Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Tuesday, January 29, 2013

አዲስ አበባ አጉስታ ጽዮን ማርያም ቤተክርስትያን ተቃጠለች


ዛሬ ጠዋት 2 ሰዓት ላይ የተነሳ ፎቶ


ቤታቸውን በፍቃደኝነት ዳግም በመስራት ላይ ያሉ ወጣቶች


ቀድሞ ቤተክርስቲያኒቱ እዚህ ቦታ ላይ ነበረች
  • ትላንትና ከቀኑ 7 ሰዓት በተነሳ እሳት ቤተክርስትያኒቱ ውስጥ ከሚገኙ ታቦታት   ከመጽፍትና ከመስቀል ውጪሙሉ በሙሉ አውድሟታል :: ቤተክርስቲያኒቱ በጠራራ ጸሀይ ፤ በቆርቆሮ የተሰራው ግድግዳ እና ድንገት በተነሳ እሳት በአንድነት በመሆን የደረሰውነ ጉዳት  ከፍ አድርገውታል
  • እስከ ዛሬ ከቀኑ 6 ሰዓት ድረስ ከ200 ሺህ ብር በላይ ተሰብስቧል ፤ በአሁኑ ሰዓት በርካታ ምዕመናኖች ቦታው ላይ በመገኝት ቤተክርስቲያኒቱን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ 
    •      ከትላንት ማታ ጀምሮ የተጀመረው ስራ አሁንም ቀጥሏል ፤ ቤተክርስቲያኒቱ ከተቃጠለች 24 ሰዓት ሳይሞላት ማገር አቆመው የጎን ቆርቆሮ የማልበስ ስራ ተጠናቋል፡፡
      •     አካባቢው ያለው ሰው ስራውን ለሚሰሩት ሰዎች እንጀራ ወጥ ፤ ለስላሳ ውሃ እና አስፈላጊ ነገሮችን በማቅረብ ከ48 ሰዓት በፊት ስራን ለመጨረስ እየተረባረበ ይገኛል
      •                የእሳቱን መነሻ አሁንም እየተጣራ ይገኛል  ; እሳት አደጋ ተደውሎለት በሰዓቱ ባለመምጣቱ አደጋውን የከፋ አድርጎታል 
  • የእመቤታችን የቅዱስ ዮሃንስና የቅዱስ ኡራኤል ታቦቶች ምንም አለመሆናቸው እጅጉን አስገርሟል
  • በርካታ ሰዎች እሳቱን ለማጥፋት ተረባርበው ነበር
  • ትላንትና 70 ሺ ብር ከምዕመኑ መሰብሰብ ተችሏል ፤ ዛሬ ጠዋትም ቤተክርስቲያኒን ለመስራት ብር እየተሰበሰበ ይገኛል
  • ዛሬ ጠዋት በርካታ ወጣቶች ቤተክርስቲያኒቱን ዳግም ለማቆም እየተረባረቡ ይገኛ
  • የአካባቢው ወጣቶች እሳቱን ለማጥፋት ያደረጉት መረባረብ እጅግ ያስገረመ ነበር ፤ አሁንም ቤቷን ለማቆን ያለ እረፍት እየሰሩ ይገኛል ፤
     

No comments:

Post a Comment