Journalist Eskinder Nega |
ኢሳት ዜና:-በሽብር ወንጀል ተከሶ 18 ዓመታት የግፍ እስር የተፈረደበት ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ዛሬ
ረፋዱ ላይ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ለማቅረብ ተገኝቶ ነበር። እስክንድር ይግባኝ ለማለት ዝግጅቱን ያጠናቀቀ
ቢሆንም፣ የይግባኙን ሰነድና ለፍርድ ቤት ሊያቀርበው ያዘጋጀውን የወረቀት ማስታወሺያዎች የቃሊቲ እስር ቤት ፖሊሶች
ስለነጠቁት ሳይችል ቀርቷል።
ጋዜጠኛ እስክንድር ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ለእስር ቤት ፖሊሶች ትእዛዝ እንዲጻፍለትና አጭር ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።
የጠቅላይ
ፍርድ ቤት መሀል ዳኛ ፣ ዳኘ መላኩ፣ ቀኝ ዳኛ በላቸው አንሲሾ፣ እና ስማቸው ያልተጠቀሰ ግራ ዳኛ እስክንድር
ባቀረበው አቤቱታ ላይ ከተነጋገሩ በሁዋላ ፣ የማረሚያ ቤቱን ተወካይ ፖሊስ ጠርተው የእስክንድርን ማስታወሺያዎች
ለምን እንደቀሙ ጠይቀዋል።
የእስር ቤቱ ተወካይ በበኩላቸው “እስረኛው እንደማንኛውም እስረኛ መያዙን ፣
በእርሱ ላይ የተለየ በደል አለመፈጸማቸውን” ጠቅሰው፣ ” ነገር ግን ወረቀቶቹ በእስር ቤት ሀላፊዎች እንዲመረመሩ
እና ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ቢጠየቅም ፈቀደኛ ባለመሆኑ ነጥቀነዋል፣ ወረቀቶቹ እንዲታዩ ከፈቀደ ጽሁፉን ተመልክተን
እና ማህተም አድርገን ከማረሚያ ቤት እንዲያወጣ እንፈቅዳለን” ብለዋል።
ጋዜጠኛ እስክንድር ” እኔ ለመከራከር ዝግጁ ነኝ፣ ስለዚህ ቀጠሮየ አጭር ይሁንልኝ” በማለት ፍርድ ቤቱን የጠየቀ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱም ለህዳር 13 ቀን 2005 ዓም ቀጠሮ ሰጥቶ ችሎቱ ተበትኖአል። ጋዜጠኛ እስክንድር በ4 ፖሊሶች ታጅቦ እና እጆቹ በካቴና ታስረው ፍርድ ቤት ቀርቧል። የህሊና እስረኛው እስክንድር ነጋ የ2012 የፔን ፍሪደም አዋርድ አሸናፊ መሆኑ ይታወቃል።
No comments:
Post a Comment