(ከመልዕክተ ተዋሕዶ - ዘሮኪ/ PDF)፦ እንግዲህ ላለፉት 20 ዓመታት ከችግራችን ጋር ተወልዶ፥ ያደገው መንግሥት ፥ አቋሙን በግልጽ
አሳውቆናል። “ነገ ልትዳሪ ነው ሲሏት፥ ካልታዘልኩ አላምንም” እንዳለችው ሙሽራ መሆኑ ይብቃን፥ እርማችንን እናውጣ። ስለ ነገ እናስብ፥ ስለ ቤተ ክርስቲያን
እናስብ፥ ስለ አባቶቻችን እናስብ። የግዴታ ማክሰኞን መጠበቅ ያለብን አይመስለኝም።
ቅዱስ ሲኖዶስ በመጪው ማክሰኞ በሚያደርገው ስብሰባ ላይ፥ ካስታወሰን መልዕክታችንን መነጋገር ያለብን፥ ዛሬንና
ነገ ብቻ ነው። የመንግሥትን አቋም ባይገርመንም የሚጠበቅ ስለሆነ ሰምተነዋል። የቅዱስ ሲኖዶስ ግን ማክሰኞ ይለይለታል። ቅዱስ ሲኖዶስ
የማነው ወይ የኛ የኦርቶዶክስያዊያኑ ነው!
አለበለዚያ፥ ተጠሪነቱ በቀጥታ ለመንግሥት ነው። እንደኔ እንደኔ የቅዱስ
ሲኖዶስም ቢሆን፥ ግልጽ ይመስለኛል። ይህንን ለመረዳት፥ ወደ ፊት
ሁለት ቀን ጠብቆ ማየት ሳይሆን፥ ወደ ኋላ ብዙ ዓመታትን ማስታወስ ይበቃል።





