Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Tuesday, October 2, 2012

ሽማግሌ ሲሸብት ይጨምታል ፣ የእንጨት ሽበትስ? እንግዳ ታደሰ

Ato Sebhat Nega
የአቦይ ስብሃትን አማራና ኦርቶዶክስ  የሚል ያልተሞረደ  አነጋገር  በገዛ ተጋሩ ላይ ሳደምጥ ፣እንደ ወራጅ ዉሃ አሳዳሪ ማጣት እያለች የምትዘፍን  አቀንቃኝ  ዜማ ትዝ አለኝ ፡፡ ሽበታቸው ዉብታቸው ሳይሆን ፣ ሽበታቸው ነውራቸው የሆነባቸውን የንጨት ሽበቶችን በማምሻ እድሜያቸው ላይ ስትመለከቱ ምን ይሰማችኋል ? ባህላዊ እሴቶቻችንና – ሃይማኖታችን በጸያፍ እንዳንናገር የሚያግዱንን ያልተሞረዱ አነጋገሮች እንዳመጣላቸው የሚናገሩ፣ ቂመኛ እና የድፍ ማስወገጃ ቦይ የሆኑትን ፣ በአንድ ዘር ላይ ያነጣጠረ ያደፈ አነጋገርን ፣ ከውሃት አመሰራረት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ሳይለወጡ የሚናገሩትን የአቦይን አነጋገር ስትሰሙ   ምን ተሰማችሁ ? የአቦይ መንግሥት በቻይናዎች የሚደገፍ መንግሥት በመሆኑ ፣ ምናልባት ከቻይናዎች ጥቅስ ብንጠቅስላቸው ቶሎ ሊረዱት ስለሚችሉ እነሆ ጥቅሱ ፡፡


Harsh words and poor reasoning never settle anything. ችኩል ንግግሮችና ድኩማን ምክንያቶች መፍትሄ የማይሰጡ ስንኩሎች ናቸው ይመጥነው ይሆን ወደ አማርኛ ስንመልሰው ? በህዉሃት ሰፈር ቋንቋውም ተጠፋፍቶ ፣ አነጋገሩም አልተግባብቶ በሆነበት መንደር ፣ የሚባርቁ አነጋገሮች አገራችንን ለገጠማት ችግር አቧራውን አያስተኛም ፡፡ ይልቁንም ነገሮችን ወጥረው ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ ይወስዱታል ፡፡ አቦይ ስብሃት አሳዳሪ ያጡ ፣ እንደፈለጋቸው የሚፏልሉ ፥ አገሪቱን ከመሸታ ቤት ሆነው የሚመሩ ሆነው እስከመቼ እንደሚቀጥሉ የታወቀ ነገር የለም ፡፡ አንዳንዶች በአሁኑ ወቅት ‘’ ሲኮምር ነጋ ‘’ ብለው ሸገር ላይ በቅጽል ስም የሚጠሯቸው ስው ሹመትና ስልጣን ምን እንደሆነ ያቶ’ ኃይለማርያም መንግሥት ቶሽ ካላላቸው ፣ እኝህ ሰው በብሄረሰቦች መሃከል የበለጠ መካረር ፈጥረው አገሪቱን ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ እንዳይመሯት ከፍተኛ ስጋት አለኝ፡፡

የአቶ ኃይለማርያምን መመረጥ አስከትሎ ፣ ገዛ ተጋሩ በተባለው የትግርኛ ፓልቶክ ላይ ፣ ከንግዲህ ወዲያ ስልጣን ከአማራውና ከኦርቶዶክሱ እጅ ወጥቷል ፡፡ እጅግ ደስ ! ደስ ! ደስ ! ይበላችሁ ብለዋል ፡፡ምናልባት አቦይ በዚህ አነጋገራቸው ፣ ወያኔ አገር ከያዘ በኋላ የተወለደውን ትውልድ ሊያወናብዱበት ይችሉ ይሆናል ፡፡ 

የኦርቶዶክስ ሃይማኖት መነሻው ከየት ነው ? ንጉሳችን የነበሩት አጼ ዮሃንስ ይከተሉት የነበረው ኃይማኖት ምን ነበር ? አጼ ዮሃንስ በንግሥናቸው ዘመን ፣ አማርኛን የሥራ ቋንቋቸው እንዲሆን ያስገደዳቸው የትኛው አማራ ነበር ? የትግራይ ህዝብ ባብዛኛው እምነቱ የየትኛው ሃይማኖት ተከታይ ነው? ወደ አጼ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ስንመጣ ፣ አጼ ኃይለሥላሴ ወላጅ አባታቸው ከየትኛው ነገድ ነበሩ ? እናታቸውስ ? ኮለኔል መንግስቱስ አባታቸው ከየት ነገድ ነበሩ ? አቶ መለሥስ ከየትኛው ነገድ ነበሩ ? ብዙ መዘርዘር ይቻላል ፡፡ ይህን ለታሪክ ተመራማሪዎች እንተወው ፡፡

ብሄራዊ ትግል – የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ድርጅት የካቲት 1968 መግለጫ ,
ወያኔ ሀርነት ትግራይ በረሃ በነበረበት ወቅት ባወጣው ማንፌስቶው ገጽ 18 ላይ እንዲህ ይላል ፡፡ ‘’የትግራይ ህዝብ ብሄራዊ ትግል  ፀረ የአማራ ብሄራዊ ጭቆና ፣ ፀረ ኢምፔርያሊዝም እንዲሁም ፀረ ንኡስ ከበርቴ ለውጥ ነው ፡፡ስለዚህ  የአብዮታዊ ትግል ዓላማ ከባላባታዊ ሥራትና ከኢምፔርያሊዝም ነጻ የሆነ የትግራይ ዲሞክሪያሳዊ ሪፓብሊክ ማቋቋም ይሆናል’’ ፡፡ አራት ነጥብ ፡፡

በዚህ ማንፌስቶ ላይ በዝርዝር ብንሄድበት ፣ በአብዛኛው የሞላው ጥላቻ ከምኒሊክ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ ፣ ጸረ ሸዋዊ የሚል ቃላትን ያጨቀ ጸረ አማራ ቃላቶችን ነው ፡፡ አምሀራና ኢምፔርያሊዝም አንድ ናቸው ብሎ ጎረምሳው ስብሃት ነጋ ያኔ የጻፈው ዘረኛ ማንፌስቶ ፣ አቦይ ሆነውም  ከነ-ሸበታቸው ወርዷል ፡፡

ይህ ሁሉ ጥላቻ ከምን የመነጨ ነው ? ከቤተሰብ በተወረሰ የዘረኝነት ውርስ ወይስ ከባንዳ ቤተሰቦች በተወረሰ ቅርስ ? የአቦይን ትውልደ ውርስ በሚያሳይ መልኩ ፣ ኮለኔል አሥራት ቦጋለ ዜሮ ! ዜሮ ! ምርጫው ዜሮ በምትል አንዲት የታተመችበት ዓመተ ምህረቷን በማትጠቅስ ትንሽ ጥራዝ ውስጥ እንዲህ የሚል ጽሁፍ ስለአቦይ ጽፈዋል ፡፡
የቶ ስብሃት ነጋ አጎት/ የእናቱ ታላቅ ወንድም- ደጃዝማች ተክሉ መሸሻ በኢጣልያን ወረራ ዘመን በደቡብ ኢትዮጵያ የኢጣልያ ባንዳ ጦር አዛዥ ሆኖ ጣልያን በደቡብ ኢትዮጵያ የተሰለፈውን የኢትዮጵያ ጦር በታንክ በመድፍ ከአውሮፕላን በሚወርድ ቦንብና የመርዝ ጭስ አጥቅቶ ድል ካደረገ በኋላ የደቡብ ኢትዮጵያ ጦር አዛዥ የነበሩት ራስ ደስታ ዳምጠው ቆስለው ከጦር ሜዳ በማፈግፈግ በጉራጌ አካባቢ መስቃ ከተባለው ሥፍራ ተኝተው በስቃይ ላይ እያሉ ደጃዝማች ተክሉ እግር በግር ተከታትሎ ቁስለኛውን በመያዝ ከግንድ ጋር አስሮ በጭካኔ ደብድቦ ከገደላቸው በኋላ ራሳቸውን ረግጦ በመቆም ፎተግራፍ በመነሳት ለጣልያኑ ጌታው ግዳይ ያቀረበ ከሃዲ ባንዳ ነበር ፡፡ 

በሚል በዝችው ጥራዝ ገጽ 31 ላይ የጻፉ ሲሆን ፣ ለዚህም እንደዋቢ ማስረጃ HAILE SELASSIE’S WAR  ከተባለው የ-Anthony Mockler  መጽሃፍ ውስጥ ገጽ 173 ላይ ያገኙትን ታሪክ በማጣቀሻነት ገልጸዋል፡፡የዚህ መጣጥፍ ጸሃፊ የድርጊቱን ትክክለኝነት ለማረጋገጥ ይህን የአንቶኒ ሞክለር መጽሃፍ ገጽ 173 ላይ ሲያነብ ፣ ድርጊት ፈጻሚው አንድ የትግራይ ደጃዝማች ባንዳ ተክሉ መሸሻ የተባለ ሰው እንደሆነ ሲያረጋግጥ ፣ የጃንሆይ ልጅ የሆኑት የልዕልት ተናኘወርቅ ኃይለስላሴ ባለቤት ፣ ራስ ደስታ ዳምጠው ከቆሰሉበት የጦር ሜዳ በመሸሽ በትውልድ መንደራቸው መስቃን ውስጥ ከተደበቁበት ጎጆ ውስጥ ጎትቶ ከግንድ ጋር በማሰር ይህ ሰው እንደገደላቸው አንቶኒ ጽፏል ፡፡ ባንዳው ተክሉ መሸሻ ግን የአቦይ ስብሃት አጎት እንደሆኑ አይጠቅስም ፡፡ ምናልባት የትግራይ ክልል ህዝብ ይህን ታሪክ ሊያረጋጥ ይችል ይሆናል፡፡

አቦይ በተደጋጋሚ በሚያገኙት የመገናኛ ብዙሃን ላይ , ሲጠየቁ ፣ እየሳቁ የዋህ ይመስላሉ ፡፡ ግን ቻይናዎች እንደሚሉት – A man may smile and smile, but still be a villain. በጥርሱ እየሳቀ እያለ የሚያስጠነቅቀን ዘፈን የማን ነበር ?

No comments:

Post a Comment