ኢሳት ዜና:-አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ከደቡብ ክልል ከወላይታ ብሄረሰብ የተገኙ መሆናቸው በክልሉ ነዋሪዎች
ዘንድ ምን ስሜት ፈጠረ የሚለውን ለማወቅ ኢሳት ከተለያዩ የክልሉ ነዋሪዎች ጋር ቃለምልልስ አድርጓል።
አንዳንድ ነዋሪዎች የእርሳቸው መመረጥ ደስታ የፈጠረላቸው መሆኑን ቢናገሩም፤ አብዛኞቹ ግን ሹመቱ የይስሙላ በመሆኑ ምንም ስሜት እንዳልሰጣቸው ይናገራሉ።
አቶ
ኦታራ ኦሼ የጋሞጎፋ ዞን ተወላጅ ናቸው። የአቶ ሀይለማርያም ሹመት ” ‘ ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም’ አይነት
ነው፤ ኢህአዴግ የ20 አመት ሳይሆን የ40 አመት ራእይ እናስፈጽማለን እያለ በሚናገርበት ጊዜ፤ ምን ይጠበቃል”
በማለት ለውጥ እንደማይመጣ ገልጠዋል::
ወጣት ዲንጋም የተባለው የዲላ ነዋሪ በበኩሉ የአቶ ሀይለማርያም
ደሳለኝ ሹመት ለውጥ ያመጣል የሚል እምነት እንደሌለው ገልጧል ። ወጣት ዲንጋማ እንደሚለው ግለሰቡ የተቅላይ
ሚኒስተርነቱን ድርሻ ከምር የያዙ ባለመሆኑ ፤ ለውጥ የመጣል ተብሎ በክልሉ ህዝብ እንደማይታሰብ ተናግሯል በአዋሳ
ከተማ ነዋሪ የሆኑት የተቃዋሚ ፓርቲ አባሉ አቶ ሲዳ ሀይሌ ደግሞ፤ድርጅቱ ኢህአዴግ እስካለ ድረስ የአቶ መለስ
መሄድና የአቶ ሀይለማርያም መምጣት_ ለውጥ እንደማያመጣ ገልጠዋል። <ኢህአዴግ ሄደ፤ ኢህአዴግ ተተካ
ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠቅመው የለም> ሲሉ አቶ ሲዳ አክለዋል
No comments:
Post a Comment