Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Sunday, September 9, 2012

በጄነራል ሳሞራ ዩኑስ የሚመሩ የህወሀት አባላት ጀነራሎች የመለስ ቦታ የሚገባው ለኛ ነው የሚል ጥያቄ ማንሳታቸው ተሰማ

ኢሳት ዜና:-ከኢህአዴግ  ሥራ አስፈፃሚ ሾልከው  የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ ጀነራል ሳሞራ ዩኑስ እና በሥራቸው ያሉ የህወሀት ጀነራሎች ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ብቁ የሆነ ሰው ከነሱ መካከል ስላለ በመለስ ቦታ ምንም ዓይነት ሹመት እንዳይሰጥ  መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጀነራሎቹ፦“መለስን መተካት የሚችል ብቁ ሰው አለን። ከኛ ፈቃድና ዕውቅና ውጪ ማንም ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሾም አይችልም!”ነው ያሉት።የጀነራሎቹ መልዕክትና አቋም መሰማቱን ተከትሎ በኢህአዴግ አመራሮችና አባላት መካከል ጭንቀት መፈጠሩም ታውቋል።


ይህ በ እንዲህ እንዳለ ኢህአዴግ ሊቀ-መንበሩን እና ምክትል ሊቀመንበሩን  እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር የፊታችን ሴፕቴምበር 16 እንደሚመርጥ የኮሙኒኬሽን  ጽህፈት ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል ለብሉምበርግ ነግረውታል። የግንባሩ ሊቀመንበር የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆን እንደሚችል ቃል አቀባዩን አቶ ሽመልስ ከማልን በመጥቀስ ብሉምበርግ ዘግቧል።

የ አቶ መለስ ማረፍ በመንግስት ብዙሀን መገናኛ በተገለጸበት ወቅት ፤ምክትል  ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ፦”ተጠባባቂ ጠ/ሚ/ር” እንደሆኑ የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ በረከት ቢያስታውቁም፤ በ አሜሪካ የተመድ አምባሳደር ሱዛን ራይስን ጨምሮ በአቶ መለስ ቀብር ዕለት የተገኙ የውጪ አገር መሪዎች፦አቶ ሀይለማርያምን ፦”ተጠባባቂ ጠ/ሚ/ር እያሉ ቢጠሩም፤ እስካሁን ድረስ ሹመታቸው ሊጸድቅ አልቻለም።

የ አቶ ሀይለማርያም ሹመት የፊታችን መስከረም 16 ይጸድቃል ተብሎ በስፋት እየተጠበቀ ባለበት ጊዜ የህወሀት ጄነራሎቹ ያልተጠበቀ ጥያቄ ማንሳታቸው፤ የመለስን መሞት ተከትሎ በኢህአዴግ ውስጥ  እየተባባሰ የተፈጠረውን ሽኩቻ ይበልጥ ያወሳስበዋል ተብሎ ተፈርቶአል።

በ ኢትዮጵያ ከሚገኙ ወደ 60 የሚጠጉ ጀነራሎች 58 ቱ የህወሀት አባላት እንደሆኑ፤ የግንቦት ሰባት ራዲዮ ከነ ስም ዝርዝራቸው እና ከያዙት ሀላፊነት ጋር በዝርዝር ማቅረቡ አይዘነጋም።

ስለ ጉዳዩ አስተያየታቸውን ይሰጡ ዘንድ ኢሳት ያነጋገራቸው አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አገር ቤት ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ፤ ጀነራሎቹ አነሱት የተባለውን ጥያቄ እርሳቸውም እንደሰሙት በመጥቀስ፤ይሁንና  ካለውና ከሆነው ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት ኢህአዴግ አቶ ሀይለማርያምን ከመሾም ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለው አስረድተዋል።

“ከ እንግዲህ ከዚያ ውስጥ ሹመት እንስጥ ቢሉ፤ ከራሳቸው ጋር ብቻ ሳይሆን ከብዙሀኑ ህዝብና ከለጋሽ መንግስታት ጋር ጭምር ነው የሚጣሉት”ብለዋል-የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሩ።

የአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትርነት የማይጸድቅ ከሆነ፤ ኢህአዴግ መራሹ መንግስት  ዩናይትድስቴትስን ጨምሮ በለጋ ሽ አገሮች ዘንድ ከፍተኛ አጣብቂኝ እንደሚገባ ሌሎች የፖለቲካ ተንታኞችም  ሲናገሩ ይደመጣሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ ህወሀት ከትናንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ ” ታጋይ መለስ የትግራይን ህዝብ በብቃት በመምራት ከመሰል ጓዶቹ ጋር በመሆን ግንባር ቀደም ሚናውን የተጫወተ የህዝብ ልጅ ነበር ካለ በሁዋላ፣ ህወሐት ከውልደቱ ጀምሮ በድል እሰኪጠናቀቅ ድረስ ያጋጠሙ ውስብስብ ችግሮችን በመተንተንና መሠረታዊ መፍትሄዎቻቸውን በማስቀመጥ የመሪነት ሚና መጫወቱን ገልጧል።

No comments:

Post a Comment