Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Saturday, August 4, 2012

ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ በኩዌት ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እራሷን አጠፋች

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
አረብ ታይምስ ትናንት ባወጣው ዘገባ እንደገለፀው ከሆነ፣ ኢትዮጵያዊቷ ትሰራበት የነበረው ቤት ውስጥ ራሷን የመግደል ሙከራ ስታደርግ ተይዛ ወደ ሆስፒታል ተወስዳ ስነልቦና ሕክምና እንድትወስድ ተደርጋ ነበር።

ሆኖም ከሆስፒታሉ ስትወጣ  “ጃሃራ” በሚባል ስፍራ ወደሚገኘው “አል-ነኢም” ፖሊስ ጣቢያ ተወስዳ በመታሰር በምርመራ ላይ ሳለች፤ የእስር ቤቱ መታጠቢያ ቤት ውስጥ አድርጋው በነበረው ሂጃብ  የራሷን ሕይወት አጥፍታ ተረኛው ፖሊስ እስረኞችን በሚጎበኝበት ወቅት አስከሬኗን ማግኘቱን ዘግቧል።

አረብ ታይምስ ሟቿ ኢትዮጵያዊ መሆኗን ከመግለጽ በቀር ስለማንነቷ የገለፀው ምንም አይነት መረጃ የለም።

ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን ሳዶ ይቅርታ አልጠይቅም አሉ

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ባለቤታቸው የታሰሩባቸው የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን ሳዶ፦”ይቅርታ ጠይቁ” በመባላቸውን በመጥቀስ፦” የሠራሁት ስህተት ስለሌለ የምጠይቀው ይቅርታ የለም” አሉ። ባለቤቴ  ከህፃናት ልጆች ተነጥላ ትክክለኛ ባልሆነ ማስረጃ ታስራብኛለች ሲሉም  አቤት አሉ።

ሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ  የባለቤታቸውን መታሰር አስመልክቶ በኢትዮ ቻነል እና በሰንደቅ ጋዜጦች ለወጡት ዜናዎች መልስ በሰጡበትና በዛሬው የ ኢትዮ ቻነል ጋዜጣ ላይ በታተመው ጽሁፋቸው  ፤በጋዜጦቹ የወጡትን ጽሁፎች ተከትሎ  ባለቤታቸው  ከሰሞኑ የ እስልምና ተከታዮች እንቅስቃሴ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ተደርጎ የሚወራው ስህተት እንደሆነ ገልጸዋል።

በደቡብ ክልል በፕሬዚዳንቱና በአፈ ጉባኤዋ መካከል በተፈጠረው ውዝግብ ምክር ቤቱ ለሁለት ተከፈለ

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ባለፈው ማክሰኞ የክልሉ ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከሲዳማ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ የአገር ሽማግሌዎችን ሰብስበው “የሲዳማ ጥያቄ ፣ ወቅታዊ አለመሆኑንና አብዛኛውን ህዝብ የማይወክል መሆኑን” ተናገሩ በማለት ለማግባባት ሞክረው እንደከሸፈባቸው መዘገባችን ይታወሳል።

ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ከሌሎች የመገናኛ ብዙሀን የተወከሉ ጋዜጠኞች በስፍራው ተገኝተው “የሲዳማ ጥያቄ  የጸረ ሰላም ሀይሎች ጥያቄ ነው” በማለት ይዘግባሉ ተብሎ ሲጠበቅ፣ ስብሰባው በውዝግብ ተደምድሟል።

የአቶ መለስ ዜናዊ መጨረሻ አሁንም የኢትዮጵያውያን ያልተመለሰ ጥያቄ ሆኗል

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
እጅግ ውስብስብ የሆኑ ሚስጢሮችን በማውጣት የሚታወቁት አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን የአቶ መለስን የደህንነት ሁኔታ ለማወቅ አለመቻላቸው ብዙዎችን አነጋግሯል። አንዳንድ ወገኖች የምእራባዊያን የመገናኛ ብዙሀን ከአሜሪካ ወይም ከአውሮፓ መንግስታት የ”ይለፍ መብራት” ካልበራላቸው፣ ዜናዎችን ለማውጣት ፈቃደኛ አይሆኑም በማለት ሲናገሩ ሌሎች ደግሞ ኢትዮጵያ የምእራባዊያን የመገናኛ ብዙሀን የምትስብ አገር ባለመሆኑዋ የመገናኛ ብዙሀኑ ትኩረት እንደነፈጉዋት ይገልጣሉ።

በመሀሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ ተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን ድረገጾች በመግባት ዜናዎችን በእየለቱ ይቃርማሉ። አንዳንድ ኢትዮጵያውያን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን ቦታ መራቅ ለኢትዮጵያ አዲስ ተስፋን ይዞ ሊመጣ ይችላል ሲሉ፣ ሌሎች ወገኖች ደግሞ፣ በፍትህ ጋዜጣ ላይ የደረሰውን በመፍራት ከእስካሁኑም የባሰ አፋኝ መንግስት እንዳይመጣ ይሰጋሉ።

የሱዳን የደህነት አባላት የቤንሻንጉል ነጻ አውጭ ድርጅትን መሪ ልጅ አሰሩ

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፳፯ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
መንግስት ሰሞኑን ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ነጻ አውጭ ድርጅት ሰራዊት አባላት ጋር ድርድር በማድረግ ስምምነት ላይ መድረሱን አስታውቆ ነበር።

የኢትዮ ቻነል እና የሳምሶን ማስታወቂያ ድርጅት ባለቤት የሆነው ሳምሶን ማሞ ከነ ባለቤቱ ታሰረ

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፳፯ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የኢትዮ-ቻናል ጋዜጣ ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የሳምሶን አድቨርታይዚንግ ዋና ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ሳምሶን ማሞ እና የኢትዮ-ቻናል ጋዜጣ አሳታሚ የዜድ ፕሬስ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ዘውድነሽ ታደሰ ባለፈው ሐሙስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል ::

በጋምቤላ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነርና ሌሎች 4 ባለስልጣናት ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ባለፉት ሁለት ወራት በጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች እንዲሁም የሼክ ሙሀመድ ሁሴን አላሙዲን ኩባንያ ሰራተኞች ላይ በተፈጸመው ጥቃት ፣ ከታጣቂዎች ጋር በመሆን ጥቃቱን አስፈጽመዋል የተባሉት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ያለመከሰስ መብታቸው በክልሉ ምክር ቤት እንዲነሳ ተደርጓል።

Friday, August 3, 2012

ሀገሪቱ በማን እየተመራች ነው?, በብስራት ወ/ሚካኤል

ሰው ከዚህች ዓለም ፍጡር አንዱ ብቻ ሳይሆን መኖሪያቸውን በምድር ያደረጉትንም እንዲገዛና እንዲጠቀም የተፈቀደለትም ጭምር ፍጡር ነው፡፡ ይህ ሲባል ግን እንደሚዋለድ እንደሚያድግ እና እንደሚሞት መረሳት የለበትም፤የሰው ልጅ ሟች ነውና፡፡

እንዳለመታደል ሆኖ የገዥው ቡድን መሪዎች ግን ብዙዎች ተሰውተው እዚህ የደረሱ መሆናቸው እንኳ ያሰቡት አሊያም የሚያስቡት አይመስልም፡፡እነኚህ ሰዎች ደግሞ ከታሪክና ትውልድ ሳይሆን ከአደጋ እንጂ ከሌላ መማርን የሚፈቅዱ መስልም፡፡ 

የአማራ ክልል ወጣቶች ማህበር ፕሬዚዳንት ከአገር ተሰደደ

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የአማራ ክልል የወጣቶች ማህበር ፕሬዚዳንት በመሆን ያገለገለው፣ በክልሉ ውስጥ በወጣቱ ዘንድ ከፍተኛ ከበሬታ ያተረፈውና ወጣቱን ለለውጥ ለማንቀሳቀስ ከፍተኛ ስራ መስራቱ የሚነገርለት ወጣት ዘመነ ካሴ እንዲሁም የህግ ምሩቃን የመሰረቱት የአባይ ፍሬዎች ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር የሆነው ከፍያለው ጌጡ ከገዢው ፓርቲ የደህንነት ሰዎች ክትትል አምልጠው ወደ ሶስተኛ አገር ተሰደዋል።

ከመለስ አስተዳደር በኋላ የሚጠበቁ ክስተቶች, በፕሮፌሰር መሳይ ከበደ


የፈላጭ ቆራጭ አምባገነናዊ ስርዓት እና በአንድ ግለሰብ ላይ የተከማቸ ስልጣን ዋንኛው ችግር፤ ቋማዊ የስልጣን ሽግግርን ሊያስተገብር አለማስቻሉ ነው፡፡ በአብዛኛው እንዲህ ያሉ የስልጣን ሽግግር መንገዶች በተጻፉ እና ዋጋ ባላቸው ሕገ መንግስቶች ውስጥ ተካተው ይገኛሉ፡፡ 

ቢሆንም ቅሉ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ እና ኃይልን በማንአለብኝነት የመጠቀም አካሄድ ከጥቅም ውጪ አድርጎ ለሚንዳቸው፣ ተቋማት ቅቡልነትንም ሆነ ህዝባዊ ከበሬታን ሊያተርፉ አይችሉም፡፡ ይልቁኑም ስልጣንን የማስተላለፍ ግድ-ባይነት በተለያዩ ተቀናቃኞች መሀል መራር ሽኩቻን ይቀሰቅሳል፡፡ የተቀናቃኞች እንደአሸን መፍላት፣ ሀይልን በማንአለብኝነት የመጠቀም ተፈጥሯዊ ውጤት ነው፡፡ ስልጣን/ ኃይል ከቅቡልነት ማዕቀፍ ውጪ ሲተገበር፤ ለስልጣን ተፎካካሪዎች የሚያስተላልፈው መልእክት ተነጥቆ መወሰድ ያለበት ነገር መሆኑን ነው፡፡ ይህም የተቀናቃኞችን ሽኩቻ ያንረዋል፡፡ ሌላው የፈላጭ ቆራጭ ኃይል መልፈስፈስ የሚያስከትለው ውጤት ለህዝባዊ አመጽ የመነቃቃት አዝማሚያን ነው፡፡