Welcome!
"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu
Tuesday, February 5, 2013
Monday, February 4, 2013
ሽብርና ፍርሃት ለመፍጠር የሞከረው የህወሃት ጀሌ ተጋለጠ
(አዲስ ቮይስ) በጋዜጠኛ አበበ ገላው እና በቤተሰቡ ላይ ህገወጥ በሆነ መንገድ በተከታታይ ስልክ በመደወል ሽብርና ፍርሃት ለመፍጠር የሞከረው ግለሰብ ማንነት ተጋለጠ።
ግለሰቡ በተለይ በአለፈው ወር ላይ ወደ ኢሳት ሬድዮ የአድማጮች መልእክት መቀበያ በመደወል በተለይ ለጋዜጠኛው
በተወው መልእክት ደምህን እንጠጣለን እንዲሁምቤተሰቦችህን እንፈጃለን፣ በአዲስ አበባ ያለህን ቤት እናቃጥላለን የሚሉ
ሁለት ተከታታይ መልእክቶችን አስቀምጦ እንደነበር ታውቋል።
Tuesday, January 29, 2013
ሒትለርና አይሁድ፤ መለስ ስብሀትና አማራ
በሉሉ ከበደ
ውድ አንባቢያን “ዘራፊ ሚሊየነሮች” ለሚለው ጽሁፍ ካደረሳችሁኝ መልሶች አጠር ያለውን አንዱን እንመልከትና ወደሚቀጥለው ጉዳይ እናመራለን።
“ወዳጄ ስለነዚህ እርጉም ሰዎች የጻፍከዉን ከማህደሬ አዉጥቼ ዛሬ አነበብኩት። እግዜር ይስጥህ። ምን እላለሁ። አፍዝ አደንግዝ እንደተደረገብን ሁሉ ዝም ብሎ ማየት ሁኗል ።ጉርሻ በሚሸጥበት አገር ሰዉ በቁንጣን አለቀ ሲሉን ለማመን ይዳዳናል። ምን አይነት እርጉም ወራዳ ትዉልድ እንደሆንን ነዉ የሚያሳየዉ።
“መናገር የማልፈልገው ብዙ ነገር አለ” ብጹእ አቡነ ሕዝቅኤል
የቅ/ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል |
- “ቤተክርስቲያናችን ከግብጽ ባርነት ወጥታ ራሷን ችላ እየተራመደች በመሆኗ ከእነሱ የምትዋሰው ነገር የላትም፡፡” ብጹእ አቡነ ሕዝቅኤል
- “አቡነ መርቆሪዎስ ሳይወዳደሩ በቀድሞ የፕትርክና ስልጣናቸው ይቀጥሉ ማለትም መንፈሳዊው ህግ አይደግፈውም” ብጹእ አቡነ ሕዝቅኤል
- የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔ የተቃወሙት ዋና ጸሐፊው ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ አቀረቡ ....... Haratewahedo
- “ራሴን ከቅዱስ ሲኖዶስ አግልዬ ብሆን ኖሮ እዚህ አታገኙኝም ነበር፡፡” ብጹእ አቡነ ሕዝቅኤል
የአጉስታ ጽዮን ማርያም ቤተክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ
(አንድ አድርገን ጥር 16 2005 ዓ.ም)፡- ቦታው ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ከጦር ኃይሎች ወደ ወይራ ሰፈር ሲሄዱ ከ2 ኪሎሜትር በኋላ ከአጉስታ ልብስ ስፌት ፋብሪካ አለፍ ብሎ ይገኛል፡፡ በ14/05/2005 ዓ.ም ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ምክንያቱ እስከ አሁን ያልታወቀ አሳት የአጉስታ ጽዮን ማርያም ቤተክርስቲያን ላይ ከፍተኛ አደጋ አድርሷል ፤ ቤተመቅደሱ የተዘጋው ከጠዋቱ 3 ሰዓት በፊት ቢሆንም እሳቱ ግን የተነሳው 7 ሰዓት አካባቢ መሆኑ ሰዎችን አነጋግሯል ፤ ከቤተክርስቲያኒቱ በጣሪያ በኩል ትንሽ ትንሽ ጭስ መውጣት ከታየ በኋላ ብዙም ጊዜ ሳይሰጥ ነዳጅ የተርከፈከፈበት እስኪመስል ድረስ ተንቦገቦገ ፤ በደቂቃዎች ውስጥ በርካታ ሰዎች ከአካባቢው በመሰባሰብ እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ጥረት አደረጉ ፤ እሳቱን ለማጥፋት አካባቢው ላይ ባለው ነገር ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም በወቅቱ እሳቱን ማጥፋት ግን አልተቻለም ፤ ይህ ጉዳይ ከአቅም በላይ መሆኑን በመገንዘብ ለአዲስ አበባ እሳት አደጋ መስሪያ ቤት ስልክ ተደውሎ የነበረ ቢሆንም እነርሱ እስኪመጡ ድረስ እሳቱ ከፍተኛ ጉዳይ አድርሶ ነበር ፤ በቦታው የደረሱበት ሰዓትም ብዙ ነገሩ ወደ አመድነት የተቀየረበት ጊዜ ነበር ፤ ሕዝቡን እጅጉን ያስገረመው በውስጡ የነበሩት የእመቤታችን ፤ የቅዱስ ኡራኤልና ፤ የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሀንስ ታቦታት ምንም ያለመሆናቸው ጉዳይ ነበር ፤ ከዚህ በተጨማሪ ማገሩን የበላው እሳት አባቶች ቅዳሴ ላይ የሚይዙት የእንጨት የነሀስና የብር መስቀሎች እና የተለያዩ ቅዱሳት መጻህፍት ምንም እሳት ሳይነካቸው መገኝታቸው በምዕመኑን ዘንድ አግራሞትን ፈጥሯል ፡፡
ሕወሐት ለሁለት ተሰነጠቀ፤ ወረቀት ለአባለት ተበተነ
ኢየሩሳሌም አርአያ
ዛሬ በመቀሌ ለአባላ ትና አልፎም ለህዝቡ በተበተነ የትግርኛ ፅሁፍ እነ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሐዬ፣ ፀጋዬ በርሔ ከነባለቤታቸው እንዲሁም ሌሎች ከድርጅቱ እንዲባረሩ በተበተነው መግለጫ ተጠቁሞዋል። በመግለጫው፥ ከጀርባ አሉ የተባሉትና « የዚህ መኅንዲስ» ተብለው የተፈረጁት ስብሃት ነጋ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ከተባሉት መካከል በዋነኛነት ተፈርጀዋል። እነ ቴውድሮስ ሃጎስ፣አዜብ መስፍንና በረከት እጃቸው እንዳለበት የተነገረለት ይኸው መግለጫ ተከታዩን ይመስላል፤ «ተቆርቋሪ ለሆናችሁ የትግራይ ተወላጆ በሙሉ፤ «ድርጅትህ ሕወሐት እስከ ዛሬ ታግላ እዚህ ደረጃ አድርሰሃለች። በተለይም የሁሉም ነገር አድራጊና ፈጣሪ የነበረው ባለ ራዕይው መሪህ በቅርብ ጊዜ አጥተኽል።
Sunday, January 20, 2013
የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን 70 በመቶው የአመራር ቦታ በህወሀት አባለት የተያዘ ነው ተባለ
ኢሳት ዜና:-ግንቦት7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለኢሳት በላከው ሁለተኛ ጥናቱ ላይ እንዳመለከተው
በ11 መምሪያዎች የተዋቀረው በስሩ አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱስትሪዎቸን የሚያስተዳደርው የኢትዮጵያ ብረታ ብረት
እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን አስራ አንድ ትላልቅ መምሪያዎችና አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱሰትሪዎች በዋና ሀላፊነት፤
በዳይሬክተርነትና በምክትል ዳይረክትርነት የሚመሩ በ29 የከፍተኛ አመራር አባላት ነው።
ፍረደም ሐውስ የ 2013 ኢትዮጵያ ነጻነት የሌለባት ናት አለ
ኢሳት ዜና:-በአለም ላይ ያሉ አገሮችን ነጻነት ( ፍሪደም) በማወዳደር ሪፖርቱን የሚያወጣው አለማቀፋዊ እውቅና
ያለው ፍሪደም ሀውስ የ2013 ሪፖርቱን ይፋ ሲያደርግ እንደገለጠው ኢትዮጵያ ነጻነት የሌለባት አገር ናት
ብሎአታል።
ፍሪደም ሐውስ የአለም አገራትን ነጻነት የሰፈነባቸው ከፊል ነጻነት ያለባቸውና ነጻነት የሌለባቸው አገራት
በማለት በሶስት ከፍሎ የተመለከተ ሲሆን ፣ ነጻነት የሌለባቸው አገራት ተብለው የተፈረጁት መሰረታዊ የሆኑት የፖለቲካ
መብቶች የሌሉባቸው፣ እንዲሁም የሰቪል ነጻነቶች የተነፈጉባቸው አገሮች ናቸው።
Subscribe to:
Posts (Atom)


