Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Sunday, August 12, 2012

በማሌዥያ ጫት ይዛ የተገኘችው ኢትዮጵያዊ ተከሰሰች

ኢሳት ዜና:-ነሀሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የተከለከለ ዕጽ  በማዘዋወር የተጠረጠረችው ኢትዮጵያዊቷ የቤት እመቤት ጫት ይዛ በመገኘቷ ትናንትና በፍርድ ቤት ክስ እንደተመሰረተባት የተለያዩ የማሌዥያ የዜና አውታሮች ዘገቡ።

የ36 ዓመቷ ሙና መሃመድ ኢብራሂም፣ እ.ኤ.አ ሃሙስ ኦገስት 2/ 2012 የማሌዥያው  ኬ.ኤል ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ውስጥ  90 ኪሎግራም የሚመዝን ካቲኖን የተሰኘ እፅ ወይንም ጫት ይዛ በመገኘቷ በቁጥጥር ስር እንደዋለች ታውቋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በአርማጭሆ ወታደራዊ ጥቃት መፈፀሙን አስታወቀ

ኢሳት ዜና:-ነሀሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሕአግ በሰሜን ጎንደር አርማጭሆ ልዩ ስሙ አዋሳ በተሰኘ አካባቢ ከመንግስት ልዩ ሃይል ታጣቂ ጋር ሐምሌ 28-2004 ዓ∙ም ባካሄደው ውጊያ 11 የመንግስት ቡድን ቅጥረኞችን በመግደልና 19 በማቁሰል አንፀባራቂ ድል ማግኘቱን ለኢሳት በላከው መግለጫ አመልክቷል።

በእለቱ የግንባሩ  ሰራዊት የተለመደውን ታሪካዊ ጀብድ ሲያከናውን የአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ ድጋፍና አቀባበልም እንዳደረገለት ገልጧል።

ካለፉት ሁለት ወራት ጀምሮ የሚታየው ገንዘብ የማሸሽ እንቅስቃሴ ንግዱን እየጎዳ የኑሮውን ውድነትም እያባበሰው ነው ተባለ

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በአንድ የግል ባንክ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኛ ለኢሳት እንደገለጡት፣ የተለያዩ የውጭ እና የአገር ውስጥ ባለሀብቶች ባለፉት ሁለት ወራት ከዚህ በፊት ታይቶ ባልታወቀ ሁኔታ ገንዘባቸውን አሽሽተዋል። ይህንኑ ተከትሎም ንግድ ባንክ ለመድሀኒትና መሰረታዊ ለሚባሉት የፍጆታ እቃዎች መግዢያ ካልሆነ በስተቀር ፣ ማንኛውም ነጋዴ ሌተር ኦፍ ክሬዲት እንዳይከፍት መመሪያ አስተላልፎአል። እገዳው በአገሪቱ የሚታየው የዶላር እጥረት እስከሚቀረፍ ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ እንደሚጸና ታውቋል።

ብሄራዊ ባንክም ሆነ ንግድ ባንክ እስካሁን ድረስ የሰጡት ይፋዊ የሆነ መግለጫ  ባይኖርም፣ የባንክ ሰራተኞች ግን ዶላር በገፍ ወደ ውጭ አገር እየተሸኘ መሆኑ ለችግሩ ዋነኛው መንስኤ ሆኗል ብለው እንደሚያምኑ የባንክ ሰራተኛው ገልጠዋል። የአቶ መለስ ዜናዊ የደህንነት ሁኔታ በውል አለመታወቅ ባለሀብቶች ገንዘባቸውን ለማሸሻቸው ዋነኛ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ነው ሰራተኛው ግምታቸውን ያሰፈሩት።

Friday, August 10, 2012

የአቶ መለስ መሰወር የስልጣን ሽኩቻና ፍርሀትን ጋርጧል ተባለ

ኢሳት ዜና:-ነሀሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የአቶ መለስ ለረጅም ግዜ ከስልጣን መሰወር፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ድብቅ የስልጣን ሽኩቻ፤ በአፍሪካው ቀንድ ደግሞ፤ ፍርሀትን እንደፈጠረ ፋይናንሳል ታይምስ የተሰኘው ጋዜጣ ዘገበ።

መንግስት አቶ መለስ ከሕመማቸው እያገገሙ እንደሆነ ቢናገርም፤ የአቶ መለስ ዜናዊ መሰወር ግን የጎሳ ፖለቲካን አደጋዎች እንዲያገጡ በሚያደርግና፤ ስርአቱን ለአደጋ በሚያጋልጥበት መለኩ ድብቅ የስልጣን ሽኩቻን ጭሯል ሲል ፋይናንሻል ታይምስ ዘግቧል።

በደሴ ከተማ ሙስሊሞች ከፌደራል ፖሊስ ጋር ተጋጩ

ኢሳት ዜና:-ነሀሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የጁመኣን ሶላት ጸሎት ለማድረስ ዛሬ በደሴ አረብገንዳ የተሰባሰቡ ሙስሊሞች ከፖሊስ ጋር ሲጋጩ ውለዋል።

በደሴና አካባቢዋ የሚገኙ ሙስሊሞች አረብገንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው መስጊድ ለመስገድ በሚሰባሰቡበት ወቅት፣ በስፍራው ሲጠባበቁ የነበሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት በመስጊዱ ጸሎት ማድረስ አይቻልም በማለት መከልከላቸውን ተከትሎ ነው ችግሩ የተፈጠረው።

ገዢው ፓርቲ ህዝብን ያረጋጋሉ የተባሉ ካድሬዎችን ወደ ገጠር አሰማራ

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የአቶ መለስ ዜናዊ የጤና ሁኔታ ከፍተኛ የህዝብ የመነጋገሪያ አጀንዳ እንደሆነ በቀጠለበት በዚህ ወቅት፣ ገዢው ፓርቲ ህዝብን ለማሳመን ይችላሉ ብሎ የሚያስባቸውን ካድሬዎች ወደ ገጠር መላኩ ታውቓል።

የብአዴን ካድሬዎች በአማራ ክልል በሚገኙ ወረዳዎች ህዝቡን እንዲያረጋጉ እንዲሁም የህዝቡን ስሜት እንዲያጠኑና ወደ ማእከል ሪፖርት እንዲያደርጉ ተልከዋል። ካድሬዎቹ ህዝቡን ለማሳመን ምን ማለት እንዳለባቸው በትክክል እንደማያውቁ፣ ይልቁንም ራሳቸው ካድሬዎቹ በከፍተኛ ግራ መጋባት ውስጥ እንደሚገኙ ታውቋል።

ኢምሬት ውስጥ ሁለት ኢትዮጵያውያን እንስቶች በእሳት አደጋ ሞቱ

ኢሳት ዜና:-ነሀሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በኢምሬት አንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ባለፈው ማክሰኞ የተነሳ የእሳት ቃጠሎ የስድስት ሰዎች ሕይወት ሲቀጥፍ፣ ከነኚህም አንደኛዋ ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ መሆኗን  “ዘ-ናሽናል” የተሰኘው ድረ ገጽ ዘገበ።

“አጅማን” ከተማ አቅራቢያ “አል-ሃሚድያ” የተሰኘ አካባቢ በሚገኝ ቪላ ውስጥ በድንገት ቤታቸው ውስጥ እሳት መነሳቱን ያዩት እናት፣ አስቸኳይ እርዳታ እንዲደረግላቸው የስልክ ጥሪ ያደርጋሉ። ሆኖም በደቂቃዎች ልዩነት ከእሳቱ ይወጣ በነበረው ከፍተኛ ጭስና ንዳድ የተነሳ፣ የ7፣ የ11 እና የ14 ዓመት እድሜ ያላቸው ሴት ልጆቻቸው፣ እንዲሁም የኢንዶኔዥያና የኢትዮጵያ ዜግነት ያላቸው ሁለት የቤት ሰራተኞቻቸውን ጨምሮ እርሳቸውም ሲሞቱ፣ የ15 ዓመት ዕድሜ ያለው ልጃቸው ግን በመስኮት ዘሎ ሕይወቱን ማትረፉ ታውቋል።

ፍትህ ጋዜጣ ዛሬም እንዳትታተም ተከልክላለች

ግራ የገባኝ ግን ጋዜጣዋ የታገደችው በዝግ ችሎት መሆኑ ነው፡፡ እንድትወረስ የተወሰነውም በዝግ ችሎት ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ሶስተኛ ወንጀል ችሎት (በዝግ ችሎት) ሶስት ክስ እንደተመሰረተብኝ በሬዲዮ ሰማሁ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡- ዛሬ ከሶስት ጓደኞቼ ጋር ምስ እየበላሁ ሳለ በምግብ ቤቱ የሬዲዮ ፋና ዜና እየተላለፈ ነው፡፡ ዜናው ቀጥሏል፡፡ "የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ ሶስት ክሶች ተመሰረቱበት፡፡

ማስተዋል የህትመትና ማስታወቂያ ስራ ድርጅትም በተመስገን ላይ በቀረቡ ክሶች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ሁለተኛ ተከሳሽ ሆነዉ ጉዳያቸዉ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍረድ ቤት 16ተኛ ወንጀል ችሎት ታይቷል፡፡

ፌደራል ፖሊስ ለመጀመሪያ ጊዜ “የጁነዲን ሳዶን ባለቤት ያሰርኩት በሽብርተኝነት ጥርጥሬ ነው” አለ

ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ የአቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤት ወ/ሮ ሃቢባ መሐመድ ከሁለት ሣምንት በፊት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት ከሽብር ተግባር ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው መሆኑን ፖሊስ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ አደረገ ሲል ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው ሰንደቅ ጋዜጣ ዘገበ። 
የፌዴራል ፖሊስ የውጪና ሕዝብ ግንኙነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ኮማንደር አበበ ዘሚካኤል ስለጉዳዩ ከሰንደቅ ጋዜጣ ተጠይቀው በሰጡት ቃለ ምልልስ ወ/ሮ ሃቢባ የተያዙት ከተጠረጠሩበት ወንጀል ጋር በተያያዘ ጥብቅ ክትትል ሲደረግባቸው ቆይቶ ከፍ/ቤት በወጣ የመያዣ ትዕዛዝ መሠረት ነው። 

Thursday, August 9, 2012

በአማራ ክልል ባለስልጣናት በሕዝብ ታገቱ

ኢሳት ዜና:-ነሀሴ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በአማራ ክልል ባለስልጣናት በሕዝብ ታገቱ በእገታው ተሳትፈዋል የተባሉ 12 ወጣቶች በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ታሰሩ በአማራ ክልል የክልሉ ባለስልጣናትን ጨምሮ የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳዳሪዎች፣ የሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ ባለስልጣናትና ሌሎች የክብር እንግዶች ተሰርቶ ያልተጠናቀቀ መንገድ ተረክበዋል በማለት በአካባቢው ነዋሪዎች መታገታቸውን ሰንደቅ ዘገበ።