ኢሳት ዜና:-ሐምሌ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በትናንትናው እለት ከአዋሳ ከተማ በ26 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዋ ማልጋ ወረዳ በተፈጠረው
ግጭት 3 የፌደራል ፖሊስ አባላት በጽኑ መቁሰላቸውን የዘገብን ቢሆንም፣ ዛሬ ዘጋቢያችን ተዘዋውሮ ያጠናከረው መረጃ
እንደሚያመለክተው ከ19 በላይ ፖሊሶች እና ከ20 በላይ ነዋሪዎች በጽኑ ቆስለዋል።
አናታቸው የተፈነከተ ፣ እግራቸው የተሰበረ፣ እንዲሁም በጥይት የቆሰሉ የፌደራል ፖሊስ አባላት መንገድ ላይ
ወድቀው ይታዩ ነበር። በገበያ ላይ የነበረው የአካባቢው ህዝብ ባገኘው መሳሪያ ሁሉ በመጠቀም ከፖሊሶች ጋር ግብ ግብ
የገጠመ ሲሆን፣ መሳሪያ የታጠቁ ነዋሪዎች፣ አፈሙዛቸውን ወደ ፖሊሶች በማዞር በርካቶችን አቁስለዋል።









