ኢሳት ዜና:- በምክትል ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አቅራቢነት ማክሰኞ ዕለት የተሰጠው ወታደራዊ ሹመት ከብሔራዊ ተዋጽኦ አንጻር በመከላከያ ውስጥ ያለውን የቆየ ቅሬታ ማባባሱን ምንጮች ጠቆሙ፡፡
ትላንት
ከሕመማቸው በማገገም ላይ ባሉት ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የተሰጠው ወታደራዊ ሹመት 34 የመከላከያ ኮሎኔሎችን
ወደ ብርጋዴር ጄኔራል ያሳደገ ሲሆን ከነዚህ ሹማምንት መካከል ከግማሸ በላይ የሚሆኑት የቀድሞ የህወሃት ታጋዮች
መሆናቸው ከብሔር ተዋጽኦ አንጻር ወትሮም የነበረውን ውጥረት እንዳባባሰው ምንጫችን ጠቁመዋል፡፡






