላ የሚልበት ደረጃ ላይ ደርሷል ማለት ነው፣ ምናልባትም ደግሞ መንግስትምየኢትዮጵያን ሕዝብ ስለሚጠላው የተለየ ነገር አይጠብቅ ይሆናል፣ ምናልባትም ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ጥሩ ነገር ተሳክቶልኝ ሰርቼእክሳቸዋለሁ ብሎ አስቦ ይሆናል፡፡ የመንግስት ፍላጎት ምንም ቢሆን ምን የሕዝቡ ጥላቻ ግን የሚያመለክተው ለውጥ እየፈለገ እንዳጣብቻ ነው፡፡

ፍጥረታዊ ፍትሕ ወይስ ዘረኛ ፍርደገምድልነት?

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
(ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)
 
  ወንጀለኛ!
ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ የመርገጫ ማህተም የሆነውን ፓርላማ ግፈኛው ፈላጭ ቆራጭ መለስ ዜናዊ ተገደው ከደቡብ ኢትዮጵያ  ‹‹የተፈናቀሉትን›› የአማራዎች (አንዳንዶች‹‹በተንኮል ዘዴ ዘር ማጥፋት›› ብለውታል) በተመለከተ፤ በጉዳዩ ላይ ተቃውሞ ያሰሙትንና ፤ ዜናውን እንዲሰራጭ ያደረጉትን፤ በደፈናው ሃላፊነት የሌላቸው በማለት በማዉገዝና እውነቱን ሸምጥጦ በመካድ ጨርሶ መፈናቀል እንዳልተካሄደ ለማሳመን ሲፈላሰፍ ታይቷል፡፡  መለስ  ስለመፈናቀሉ  ማሳሳቻውን ማስረጃ ሲያቀርብ አንዳችም መፈናቀል ያልተካሄደ በማስመሰል  አንዳንድ  ሕገወጥ ከሰሜን ጎጃም የፈለሱ (‹‹ሰፋሪዎች›› ይላቸዋል) ከደቡብ መኖርያቸው የተነሱበት ምክንያት ቦታው የአካባቢ ደንና ፊጥረታዊ  ሃብት ጥበቃ ነው ሲል ሊሞግት ሞክሯል፡፡ እንዲያውም ለምን ያሉትንና የጋራነት መታወቂያችን ኢትዮጵያዊነት ነው በማለት የቆሙትን ድርጅቶች በተመለከተ፤ መለስ በጠራራ ጸሃይ ሲሰብክ:
….. ባለፉት አሰርት ዓመታት በታሪክ አጋጣሚ፤በርካታ ሰዎች፤… ወደ ሰላሳ ሺህ የሚጠጉ ሰፋሪዎች፤ ከሰሜን ጎጃም (የፈለሱ) በቤንጅ ማጂ ዞን (በደቡብ ኢትዮጵያ)ሰፍረዋል፡፡ በጉራ ፈርዳ 24.000 ሰፋሪዎች አሉ፡፡ ቦታው ጫካማ ስለሆነ ብዙ ሰው አይኖርበትም፡፡በተለያየ ሰበብና አጋጣሚ ሁሉም የድርሻውን ያገኛል የሚጎዳ አይኖርም፡፡እነዚህ ህገወጥ ሰፋሪዎች ባልተቀናጀ መልኩ ነው የሰፈሩት፡፡ እነዚህ ህገ ወጥ ሰፋሪዎች በተናጠልና በተመሰቃቀለ መንገድ፤ የአካባቢውንም የዓየር ሁኔታ በሚበክል መልኩነው የሰፈሩት፡፡ይህ ደሞ አጥፊና ጎጂ ነው፡፡
ሰፈራው የአካባቢውን ዓየር ሁኔታ ባገናዘበ፤ የጫካውን መጥፋት ከግንዛቤ ባስገባ መልኩ ታስቦ የተከናወነ አይደለም፡፡ድንግል የሆነው ጫካ መጠበቅ አለበት፡፡ሰፋሪዎቹበቀላሉ ሊለማ የሚችልና አፍሪ ቦታ ነው የፈለጉት፡፡ደን ሆነ አልሆነ ደንታ የላቸውም፡፡ደኑን እየጨፈጨፉ ለኑሮ የሚያስፈልጋቸውን ከሰል ያከስላሉ፡፡ በዚህ የተነሳም በርካታየአካባቢ ብክለትና ጉዳት ተፈጽሟል፡፡…… ሰፋሪዎች ወደፈለጉበት ቦታ ሄደው በመስፈር የአካባቢውን ደን በማጥፋት መኖር አይችሉም፡፡ሕገ ወጥ በመሆኑ ሊቆምይገባዋል፡፡ ይህን እውነታ ለማጭበርበር የሚጥሩ ሁሉ ሃላፊነት የጎደላቸው ናቸው፡፡ ዕውነትን አጥርቶ ማየት ያስፈልጋል፡፡የሁሉም ኢትዮጵያዊያን መብት በእኩል ደረጃሊጠበቅ ይገባል፡፡ አማሮች ተፈናቀሉ ለስደት ተዳረጉ በማለት የሚጮሁት ማንንም የማይጠቅም ቅስቀሳ ነው በማድረግ ላይ ያሉት፡………..
መለስ በቀላሉ ሲያስቀምጠው፤ እነዚህ ‹‹የሰሜን ጎጃም ሰፋሪዎች›› የአካባቢውን የደን ሁኔታ ያጠፉ ወንጀለኞች ናቸውና ተገደው መነቀልና መሰደድ አለባቸው፤ እንዲያውም በወንጀል ባለመጠየቃቸው እድላቸውን ሊያመሰግኑ ይገባል፡፡ የአፍሪካ የከባቢ ዓየር ዋና ሹም ስለአካባቢ ዓየር ሲነሳ በአፍሪካ ካሉት ከማንኛቸውም በበለጠ እውቀትና  ችሎታ ያለው ሰው ቢፈለግ ከመለስ ሌላ ጨርሶ የት ሊገኝ?! ምንስ ቢሆን የአፍሪካ ዋና የከባቢ ዓየር መኮንን ተብሎ የለም እንዴ!   በ2009 መለስ በኮፕንሃገን በተካሄደው ስብሰባ ላይ የአፍሪካዊያንን ተደራዳሪዎች በመምራት ተገኝቶ ነበር፡፡  በዚህ ቦታ የአፍሪካ ተደራዳሪዎች መገኘት መንስኤውም፤የምእራቡ ዓለም እያጠፋና እያዛባ ያለውን የተፈጥሮ ዓየር፤ ደግሞም የተከተለውን የአየር ለውጥ፤በዓለም የሙቀት ሁኔታው መባባስን፤እና ሌላውንም በተመለከተ የሞራል ካሳና የገነዘብ መቀጫ ለመጠየቅ ነበር ዘራፍ ብሎ የተነሳው፡፡ በዚህም 40 ቢሊዮን ዶላር ካልተፋ ስብሰባውን  እንደሚያጨናግፈው ረግጦ እንደሚወጣ ደንፍቶ ነበር፡፡
እኛ በአናሳው የምናቀርበው ስምምነት ተቀባይነት ካጣ፤ ቁጥራችንን በመጠቀም ውሳኔው  ውድቅ እንዲሆን እናደርጋለን…….እንዲያውም አካሄዳቸውና ውሳኔያቸውአህጉራችንን አስገድዶ የሚዳፈር ከሆነ ስብሰባውን ረግጠን እንወጣለን፡፡……..ከዚህ ቀደም ይደረግ እንደነበረው የአፍሪካ ፍላጎትና አቋም ሊታፈን አይችልም አይገባምም፡፡……. አፍሪካ፤የአፍሪካ ሕብረት አባላትን ሀገራት የሚወክልና ሙሉ ስልጣን ያለው አንድ ብቸኛ ተደራዳሪ ቡድን ትሰይማለች፤…. ለኔ ዋነኛው ቁልፍ ጉዳይ፤አፍሪካ የዓለምን አየር መዛባት አስመልክቶ በተፈጠረው ጉዳት ልትካስ ተገቢ ነው፡፡ በርካታ ኢኒስቲቲዩሽኖች ይህን በቁጥር ለማስቀመጥ ሞክረው የተለያየ ተመን አስቀምጠዋል፡፡ከዚህ በመነሳትም ማእከላዊው ቀመር በዓመት 40 ቢሊዮን ዶላር ይሆናል፡፡
ስብሰባው በተጀመረ በማግስቱ ፤ መለስ ከ‹‹አፍሪካ አስገድዶ ደፋሪዎች›› ጋር በ10 ቢሊዮን ዶላር ውለታ ለመፈጸም ስምምነት ለማድረግ ዝግጁ ሆነ፡፡ አፍሪካውያን ወንድሞቹንም ጥሬ ብር ከአርቲ ቡርቲ ቃላት ይሻላል በማለት አሳመነ፡፡
……እርግጥ ይሄ የኔ ሃሳብ ምናልባትም ከሕግ አኳያ ለደረሰብን በደልና ጥፋት፤ በልማታችን ላይ ለደረሰብን በደል ሙሉ ካሳ ይገባናል በማለት ሃሳብ ያቀረቡትንአፍሪካውያንን ቅር ሊያሰኝ ይችላል፡፡ የኔ ሃሳብ ቀስ በቀስ ወደ ተነሳንበት ቁጥር ያደርሰናል፡፡ ይህን ፈንድ መቆጣጠርና በዚህም የአስተዳደር ስልጣን ማግኘትና በወሳኝነት መቀመጥ ዋነኛ መሳርያችንና አስተማማኝ የፋይናነስ ፍሰት ማግኛችን ነው፡፡
በኦክቶበር 2011 መለስ በአፍሪካ ኤኮኖሚ ኮንፍራንስ ላይ ተገኝቶ ባደረገው ንግግር፡-
……..በአህጉራችን ያለው መሬት፤ከመሬቱ መሳሳትና ከማለቁ የተነሳ ዛፎቹ ሁሉ ወድመዋል፤በአፈሩ መሸርሸር፤ለድርቅና ለጎርፍ፤በዓለም ላይ በመከሰት ላይ ባለው የዓየርመዛባት ሳቢያም ከዚህ ቀደም ታይቶ ወደማይታወቅ የጎርፍና የድርቅ ሁኔታ ተዳርገናል፡፡የአርሻዎቻችን መሰረትም እጅጉን አስፈሪ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው፡፡
ስለዚህም በመለስ አተማመን ወደ አውሮፓውያን አስገድዶ ደፋሪዎቻችን በመመለስ በድጋሚ ተጨማሪ የገንዘብ ካሳ ማግኘት ይኖርብናል፡፡ በኢትዮጵያ የመለስ ዜናዊ ፍጥረታዊ ተሰጥኦዎችi ተንከባካቢነት በአፍሪካ የዓየር ለውጥና የዓለምን የሙቀት ሁኔታ በተመለከተ መለስ ዜናዊ አዋቂ የሚል የለበጣ ስያሜ አግኝቷል፡፡ ይሁንና ግን በኢትዮጵያ ውስጥ በመካ ሄድ ላይ ስለአለው የአካባቢ ብክለት፤በተለይም በኢትዮጵያ የደኖችን መጨፍጨፍና መጥፋት በተመለከተ ግንዛቤ አለውን? የኢትዮጵያ የእርሻ ምርምር ኢኒስቲቲዩት (በሃገሪቱ ያለው ግንባር ቀደም የእርሻ ኢኒስቲቲዩት) ዘገባ እንደሚያመላክተው በ2020 ኢትዮጵያ ጠቅላላ ደኖቿን ታጣለች ብሏል፡፡
ባለፈው የምዕተ ዓመት ለውጥ ላይ የኢትዮጵያ ደን 40 በመቶ ነበር፡፡ በወታደራዊው አገዛዝ ዘመን በ1987 ላይ ወደ 5.5 በመቶ አዘቀዘቀ፡፡ በ2003 ወደ 0.2 ወረደ፡፡የትዮጵያ የእርሻ ምርምር ኢኒስቲቲዩት ኢትዮጵያ በየዓመቱ 200.000 ሄክታር ደን እንደምታጣ ይናገራል፡፡ በ1990 እና በ2005 መሃል ኢትዮጵያ 14.0 በመቶ የደን ሽፋኗን አጥታለች፡፡(2.114.00 ሄክታር) በተጨማሪም 3.6 ከመቶ የዛፍ ተክሎችን አጥተናል፡፡ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ በመጪው 11 ዓመታት ኢትዮጵያ በ2020 ደን አልባ ሃገር ወደመሆኑ ትሸጋገራለች፡፡
በ 2004 የተደረገ ጥናት እንደሚያስረዳው፤ኢትዮጵያ 60 ሚሊዮን ሄክታር መሬቷ በደን በቀል ዛፎች የተሸፈነ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 7 በመቶው የደን እርሻ ነው፡፡63 በመቶ ገደማው ጫካማው ቦታ ደሞ በኦሮሚያ ክልል ያለ ሲሆን የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ደግሞ በ19 በመቶ ተከታይ ሲሆን፤ ጋምቤላ 9 በመቶውን ያካትታል፡፡ በጣም የሚያስገርመውታዲያ መለስ ዜናዊ  የደን እንክብካቤን አስመልክቶ ትኩረት የሰጠው ለቤንች ማጂ/ ጉራ ፈርዳ መሆኑና፤ በ2012 በእጅጉ መጠን ያጣው ችግር፤ ስርአት አልባ የሆነው የውጪ የንግድሁኔታ በአካባቢው መዳበሩ መሆኑን ነው፡፡ ከዚሁ ጋርም የደኖችን መጨፍጨፍ ሰበብ ያደረገው እንቅስቃሴው በዘር ላይ የተመሰረተ ማሳደድና ነዋሪዎችን በትውልድ ሀረጋቸው ብቻ ለማፈናቀል መወሰኑ ነው፡፡ 

ያም ሆኖ ግን፤መለስ ለአካባቢ ደህንነት ተቆርቋሪ ለመምሰል ‹‹የሰሜን ጎጃሞችን ሰፋሪዎች›› በማስረጃ የተደገፈ መፈናቀል አወዛጋቢውን ርእስ ለመሸፈንና ከወቀሳና ከትችት ለመዳን በማታለያነት ተጠቀመበት? መለስ ዜናዊ ስለአካባቢ ዓየር መቆርቆርን፤በሃሳብ መባዘንን ስለደኖች እንክብካቤ መቆጨትን፤ በማስመሰያነት ከመጠቀም ውጪ አንድም የእውነት ፍንጭ የሌለው ነው፡፡ ባለፉት አምስት ዓመታት፤መለስ ዜናዊ  በጣም ፍሬያማ የሆኑትን ለም የደን መሬቶች  ለሳውዲዎች ለሼሆቹ፤ለህንዶች፤ለቻይናዊያን፤ለኮርያውያኖችና የዶላርን ስም ለጠሩና ቁጥር ለጠቀሱ ሁሉ በሊዝ ስም ሸጦላቸዋል፡፡  እንደ የተከበረው የኦክላንድ ኢኒስቲቲዩት  [OI]  ግንዛቤ ከ2008 ጀምሮ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ
በትንሹ 3.619.509  ሄክታር  መሬት ለውጪ ኢንቬስተሮች (ቁጥሩ ሊበልጥም ይችላል) አስተላልፏል፡፡….የኢትዮጵያ ገዢ መንግስት በመሬቶች ላይ ስለተከናነው ድርድር ሁሉ በውይይት መግባባት ተደርሶበት ነው፡፡ አንድም የተፈናቀለ ነዋሪየለም፡፡ የተሰጠው መሬትም በጥቅም ያልዋለ ጦም አዳሪ የነበረ ነው በማለት ቀልመድመድ ቢያደርግም የኦክላንድ ኢንስቲቲዩት ግን ከነዋሪዎች ጋር ተካሄደ ስለተባለው ውይይትአንዳችም ማረጋገጫ አላገኘም፡፡ ………..በውሃ አጠቃቀም ላይ አንዳችም ገደብ አልተደረገም፤ በአካባቢው ዓየር ላይ ሊያደርስስለሚችለው ብክለት(EIA) ምንም የተወሰደ ጥናት አልነበረም፤ቁጥጥርም አልተደረገም፡፡ ኢንቬስተሮች ውሃን ያላንዳች ገደብ እንዲጠቀሙበት መፍቀድ እጅጉን የሚያስገርምና አሳዛኝ ደንታ ቢስነት ነው፡፡ የኦክላንድ ኢንስቲቲዩት ከኢንቬስተሮች በተደረገት ገለጻ፤ ምንም አይነት ቁጥጥርና ገደብም ስለሌባቸው የአካባቢውን ወንዝ በመገደብ ሊገለገሉበት እንዳቀዱና በአካባቢ የዓየር ቁጥጥርም አንዳችም ችግር እንዳላጋጠማቸው ገልጸዋል፡፡
ምንም እንኳን ገዢው መንግስትና ባለስልጣኖቹ የአካባቢ ዓየር ጥበቃ ይደረጋል በማለት ቢናገሩም  ከመንግስት በኩልአንድም የማስረጃ ማሳመኛ ሊያቀርቡ፤ ጥናትና ቁጥጥር ለመኖሩና ለመከበሩም ቢሆን አንድም የመንግስትባለስልጣን ወይ ም የየአካባቢው ሹም በዚህ ጉዳይ ላይ ወደ ቦታው ደርሶ እንደማያውቅ ነዋሪዎችሲመሰክሩ፤ ኢንቬስተሮችም ይህ ሁኔታ ለመከናወኑ አንዳችም ማስረጃ የላቸውም፤ የጠኝውም ሃገር ደግሞ ይህን አይነት ሁኔታ ተካሂዶበት አይውቅም፡፡………… ከአርሻ ይዞታ ላይ መፈናቀል በሰፊው የሚካሄድ የእለት ተእለት ሂደት ነው፤ አብዛኛዎቹ ተፈናቃዮችም ተገቢውን ማካካሻ አልተከፈላቸውም፤ከመኖሪያና እርሻቸው ሲነቀሉም በሌላ አካባቢ የእርሻ ቦታ እንዲፈልጉ በመደረግ በመሆኑ ከሌሎች የአካባቢው አርሶ አደሮች ጋር በቦታ ሰበብ ውጥረት እንዲፈጠር እየተደረገ ነው፡፡
በመጨረሻውም ሼሆቹ፤ሳውዲዎች፤ህንዶች፤ቻይናዊያን፤ ኮርያዎች (ሼሳህቻኮ)  ለሙን  መሬት በማቃጠል ለውጭ ገበያ የሚሆን ምርት ለማብቀልና ለመክበር የተሰባሰቡትና መሬቱንም በሻጩ መንግስት የተከፋፈሉት ኢንቬስተሮች ሲባሉ፤ ለእለት ጉርስና ቤተሰቡን ለማኖር በማለት ኩራማን በምትሆን መሬት ላይ ኑሮውን ለማሸነፍ የሚጥረው ዜጋ ግን፤ ሕገወጥ ኗሪ (‹‹ሰፋሪ››) ይባላል፡፡ እነዚህ ስብስቦች (ሼሳህቻኮ) ለ‹‹ልማት›› በሚል የማደናገርያ ቃል፤በሚሊዮን ሄክታር የሚቆጠር መሬት ለ99 ዓመታት ተሰጥተዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ከሞነርያ ቀያቸው በጉልበት በመፈናቀል የእርሻና የመኖርያ ቦታቸውን ለነዚህ ሼሳህቻኮች እንዲያስረክቡ ተፈርዶባቸዋል፡፡  

ሼሳህቻኮች ከግምት በማይገባ ገንዘብ ያሻቸውን ያህል የመሬት ባለቤት እንዲሆኑ ሲፈቀድላቸው፤ ኢትዮጵያውያን ግን የባለቤትነት ይዞታቸውን አንዳችም የገንዘብም ሆነ የቦታ ትክ ሳይደረግላቸው እንዲባረሩ ተፈርዶባቸዋል፡፡  ሼሳህቻኮ  በብርሃን በግላጭ በአክብሮት የደስታ አቀባበል ሲደረግላቸው፤ ዜጎች ግን ጸሃይ ከመጥለቋ በፊት አካባቢውን ጥለው እንዲሰደዱ ይደረጋሉ፡፡ ሼሳህቻኮ የመሬት ባለቤትነት መብት ሲኖራቸው ኢትዮጵያውያን ደግሞ ለመሬት አልባነት ይዳረጋሉ፡፡  ሼሳህቻኮ የነገስታታነት ከበሬታ ሲሰጣቸው፤ ኢትዮጵያውያን ደግሞ በዱላ መባረርን ይቸራሉ፡፡ እንደ ኦክላንድ ኢኒስቲቲዩት ጥናት  ከሁሉም በላይ የሚያሳፈረው በ ሼሳህቻኮ እርሻዎች ላይ ለመስራትና ኑሮን ለመታገል የፈቀዱትም ኢትዮጵያውያን በመጤዎቹ እንደ እንስሳ በመቆጠር ለግፍ መዳረጋቸው ነው፡፡

ወደ ሼሳህቻኮ ግዛት እንኳን በደህና መጣችሁ! የ‹‹ሰሜን ጎጃም ሰፋሪዎች›› ሊያከብሩትና ሊከተሉት የሚገባ የአካባቢ ዓየር ሕግ አለን? የ‹‹ሰሜን ጎጃም ሰፋሪዎች›› ከይዞታቸው መነቀል አስፈላጊ መሆኑን መለስ ሲያስረዳ፤ ‹‹ሰፋሪዎቹ›› ሕገወጥ፤በዘፈቀደ ቦታውን የያዙ፤ እና የአካባቢ ዓየርንም ደህንነት የሚያበላሹ ናቸው በማለት ይወነጅላቸዋል፡፡ ለመሆኑ የመለስ ገዢ መንግስት፤ሕጋዊነትን የሚጠይቅ፤ ስርአት የተቀመጠለት፤የገጠር አሰፋፈር ደንብ አለው? ለምሳሌ በጉዳዩ ላይ የተቀመጠው ወሳኙ ሕግ፤ ‹‹የገጠር መሬት አስተዳደርና አጣቃቀም አዋጅ ቁጥር 456/2005›› በእርሻ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ሁሉ፤ መሬትን ያለምንም ገደብ ይፈቅዳል እንጂ አሰፋፈርን በተመለከተ እንዴት መከናወን እንደሚገባው የሚለው አንዳችም ነገር የለም፤ ስለአስተዳደሩም የሚገልጸው ስርአት የለም፡፡ አተገባበሩን በተመለተ ሙሉ መብቱን ሙያው፤ብቃቱ፤ችሎታውም ለሌላቸው ‹‹የአካባቢው ባስልጣናት›› ትቶታል፡፡

 በእርግጠኝነት አዋጅ ቁጥር 456 ስለ ደን መሬት ጥበቃ፤አስተዳደር አንዳችም የሚለው ቃል የለውም፡፡በደፈናው የግብር ይውጣ ያህል፤ ደን፣የደን መመናመን፤እና የደን መሬት በማለት ይዘጋዋል፡፡ የተሸሻላና አዋጅ ቁጥር 456ን የተካውም አዋጅ ቁጥር 106/2007 ቢሆን፤ እንዲያው በይሆናል ግምት፤የታወጀ እንጂ  ክልሉ የአካባቢ ዓየር ጥበቃ ኤጀንሲ የለውም፡፡ አዋጅ ቁጥር 456ን ተግባራዊ የማድረጉ ሃላፊነት በእርሻና የገጠር ልማት ቢሮ ስር የተጣለ ሚንቀሳቀሰው ግን የተፈጥሮ ሃብትንና የዱር አራዊትን በመጠበቁ ላይ እንጂ  የደን ጥበቃውን በተመለከተ ጨርሶ የተጣለበትን ሃላፊነት አልተረዳውም ወይም ከጉዳይ አላስገባውም፡፡ የመሬት አጠቃቀም ገደብን በተመለከተ በገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ድንጋጌ ቁጥር 66/2007 ከጫካማ ቦታዎች ወይም ደኖች ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ግንኙነቱ ከውሃማ ቦታዎችን ከተንሸራታች መሬቶች ጋር ነው፡፡ 

በደፈናው ብቻ ደኖችን ስለማመናመን ወይም ስመጨፍጨፍና ለእርሻነት ስለማዋል የሚጠቅስ አንዳችም ክልላዊ ሕግ የለም፡፡ እና ታዲያ ‹‹ሰፋሪዎች›› ምን አድርጉ ነው የሚባሉት?
የፌዴራሉ ‹‹የደን ልማት ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 542/2007›› ቢሆንም ዝም ብሎ የእቅድ አቅጣጫ ጠቋሚ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡አዋጁ የመንግስትንና የግል ደኖችን ያከብራል ይላል እንጂ፤ደኖች እንዴት ሊለሙ እንደሚችሉ የሚየሳየው አካሄድ አለያም ደግሞ ግለሰቦች በስራው ለመሰማራት ፈቃዱን ከየት እንደሚያገኙ አይገልጽም፡፡ አዋጁ የግል ደኖች አልሚዎችን ግዴታ ሲደረድር ስለመብታቸው ግን ምንም አይልም፡፡ የአዋጁ ብዘው ቦታ የተሞላው ወደፊት ምን ሊደረግ ይገባል በሚል የምኞት እቅድ ላይ ነው፡፡

መለስ የቤንች ማጂ ‹‹ሰፋሪዎች›› ከአስፈላጊው የአካባቢ ዓየር መመርያ አዋጅ ቁጥር 299/2002 ጋር በሚጋጭ ሁኔታ ነው በማለት ሊያሳስት ይሞክራል፡፡ ይህ አዋጅ አስቀድሞ የተባለው ፕሮጄክት ተግባራዊ ከመሆኑ አስቀድሞ ሊጠናና ሊመረመር ይገባዋል፡፡ የዚህ አዋጅ ቁጥር 299 አባባልና አተረጓጎም ‹‹ሰፋሪዎቹ››  የአካባቢን ዓየር ሁኔታ ከሚመለከተው ሕግ ተጠያቂነት ውጪ ናቸው፡፡ከዚያ ይልቅ ለአዋጅ ቁጥር 456 (የገጠር መሬቶች አስተዳደርና ጥቅም) ተገዢ ይሆናሉ፡፡ይህ ሁሉ የሕጋ ቃልና የቴክኒክ አጠራርና አላስፈላጊው ክርክር ሁሉ ይቀርና ጉዳዩ በሙሉ የፖለቲካ ጥያቄና የፖለቲካ ፍላጎት ማስፈጸሚያ ይሆናል፡፡  በጊቤ ግድብ 3 ሂደት ላይ የቀረበው የከባቢ ዓየር አስተያየት በግልጽ የሚያሳየው ሁኔታ የፖለቲካ ጉዳይ ሲሆን የሚያስከትለውን ነው፡፡
 
የዘር ጥሰት ወይስ የደን እንክብካቤ? ከደቡብ ኢትዮጵያ ቤንች ማጂ/ጉራ ፈርዳ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ አማራዎች በግዴታ መፈናቀላቸው አያጠያይቅም፡፡በአሜሪካ ድምጽ ላይ የተስተናገዱት ቃለ መጠይቆች፤ በግዳጅ መባረራቸውን በግልጽ ያስረዳል፡፡ስለዚህም ቸል የማይባለውንና ሊታለፍ የማይገባውን ጥያቄ ልንጋፈጠው የግድ ነው፡፡ይህ አስገድዶ ከቀዬ ማፈናቀል የዘር ጥላቻ ነው ወይስ የተለመደ የተፈጥሮ ሃብትን መጠበቅ ነው? መለስ ዜናዊ ይህን አስገድዶ ማፈናቀልን በተመለከተ ማሳመኛ አድርጎ የሚያቀርበው  የ‹‹ሰሜን ጎጃም ሰፋሪዎች›› የተፈናቀሉበት ምክንያት ደኑን በማጥፋታቸውና አሰፋፈራቸውም በተለምዶ እንደሚያደርጉት ስርአት ያጣና ከህግ ውጪ በመሆኑ ነው ሲል፡  የደቡቡ ገዢ ሽፈራው ሽጉጤ በበኩሉ ደሞ  መለስ ስላነሳው ‹‹ሰፋሪዎች›› ስላደረሱት የደን መጨፍጨፍ፤ አንድም ቃል አልወጣውም፡፡ የፈጣሪ ያለህ ታዲያ ማን ሊታመን ነው? ዘር ማጥፋት እንዲህ ነው ሊባል የሚችል ህጋዊ ትርጉም የለውም፡፡

በ1993 የተባበሩት መንግስታት ኮሚሽን ቃሉን ሲተነትነው ‹‹ሆን ተብሎ ታቅዶ ከተወሰነ አካባቢ የተወሰነ ዘር ተወላጆች የሆኑትን በጉልበት፤ በማስፈራራት አፈናቅሎ ቦታውን ለሌሎች ዘሮች ለመስጠት የሚፈጸም››  ይለዋል፡፡የተባበሩት መንግስታት ሴኪውሪቲ ካውንስል የባለሙያዎች ኮሚሽን ድንጋጌ 780 የዘር ማሳደድን ሲተነትንም በሰብዊ ፍጡሮች ላይ የሚፈጸም ወንጀል በመሆኑ እንደጦር ወንጀል ይቆጠራል ይላል፡፡የተለያዩ ድንጋጌዎችና ትንታኔዎች ወንጀልነቱን በተደጋጋሚና በተለያየ ጊዜ ያረጋገጡት ነው፡፡የነዚህም ‹‹ሰፋሪዎች›› መፈናቀል ሆን ተብሎ በተመረጡ ብሄሮች ላይ የተፈጸመ ነዋሪውን የማግለል ደባ መሆን አለመሆኑ በተጠናቀሩት ማስረጃዎች ሊረጋገጥ የሚችል፤ጉዳይ ነው፡፡

ማካካሻ አይገባምን?
‹‹ሰፋሪዎቹ›› የተፈናቀሉት  የሃገሪቱን ደን ከጥፋት ለማዳን ነው ተብሎል የሚለውን የመለስ ሰበብ አምነን የምንቀበል ከሆነ፣ የተፈናቀሉትና ርስታቸውን፤ መኖርያ መንደራቸውን፤ ንብረታቸውን ያጡት ከፍ ላለ የሀገር ጥቅም መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ አባባሉ የሚታመን ሆኖ ፤በአዋጅ ቁጥር 456 ‹‹ሰፋሪዎቹ›› መሰረት መብታቸው ሊከበርላቸው የግድ ነው፡፡ በአዋጁ ላይ ‹‹የገጠር መሬት ይዞታው ለሕዝባዊ ጠቀሜታ የተወሰደበት ሰው፤ በነበረበት ቦታ ላይ ባለማውና ባፈራው ሃብት መሰረት ተመጣጣኝ ማካካሻ ሊያገኝ አለያም ተመጣጣኝ የሆነ ትክ ሊሰጠው ይገባል›› ይላል፡: እነዚህ ሰፋሪዎች ግን ለተዘረፉት ቦታ፤ እንስሳትና ንብረት እንዲሁም ላደረጉት የልማት ውጤት አንዳችም ማካካሻ አልተደረገላቸውም፡፡ ጸሃይ ስትጠልቅ በድቅድቅ ጨለማ አካባቢያቸውን ለቀው፤ በጀርባቸው የለበሱትን ጨርቅ ብቻ ይዘው: ሕጻናት ልጆቻቸውን አዝለው እንዲጠፉ ብቻ ነበር የተገደዱት፡፡ ሌላው ቢቀር ከሕጉ አባባል  አኳያ ማካካሻ ሊደረግላቸው አይገባም?
እረ የህግ ያለህ! እረ የህግ ያለህ!

Several Woyanne businesses burned down in Metemma

BY Tensae Ethiopia.org
It was reported last week by Ethiopian Review that 1 hotel and several stores owned by Woyanne officials were burned down in the border town of Metemma, northern Ethiopia, by a resistance group named Ethiopian Unity and Freedom Force (EUFF). Tinsae Ethiopia has smuggled out the following photos that shows the damaged businesses. According to Tinsae Ethiopia contacts in the area, Meles Zenawi’s regime has flooded the town with heavily armed soldiers following the incident. Tinsae Ethiopia encourages attacking Woyanne businesses and infrastructure as part of its civil resistance campaign to stop it from committing atrocities against the people of Ethiopia

See the link here: http://tinsae.org/index/?p=13253
                           http://www.ethiopianreview.com/content/37743



Sunday, April 22, 2012

ከተገኘ ነውጠኛ ሊሆን ነው ቃተኛ

ይድረስ ላስጠራዥ – መለስ ዜናዊ
ከተጠራዥ ስደተኛ – ዳዊት አበበ ,  ኦስሎ ( ኖርዌይ)

በሽተኛ – የማስታወስ ችሎታዬ ከጠፋ ሰነባብቷል ፣አንዳንድ ጊዜ በመንገድ ላይ ሆኘ ሳለሁ ከቤቴ ተነስቼ ወደ ቢሮዬ መሄዴን ? ፣ ወይ ደግሞ ከቢሮዬ ወጥቼ ወደ ቤቴ መመለሴን እስከማላውቅበት ድረስ ይምታታብኛል መድሃኒቱ ምንድነው ብሎ ይጠይቃል ዝንጉው- ህመምተኛ ሳይካትሪስቱን ፡፡

ሳይካትሪስቱ – በእንደዚህ ባለ ሁኔታ ላይ ማድረግ ያለብህ ነገር ቢኖር ፣ ዘወትር ወደ ሥራህ ስትሄድ የምሳ ዕቃ መያዝህን አትርሳ ፡፡ የምሳህ ዕቃ ባዶ በሆነበት ሰዓት ወደ ቤትህ መመለስህን ተገንዘብ ፡፡ የምሳህ ዕቃ ደግሞ ምግብ በያዘ ጊዜ ወደ ቢሮህ እንደምትሄድ ያስታውስሃል ፡፡ መድሃኒቱ እሱ ነው ብሎ ይመልስለታል የስነ ልቦናው ሃኪም፡፡

እኝህ ያገራችን ጉልበተኛ መሪ ፣ ሳይካትሪስት አያስፈልጋቸውም ብላችሁ ነው ጃል ? እኔ በዚህ ሃሳብ ስጸና ፣ ብዙዎች ደግሞ የለም ! እሳቸው ለቀቅ ፥ ለቀቅ የሚያደርግ የውሸት ህመም ወይም (pathological lier ) ስለሆኑ ጠበል የሚወስዳቸው አጥተው እንጂ ህመሙ የመጃጃት አይደለም የሚሉ አሉ ፡፡ እኔ እንኳ ከላይ እንዳለው ቀልድ ሳይካትሪስት ያስፈልጋቸዋል ያልኩበት ምክንያት ፣ እዛችው ፓርላማ ውስጥ ፣ ሃያ አመት ሙሉ ሲያገሱ ፣ ሁልጊዜ ቀደሞ ያሉትን ነገር እረስተው እንደገና ሲደረማምሱት ስላስተዋልኩኝ ነው ፡፡ የፓርላማውን በር ግን ስለመሳታቸውና ስለመደረማመሳቸው ያልኩት ነገር የለም፡፡

A pathological liar is someone who often embellishes his or her stories in a way that he or she believes will impress people. Some think a pathological liar is different from a normal liar in that a pathological liar believes the lie he or she is telling to be true at least in public and is “playing” the role. 

ለቀቅ ፣ ለቀቅ ስለሚያደርጋቸው ህመም ፣ በውኑ ይህ ደዌ ተጸናውቷቸዋል ወይ ? ብለን ምክር ቤቱ ውስጥ አሉ የሚባሉ ሃኪሞችን እንዳንጠይቅ – ለጊዜው ያሉት አንድ ታማኝ ተቃዋሚ የጥርስ ሃኪም እንጂ ፣ የአይምሮ ሃኪም ስላልሆኑ ፣ ለሳቸው አሳልፎ ማስመርመር ደግሞ በአረንጓዴው ጓደኛዬ ቅጠል የሳሳውን ጥርሳቸውን ሊያውልቋቸው ስለሚችሉ ፣ እኛም በአፈ- ላማ እንዳንያዝ ባናነሳው ቢቀርብን ይመረጣል፡፡ ምናልባት ባዮሎጂስቱ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በዳማ ከሴ ወይ ባንካሴ የጠቅላይ ሚንስትራችንን በሽታ እንዲገላግሉን እንማልዳቸዋለን፡፡ አለበለዚያ ምድረ ነውጠኛን ቃተኛ ላደርገው ነው እያሉ ማስፈራራቱን ስለተያያዙት በጠፋ የመኽር ዝናብ ጤፋችንን በቃተኛ ባይጨርሱት መልካም ነው፡፡

አቶ መለስ ፣ ልክ እንደቀልዱ ፣ ወደ ቤታቸው መመለሳቸውንም ሆነ ወደ ምክር ቤት መሄዳቸውን ያጡት እየመሰሉ ነው ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የምገዛት አገር ኢኮኖሚዋ አድጎ ፥ አድጎ ተስፈንጥሮ 11% ደርሷል እያሉን ከርመው ፣ በቅርቡ መምህራን በደመወዝ ጭማሪው አለመርካት ለተወሰነም ቀን ቢሆን ያደረጉትን የሥራ ማቆም አድማ ፣ለማጣጣል ሲሉ የተጠቀሙበት ያልተሞረደ ቋንቋ በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ንቀት አሳድሮባቸዋል፡፡ አቶ መለስ የመምህራኑን ጥያቄ ለማጣጣል በሚመስል የመፍጨርጨር ትንተና ሲንዘባዘቡ እንዲህ አሉ፡፡

በአገራችን ባለው ደሞዝ የረካ የለም ፡፡ የኑሮ ዉድነቱ ከፍ ያለ ነው ፡፡ ጥሩ ደመወዝ አይከፈልም ፡፡ ይህን እናቃለን፡፡ ለዚህ ማስታገሻ ደሞዝ ብንጨምር – ግሽበቱን ከፍ ስለምናደርገው አንሞክረውም ፡፡ ለዚህ ማስተካከያ ያደርግነው ነገር ቢኖር ፣ የደመወዝ ርከን ነው ፡፡ መምህሩ የደመወዝ ጭማሪና ፣ የርከን ጭማሪ ስላልገባው ነው የተምታታበት፣ መምህሩ 99.9 % በተደረገው የርከን ማስተካከያ የተደሰተ ነው አሉን፡፡እግዜር ያሳያችሁ ፣ ከዋሹ አይቀር እንዲህ ሽምጥጥ አድርጎ ነው ፡፡ የደመወዝ ጭማሪና ፣ የርከን ማሻሻያ ያልገባው መምህር ፣ ምን አይነት ተማሪ ይፈጥር ይሆን ? ይህ ንቀት አይደለም ?

አቶ መለስ ፣ ኧንደው ለአፋቸው ሻብያ ፣ ሻብያ ፣ ይላሉ እንጂ ፣ ከሻብያ በላይ እሳቸውን ምርር አድርጎ የሚያበሳጫቸው ነገር ቢኖር ፣ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ስም ሲጠቀስ ነው ፡፡ ምድረ ነውጠኛ ሰሞኑን ፣ መምህራን ባደርጉት አድማ ፣ ቋምጦ – ቶሎ ቶሎ በሉ እንጂ ! አቀጣጥሉት እንጂ ! እያለ የውስጥ አርበኞቹን ይዞ ቢሞክርም አልተሳካለትም በማለት ምርር ብለው ሲናገሩ ፣ የሻብያን ደጃፍ ግን ፣ ቢያንስ በወር ፥ ወር ፣ እንደሚያንኳኩ ፣ በአመትም እስከ አስራ አምስት ጊዜ ያህል ለማንኳኳት እንደሞከሩ ለሻብያ በተንቦጫቦጨ አንጀታቸው ይገልጹና ፣ ነውጠኞች ግን ከሻብያም በላይ ደመኞቻቸው እንደሆኑ ይገልጻሉ፡፡ 

የአቶ ኢሳይያስ መንግሥት አበሳጭቶ ስላባረራቸው ኤርትራውያን ዜጎች በመቆርቆር ከግብጽ ድረስ የተበተኑትን የኤርትራ ወጣት ኃይሎች ፣ የግብጽ መንግስት ለኢሳይያስ መንግሥት ሊያቀብላቸው በደረሰ ጊዜ ፣ ግብጾችን በማግባባት ኤርትራውያንን እንደታደጉዋቸው እንዲህ ይገልጻሉ፡፡አንዳንድ አገሮች አስገድደው ይሄን ስደተኛ ፣ ወደ ኤርትራ ለመመለስ ጥረት በሚያደርጉበት ወቅት ፣ ይህን እንዳያደርጉ ፣ ለማግባባት ጥረት እያደረግን ነው ፡፡ በዚህም ምክንያት ፍላጎቱ የሌላቸው ለምሳሌ ከግብጽ ወደ ኤርትራ እንዲመልሳቸው ያልፈለጉ የተወሰኑ ወጣቶችን ፣ በግብጽ መንግሥት ፈቃድና በስደተኞቹ ፣ ፍላጎት ወደ ኤርትራ ከምንመለስ ይልቅ ፣ ወደ ኢትዮጵያ እንድንሄድ እንፈልጋለን ብለው ሲጠይቁ ፣ ከግብጽ መጥተው ኢትዮጵያ እንዲጠለሉ እየተደረገ ነው ፡፡ አሉን አቶ መለስ በእርሳቸው አርአያ ጠፍጥፈው ለፈጠሩት ፓርላማ ፡፡

እድለኞቹ የኤርትራ ወጣቶች ፣ አንቺ ምን ቸገረሽ ሁለት እናት አለሽ እንዲሉ ፣ በክብር መጥተው ኢትዮጵያ እንዲኖሩና በከፍተኛ ደረጃ ባሉ ዩንቨርስቲዎችም በነጻ እንዲማሩ ሲደረግ ፣ አቶ መለስ ባሳለፍነው የግንቦት ወር ኦስሎ ኖርዌይ ፣Energy for all ተብሎ በተጠራው ጉባኤ ላይ ፣ ባለ ሁለት መልኩን መለስን በመቃወም በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ፣ እጅጉን ቅያሜ ስለገባቸው ፣ጊዜ ጠብቀው ፣ ተቃዋሚዎቻቸውን ለመበቀል ከኖርዌይ መንግሥት ጋር በመዋዋል ታላቅ ንግድ ተዋዋሉ፡፡ 

አቶ መለስ በግንቦቱ የኦስሎ ጉባኤ የተደረገባቸውን ከፍተኛ ተቃውሞ አስመልክቶ ፣ የኖርዌይ ጋዜጠኛ ባደረገላቸው ጥያቄ –ይህን ድምጽ ይሰሙታል ? በመንግሥትዎ ላይ የተደረገ ተቃውሞ ነው ፣ ለዚህ መልስዎ ምንድነው ? ተብለው ሲጠየቁ የመለሱት መልስ ፣ – እንኳን ውጭ አገር ቀርቶ አገራችንም ቢሆን ዜጎች በተቃውሞ ሰልፍ ይወጣሉ ፡፡ ይህ ተቃውሞ ልክ እንደዚህ ደመና ነው ፤ ቀስ እያለ ይጠፋል ነበር ያሉት ለጋዜጠኛው፡፡ ዕለቱ በርግጥም ደመናማ ነበርና፡፡

አንዳንድ አገሮች አስገድደው ስደተኛውን ወደ ኤርትራ ለመመለስ ጥረት በሚያደርጉበት ጊዜ ፣ የኢሳይያስ መንግሥት እንዳይበላቸው ታደግናቸው ያሉት መለስ ፣ ኢትዮጵያውያንን ያለፍላጎታቸው ተገድደው ከኖርዌይ እንዲመለሱ ለምን ተስማሙ ? ምድረ ነውጠኛን ለማሸማቀቅና ለመምታት ፣ እንዲሁም ወደ አገሩ ተገድዶ በሚመለስበት ጊዜ እንደቃተኛ ሰልቅጦ ለመብላት የተደረገ እንቅስቃሴ እንደሆነ ፣ ኖርዌይ ውስጥ ያለው ስደተኛ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡

አቶ መለስ እኛን ለማስመለስ የሚደረግልዎት የርዳታ ዳረጎት በብዙ ሚልዮኖች ክሮነር እንደተጨመረልዎት ኖርዌይ ውስጥ በታተሙት ጋዜጦች አንብበናል ፡፡ አሁን በቅርቡ ከሥልጣናቸው እንዲባረሩ በተደርጉት የርዳታ ሚንስቴር ጓደኛዎ ኤሪክ ሱልሃይም እንደተጨመረልዎት ተረጋግጧል፡፡ የቅርብ ጓደኛዎት ኤሪክ ሱልሃይም ኖርዌይ ውስጥ ባሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች ታላቅ ሥራና የማጋለጥ ትግል ፣ ከቦታቸው ለጊዜው ገለል ተደርገዋል፡፡ ፣ ኖርዌይ ውስጥ ባለው አሠራር ደግሞ ፣ ይህ ክርበታ ያልተለመደ ነው ፡፡ 

አሁንም ትግላችንን እንቀጥላለን፡፡ድምጻችንንም በአለም ዙርያ እንዲሰማ እንታገላለን፡፡ በምንም አይነት ሁኔታ ለጌታቸው አሰፋ ደህንነት ማሰቃያና ማስገደያ ቄራ ጭዳ አንሆንም፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!

የግልገል ጊቤ አንድ ግድብ ስጋት ፈጥሯል

By Reporter

የግልገል ጊቤ ቁጥር አንድ የኃይል ማመንጫ ግድብ በደለል የመሞላት ችግር አስቸኳይ መፍትሔ ካልተሰጠው፣ በአገሪቱ ላይ የሚፈጥረው ተደራራቢ ተፅዕኖ ከባድ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አስገነዘቡ፡፡ ደለሉን በአፈር በተሞላ ጆንያ ለመከላከል እየተሞከረ መሆኑም  ተገልጿል፡፡

የተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሀብት ልማትና የአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ከውኃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ ዓለማየሁ ተገኑ፣ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ምሕረት ደበበና ከሌሎች ኃላፊዎች ጋር ባለፈው ሐሙስ ውይይት ሲያካሂዱ እንደገለጹት፣ የግልገል ጊቤ ቁጥር አንድ በደለል የመሞላት ችግር አስቸኳይ መፍትሔ ካላገኘ በአገሪቱ ኢኮኖሚና ፖለቲካ ላይ ከባድ ተፅዕኖ ማስከተሉ የማይቀር ነው፡፡

‹‹እውነት እንነጋገር፤ እንዲያውም እዚህ ስንወያይ ሚዲያ አንፈልግም [ነበር]፤ ጉዳዮችን በደንብ አይተን መሄድ አለብን፤›› በማለት አስተያየታቸውን መስጠት የጀመሩ አንድ የተወካዮች ምክር ቤት አባል፣ ከሁለት ዓመት በፊት የደለል ችግሩን ለመፍታት ከአካባቢ ጥበቃ፣ ከውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና ከጅማ ዩኒቨርሲቲ የተውጣጣ ግብረ ኃይል ቢቋቋምም ችግሩ አሁንም አለመፈታቱን ተናግረዋል፡፡

‹‹እንዳየነው ግድቡ ችግር አለበት፤ በጆንያ አፈር ተሞልቶ ነው እኮ ለመገደብ ጥረት የሚደረገው፡፡ እዚያው ግድቡ ድረስ ሄደን ችግሩን አይተናል፤›› ያሉት እኝህ የፓርላማ አባል፣ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራ ረገድ በክልሉም ሆነ በጅማ ዞን የተሠራ ሥራ አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት በጉዳዩ ላይ ከአሁን በፊትም ከውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር ውይይት የተደረገ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ምንም የመጣ ለውጥ የለም፡፡

ሌላዋ የፓርላማ አባል በበኩላቸው በቅርቡ ‹‹ናይል ዲስኮርስ ፎረም›› በሚል በተዘጋጀ ወርክሾፕ ግልገል ጊቤ ቁጥር አንድ ግድብ በደለል እየተሞላ መምጣቱን የሚያሳይ ጥናት ያቀረበ አንድ አጥኚ፣ ደለሉ እስከወገቡ ሲውጠው የሚያሳይ ፊልም ለታዳሚው ማቅረቡን፣ ክስተቱን ተከትሎም በቦታው የነበሩ ታዳሚዎች ‹‹በቴሌቪዥን ይቅረብና የኢትዮጵያ ሕዝብ ይመልከተው›› የሚል ጥያቄ ማቅረቡን የገለጹ ሲሆን፣ ጉዳዩ በፖለቲካ ረገድ የሚፈጥረው ተፅዕኖ ምን ሊሆን እንደሚችል ሁሉም የሚረዳው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በአካባቢው የሚኖረው ኅብረተሰብ ግድቡ አፍንጫ ሥር እንደሚያርስ፣ በቦታው የሚመረተው የበቆሎ አገዳስ የት ነው የሚጣለው? የሚል ጥያቄ እንደሚያስነሳ የገለጹት እኝሁ የፓርላማ አባል፣ ደለሉን በጆንያ በተሞላ አፈር ለመከላከል መሞከር ችግሩን ከማባባስ ውጪ የሚያመጣው ለውጥ አለመኖሩን ገልጸዋል፡፡

‹‹የቅንጅት ሥራ ሊሠራ ይገባል፤ ለፖለቲካ መጠቀሚያ ሰፊ በር ይከፍታል፤ ከህዳሴ ግድቦችና ከሌሎች ግድቦች ጋር ያያይዙታል፡፡ ‘ይኼ መንግሥት የሚያውቀው መገደብ ብቻ ነው ወይ? የገደበውን አይከታተልም?’ የሚል የፖለቲካ አንድምታ የሚያመጣ በመሆኑ ጊዜ ልንሰጠው አይገባም፤›› ሲሉ ጉዳዩ ከኢኮኖሚም አልፎ ከፖለቲካ ጋር የሚገናኝ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በፓርላማ አባላቱ ከተነሱት በርካታ ችግሮች መካከል የግንባታ ጊዜው ያለፈው የርብ የመስኖ ፕሮጀክት ጉዳይ አንዱ ነው፡፡ የርብ የመስኖ ፕሮጀክትን ባለፉት ሁለት ተከታታይ ዓመታት የጐበኙ መሆናቸውን የጠቆሙ አንድ የቋሚ ኮሚቴ አባል፣ በዲዛይኑ ውስጥ የካናል ሥራ አለመካተቱን፣ ግድቡም አሁን ባለበት ደረጃ ውኃ የመያዝ አቅም የሌለው መሆኑን ከገለጹ በኋላ፣ ‹‹ካናል በሌለበት ሁኔታ ግድቡ እንዴት አድርጐ ለመስኖ እንደሚውል ግልጽ አይደለም፤›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ አካባቢውን ተዘዋውረው በተመለከቱበትና ኮንትራክተሮችን ባነጋገሩበት ወቅት የመቆፈርያ ማሽኖችና የገልባጭ መኪኖች ችግር እንዳለባቸው የገለጹላቸው መሆኑን የጠቆሙት የፓርላማው አባል፣ በጉዳዩ ላይ ማብራርያ እንዲሰጥ ከሚዲያ ጥያቄ የቀረበላት የውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣ ‹‹ችግሩ የተፈጠረው በሲሚንቶ እጥረት ነው›› በማለት የሰጡት ምላሽ እነሱ በቦታው ተገኝተው ካዩትና ከተገነዘቡት ጋር የማይመሳሰል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ እሳቸው እንዳሉት የርብ ወንዝ የመስኖ ፕሮጀክት 14 ሺሕ ሔክታር የሚጠጋውን የፎገራና የሊቦ ከምከም ወረዳን እንደሚያለማ ቢታወቅም፣ ‹‹አሁን ባለበት ይኼ ይሳካል ወይ?›› የሚል ጥያቄ እንደሚያስነሳ አመልክተዋል፡፡

ከዓመታት በፊት የተጀመረው የደምቢዶሎ የውኃ መስመር ዝርጋታ የዘገየበት ምክንያት ምንድነው? የሚል ጥያቄም ከተለያዩ የፓርላማ አባላት ተነስቷል፡፡ የመብራት አገልግሎት ያገኛሉ ተብሎ መብራት ያልገባላቸው አካባቢዎች መኖራቸውን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ንብረቶች አላግባብ በየቦታው ተጥለው እንደሚገኙ የገለጹ የፓርላማ አባላትም ነበሩ፡፡

ከቋሚ ኮሚቴ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎች የቀረበላቸው የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ ዓለማየሁ ተገኑ ችግሮች ስለመኖራቸው አልካዱም፡፡ የደምቢዶሎ የውኃ መስመር ዝርጋታ የተጓተተው በኮንትራክተሩ አልምጥነት መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትሩ፣ በአውሮፓ ኅብረት አበዳሪነት የሚሠራውን ይህንን ፕሮጀክት ከኮንትራክተሩ ጋር ውል በማፍረስ ከማቋረጥ ይልቅ በኮንትራክተሩ ላይ ጫና በማሳረፍ ማሠራት የተሻለ አማራጭ ሆኖ መገኘቱን አስረድተዋል፡፡ ‹‹ይኼ ገንዘብ የአውሮፓ ኅብረት ገንዘብ ነው፤ ኮንትራክተሩ የመጣው ከአውሮፓ ኅብረት አገሮች ነው፣ አንድ ቦታ ብትቆነጥጥ ሺሕ ነው የምታስጮኸው፤ ኮንትራክተሩን አንነክሰው ነገር ምን እናድርግ?›› ያሉት አቶ ዓለማየሁ፣ መንግሥት ኮንትራክተሩን ቢያባርር ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ የሚወስደው ጊዜ ረጅም በመሆኑ፣ ሚኒስቴር መሥርያ ቤቱ የሚቻለውን ያህል ትግል እያደረገ ፕሮጀክቱን ለማስፈጸም በመሥራት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

እሳቸው እንደሚሉት፣ ከኮንትራክተሩ አልምጥነት በተጨማሪ ፕሮጀክት ሊያስተዳድሩ የሚችሉ የውኃ አገልግሎት ባለሙያዎች አለመኖራቸው ሌላው ችግር ነው፡፡ ‹‹ፕሮጀክቱን ለውኃ አገልግሎት አስተዳድር ብለን ብንሰጠው ማስተዳደር ይቅርና ትክክለኛ መረጃ እንኳን ማስተላለፍ የማይችል መዋቅር ነው ያለን፡፡ ይኼ የምንደብቀው ነገር አይደለም፡፡ በውኃ አገልግሎት ላይ ያለው አመራራችን አቅም ውስንነት አለው፡፡ ኮንትራት ማስተዳደር ይቅርና የተዘጋጀውን ውኃ እንኳን በትክክል ለኅብረተሰቡ እያከፋፈለ መልካም አስተዳደር የማይፈጥር ደካማ መዋቅር ነው ያለን፤›› በማለት ሚኒስቴሩ በባለሙያ ደረጃ ያለበትን ችግር ገልጸዋል፡፡

መብራት እንዳገኙ ተደርጐ በሚኒስቴር መሥርያ ቤቱ የተጠቀሱ አካባቢዎች አገልግሎቱን እንደማያገኙ ታውቋል ተብሎ በቋሚ ኮሚቴ አባላት የተጠቀሰውን በተመለከተም፣ ‹‹እኛ ተሠርቷል በምንለውና ምክር ቤቱ አልተሠራም በሚለው ለመተማመን አዲስ ሪፖርት ማውጣት ይኖርብናል፡፡ ዝርዝሩን ይዘን እንመጣለን፤ ምናልባት ከታች ተሠርቷል ተብሎ እላይ ሊያንሳፍፈን ይችላል፤ መንሳፈፍ ግን አንፈልግም፤ ታች ድረስ መሄድ ይኖርብናል፤ ሰውም አሰማርተን ቢሆን በራሳችን ሰፊ ቁጥጥር ማካሄድ እንችላለን፤›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የግልገል ጊቤ ፕሮጀክት ችግር በጣም አስከፊ መሆኑን መሥርያ ቤታቸው የተገነዘበው መሆኑን የጠቆሙት አቶ ዓለማየሁ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ወደተከለለው አካባቢ መግባታቸው ተገቢ አለመሆኑን በማንሳት ከዞኑ አስተዳደር ጋር በጉዳዩ ላይ ሰፊ ውይይት መደረጉን ቢገልጹም፣ ፎረም የተባለው ድርጅት ያቀረበው ጥናት ከበስተጀርባው ያለው ዓላማ ምን እንደሆነ መጠናት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

‹‹አንዳንድ ጉዳዮችን አንስቶ የገንዘብ መፈለጊያና መብያ የሚደረግበት ሁኔታ ስላለ [ጥናቱን] ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ነው የምናየው፤›› ያሉት ሚኒስትሩ፣ የደለል ችግሩን ለመቅረፍ የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ሥራ መሠራት አለበት በሚለው ጉዳይ ላይ ከዞኑ ጋር የተግባቡበት ሁኔታ መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡ ‹‹በቅርብ ጊዜ ከእነሱ [ከዞኑ አመራሮች ጋር] ስብሰባ አለን፤ ይህ ነገር አንገብጋቢ ነው፤ የእናንተን ነገር [አስተያየት] ወስደን በአካባቢው በሚደረገው የእንክብካቤ ሥራ በከፍተኛ ደረጃ ልንረባረብ ይገባል፤›› ብለዋል፡፡

የርብ ግድብን በተመለከተም ቦታውን በአካል ሄደው በጐበኙበት ወቅት አንዳንድ ችግሮች መኖራቸውን የተመለከቱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከካናል ዲዛይን ጋር በተገናኘ የነበረው ችግር በጉብኝታቸው ወቅት የተፈታ መሆኑን፣ የነበረውን የገልባጭ መኪኖች እጥረት ለመቅረፍም ሚኒስቴር መሥርያ ቤቱ ካስገባቸው 53 ገልባጭ መኪኖች መካከል አሥሩ ወደ አካባቢው የተላኩ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ዓለማየሁ፣ ግድቡ በአሁኑ ጊዜ ውኃ መያዝ ካልቻለ እንደገና ሌላ ዓመት መጠበቅ የሚያስፈልግ በመሆኑ ‹‹ግድቡ ውኃ መያዝ አለበት›› የሚለው ግብ መሳካት እንዳለበት መግባባት ላይ የተደረሰ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 ‹‹የርብ ግድብ ግንባታ መዘግየት ከሲሚንቶ እጥረት ጋር የሚያያዝ ነው›› በሚል የውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ሕዝብ ግንኙነት የሰጠውን ምላሽ በተመለከተም፣ ‹‹በሚዲያ ላይ የተናገረው የሕዝብ ግንኙነት ሰውዬ የሰጠው መግለጫ “Useless” (እርባና ቢስ) ነው፤ የማይጠቅምና መረጃ ሊሆን የሚችል አይደለም፤ ይህንን ገምግመናል፤ አንዳንድ ሰንካላ ምክንያት የሚሰጡ ባለሙያዎች እንዳሉ ሊታወቅ ይገባል፤›› በማለት ትችት ሰንዝረዋል፡፡   

ኢቲቪ በአኪልዳማ ድራማ የተነሳ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው (አሉ).

 By Abetokichaw
ሰሞኑን የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ ከነ አንዷለም አራጌ ጋር በተያያዘ ባወጣው ዘገባ ምክንያት አቃቤ ህግ “በፍርድ ሂደቱ ላያ ጣልቃ ገብተሀል” በሚል ፍርድ ቤት እንዳቀረበው ይታወሳል። (በቅርቡ አይደል እንዴ… እንዴት ይረሳል…? ብለው ይከተሉኝ) ያንን ወሬ ባቀበልኩዎ ግዜ ከዚህ በፊት ኢቲቪ አካልዳማ የተባለውን “ፊልም” ሲያቀርብ  አቶ አንዷለም አራጌ “ኢቲቪ በፍርድ ሂደቱ ጣልቃ ገብቷል” ብለው ቢከሱ የሚሰማቸው እንዳላገኙ አውርተን ነበር።

  በነገራችን ላይ አቶ አንዷለም በወቅቱ የኢቲቪን አኪልዳማ በከሰሱ  በነጋታው ፊልሙ በህዝብ ጥያቄ ተብሎ ተደግሟል። (በወቅቱ እኔም በሆዴ በብሽሽቅ እኮ መንግስቴን የሚችለው የለም። ብዬ አድንቄ ነበር።) ትላንት ማታ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንዳወራው ደግሞ የአኪልዳማ አዘጋጅ ጋዜጠኛ እና ኢቲቪ፤ አንድነት ፓርቲ በከሰሳቸው መሰረት ሚያዝያ 24/2004 ዓ.ም በልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሊቀርቡ እንደሆነ ነግሮናል።

 ዜናው በዚህ አበቃ ቀጥሎ የኔ አስተያየት ይቀርባል። አዲስ መስመር ላይ እንገናኝ…እኔ የምለው ወዳጄ ፍርድ ቤቱ በኮመዲያኖች ቁጥጥር ስር ውሏል እንዴ? ብዬ ልጠይቅ ነበር አጓጉል መዳፈር ይሆንብኛል ብዬ ትቼዋለሁ። ነገር ግን፤ አቶ አንዷለም አራጌ በአኪልዳማ ላይ አቤቱታ ካቀረቡ ስንት ግዜያቸው? ያኔ እርሰቸው አቤቱታውን ሲያቀርቡ የተሰጣቸው ምላሽ ወደር የለሽ ድብደባ እና “ምን ታመጣለህ!” በሚመስል መልኩ ፊልሙን ደጋግሞ ማሳየት ነበር።በዚህ የተነሳ በርካቶች “የተከበረውን ፍርድ ቤት” የተቀበረ ብለውታል ምን እርሱ ብቻ ብዙ ምድራዊ ስድቦችን እና ርግማኖችንም አውርደውበታል።

ታድያ ዛሬ እነ ተመስገን ፍርድ ቤት በቀረቡ በነጋታው ኢቲቪም ተጠራ። ከዚህ ምን አንደምጠረጥር ልናገርማ…ኢቲቪ ያደረገው ስህተት ፍርድ ቤቱ አላጣውም… ታድያ ያኔውኑ አቶ አንዷለም እንደከሰሱት ችሎት ላይ ሊያቆመው ፈልጎ ነበር። ነገር ግን ፍርድ ከላይ ነውና “እነ ፍትህ ካልቀረቡ ኢቲቪም አይቀርብም ሲሉ የበላዮቹ አዘዙ… (መጠርጠር መብቴ ነው) ታድያ እነ ፍትህ ጋዜጣ  በምን ስህተት ፍርድ ቤት ይቅረቡ? ሲፈለግ ሲፈለግ ይሄንን ያህል ግዜ ወሰደ። አሁን ገና በአቃቤ ህጉ አይን ፍትህ ጋዜጣ ላይ ስህተት የሚመስል ነገር ተገኘ።

 ከዛስ… ከዛማ በል ኢቲቪ አሁን አንተም ና… ተባለ።  ይሄ ልጅነቴን አስታውሰኛል…ልብስህን ቀይር…. እርሱ ካልቀየረ አልቀይርም።ትምህርት ቤት ሂድ … እርሱ ካልሄደ አልሄድም።ፍርድ ቤት ቅረቡ እነሱ ካልቀረቡ አንቀርብም….! (አይ ጉልቤ መሆን ደጉ) እኔ ደንቆኛል… እርስዎስ…?

Saturday, April 21, 2012

ጠቅላይ ሚንስትሩና ንቀታቸው!!

 By ተሻገር ምትኩ
ጠቅላይ ሚንስትሩ ለተወካዮች ምክር ቤት የሰጡትን ንግግር በሃፍረት ተሞልቼ ከጎደኞቼ ጋር ሳየው ቆየሁ። በሚገርም ሁኔታ ያሳፍራል። እንዴት ኣንድን ሃገር በሃላፊነት መራለሁ ከሚል ግለሰብ እንደዛ አይነት የወረደ ንግግር ይደመጣል? ያው እኔም እሱ የፈጠረኝ ትውልድ ስለሆንኩ ያሉት ባይገርመኝም እንዴት አንድ ሰው በ 20 አመት ውስጥ እራሱን ጠብቆ መናገር ያቅተዋል? 

እኛ አማሮች ላይ ያሉት ላይ እመለስበታለሁ ግን በትንሹ ስለኣስተማሪዎች የተሰጠውን አስተያየት ስላናደደኝ ትንሽ ልበል። እዚህ ላይ አንድ ነገር ካላልኩ በጣም እወዳቸው የነበሩትን አስተማሪዎቼን የማዋርድ ስለመሰለኝም ጭምርም ነው።

አስተማሪዎች የተከበሩና ትውልድ ለመቅረጽ የሚጫወቱትን ሚና ለኣንባቢ በማስረዳት ማሰልቸት ኣልፈልግም። ግን እንበልና (ጠቅላይ ሚንስትሩ እንዳሉት) ከብዙ ሺ አስተማሪዎች ጥቂቶች መጥፎ ናቸው እንበል። እነዛ ግን በደካማነታቸው ስንት ሰው ጎድተዋል? 10 ሰው? 100 ሰው? 1000 ሰው? ምናልባተም በ አስር ሺዎች እንበል። ጠቅላይ ሚንስትሩና የሳቸው ጠባብ ፖሊሲ ኣንድ ትውልድ ደምስሶ ሁለተኛውን እያደነቆረ እንደሆነ አያውቃሉ? እሳችው ደካማ ሚልዋቸው አስተማሪዎች ስለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚሉትን ሰምተዋል? እንደሰማሁት ከሆነ ማይክራፎን ብዙ ግዜ ሲይዙ መስማት ይከብዳል ሲሉ እንጅ እስካሁን እውነት አልመሰለኝም ነበር።

ስለኛ አማሮች ደሞ ሲያወሩ ፡ ያው የለመደባቸውን ቤት ያፈራውን ከፋፍለህ ግዛን ሊጠቀሙብን የሞከሩ ይመስላል። ሲናገሩ “ምስራቅ ጎጃም” የሚለወን ቃል መጠቀማቸው ሌሎች አማሮች አፋችሁን ዝጉ ነው? ወይስ ጉዳዩ ጠቃላላ ኢትዮዽያዊያንን አይመለከትም ለማለት ነው? ያንን እንደወም እንደንቀትና ድፍረት ያዩ ፡ አማራው መደራጀት አለበት ብለው እየገፉበት ይገኛሉ። ስላልተደራጀን አንጠቃለን ሲሉን የነበሩትን ወንድሞቻችንን አሁን ጆሮቻንን ከፍተን መስማት ጀምረናል። ጠ/ሚንስትሩ ሚሉት በጣም ይገርማል ፡ የጉራ ፈርዳን አካባቢ አማሮች ምስራቅ ጎጃም አደረጉት የሚሉን ፣ ከ አንድ አካባቢ የመጡ ህዝቦች በመብዛታቸው የተነሳ የአራት ኪሎ ቤተመንግስቱንና አንዳንድ የ አዲስ አበባን ኣካባቢዎች የምኖች ሰፈር እየተባሉ እንደሚጠሩ ያውቃሉ?

የሰሞኑን የ ጠ/ሚንስትሩን ንግግር ወትሮው እንደምናደርገው ከ ደኞቼ ጋር አብረን ስንከታተለው ነበርን። በየጊዜው ስለሀገራችን ፖለቲካና ስለተለያዩ ጉዳዮች ተገናኝተን ምንወያይበት ሻይ ቤት (ኮፊ-ሀውስ) ተቀምጠን ሳለን ጏደኞቼ የተለመደውን ስድብና ዘለፋ ይሄ ሼባ ምናምን እያሉ ጠ/ሚንስትሩን ስብእና የሚነኩ ነገሮች ሲናገሩ ፡ ሁልግዜ ስራ በዝቶባቸው ነው እያልኩ እንደምከራከርላቸው ከትላንት በስትያ ግን ቃል ሳልተነፍስ ነገሩን ሳዳምጥ ቆየሁ። 

እንዴት ስራ አይብዛባቸው? በዚች ጉዳይ ላይ አስቡት እስቲ ፡ እራሳቸው መርማሪ ፖሊስ ፣ ከዛም አባራሪ ፖሊስ ፣ ባለሙያ ፍርድ ሰጪ(ወረቀት እጨርሳለሁ እንጂ ዝርዝሩ አያልቅም) እያለ ይቀጥላል። እናም እነዢህ ጏደኞቼ ሲያብጠለጥሉዋቸው “ይሄ ሼባ ጉራፈርዳን ምስራቅ ጎጃም አደረጉት ሚለን ሰሜን ጎንደርን ከነ ካርታው የምን ይዞታ አደረጉት እየተባለ እንደሚወራ አልሰማም እንዴ?” እያሉና የተለያየ ነገር በማንሳት ከፍ ዝቅ ሲያደርጉዋቸው አመሹ። ወጣትነት ጥሩ ነው። ከ ጠ/ሚንስትሩ ሚፈልቁትን የወረዱ ሃሳቦች ወይንም በትምህርት አለዛም በእድሜ የማስተካከል እድሉ አለን። ይብላኘ ለሳቸው። 

እኛ ውጣቶች እንደውም ካስፈለገን የ አምስት አመት የ ስብእናና ውርደትን የመከላከል ትራንስፎርሜሽን እቅድ አውጥተን 11 ፐርሰንት እድገት አክለንበት ምናሳካው ይመስለኛል።በሰሞኑ የ ህዝብ ንግ ግር ላይ ጠ/ሚንዝትሩ ያለማፈር እንደዛ ሲተረተሩ እንዴት ከኔና ከኔ ትውልድ ጥሩ ነገር ሊጠበቅ ይቻላል? ይሄ ሁሉ ውሸት አይናቸውን በጨው ኣጥበው ሲዋሹ እኔዴት ቢንቁን ነው? ከሱም ብሶ አጎንብሶ አለ የሃገረ ሰው። 

ጠ/ሚንስትሩ ብሄራዊ ሆነው እኛ አማሮች ተነካን ስላልን ጎጠኞች ተብለን የተፈረጅነው በየትኛው ስሌት ንው? እኔምለው ጠ/ሚንስትሩ በብዙ ሚልዮን የሚቆጠረውን የኢትዮዽያ ህዝብን ትተው በጥቂት ሚልዮን እንደውም ወርደው በመንደርና አካባቢ ተደራጅተው ስልጣ ላይ መፈናጠጣቸውን ረሱት እንዴ? አልፈው ተርፈው ኢትዮዽያን እያስተዳደርኩ ነው እያሉን ዞር ብለው የዛው ኣናሳ ስብስብ መሪ ሆነው እስከዛሬ ህዋሀትን እያስተዳደሩ እንዳሉ ዘነጉት እንዴ? ያም ሆነ ይህ አይደለም በ ፓርላማ ፊት ቢወራጩ ነጠላ ዘቅዝቀው እያለቀሱ ቢነግሩንም ምናምናቸው ከመሰላቸው አዝንላቸዋለሁ። እወነቱን እናውቃለን። እናም ያባረረ ቢረሳም የተባረረ አይረሳም!!!

እኔን ለማግኝት ከፈለጉ ፡ teshagermitiku@yahoo.com በሚለው አድራሻ እገኛለሁ።