Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Sunday, June 10, 2012

የፌደራሉ መንግስትና የሲዳማ ዞን በአዋሳ እጣ ፈንታ ላይ ውጥረት የበዛበት ውይይት እያካሄዱ ነው

ኢሳት ዜና:- ሰኔ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የፌደራል መንግስቱ አዋሳን በስሩ ለማድረግ እቅድ እንዳለው ሲታወቅ፣ የሲዳማ ዞን በበኩሉ ድርጊቱን ይቃመዋል። በቅርቡ በተደረገው ውይይት ላይ አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር፣ የሲዳማ ዞን ባለስልጣናትም የፌደራል መንግስቱ ባለስልጣናት የሚመሩትን ስብሰባ ረግጠው መውጣታቸውንና ጉዳዩን ከፌደራል መንግስት ባለስልጣናት እውቅና ውጭ እያካሄዱት ነው።

አዲሱ ውዝግብ የአዋሳን ህዝብ ትኩረት መያዙም ታውቋል። በ1994 ኣም በፌደራል መንግስትና በዞኑ መካከል በተፈጠረው አለመግባባት  ከ40 እስከ 100 የሚደርሱ የሲዳማ ተወላጆች መገደላቸው ይታወሳል። የመለስ መንግስት ከፍተኛ የህዝብ እልቂት ያስከተለውን የቆየ ችግር መልሶ በማምጣት ሌላ ችግር ለመፍጠር ለምን እንደተነሳሳ ግልጽ የሆነ ነገር የለም ይላሉ የአካባቢው ነዋሪዎች።

በሌላ ዜና ደግሞ በወላይታ ዞን የሚኖሩ መምህራን በአዲስ ራእይ ላይ በወጣ ጽሁፍ ውይይት ለማድረግ በሚል ለአንድ ሳምንት ትምህርት እንዲዘጋ መደረጉ በመምህራን እና በተማሪዎች ተቃውሞ ቀርቦበታል። በፈተና ወቅት ለመምህራን የፖለቲካ ስልጠና በመስጠት ትምህርት እንዲዘጋ ማድረጋቸውን   መምህራን እና ተማሪዎች ቢገልጹም በመንግስት በኩል ግን ምንም አይነት የማስተካከያ እርምጃ አልተወሰደም።

በሌላ በኩል ደግሞ በዚሁ ከተማ አንድ የጋዜጣ አዟሪ በፖሊስ ተይዞ እስር ቤት ገብቷል። ጋዜጣ አዟሪው ፍትህ ጋዜጣን ሲያሰራጭ በነበረበት ጊዜ መያዙን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ከዚህ ቀደም የግል ጋዜጣ እንዳይሸጥ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ሲሰጠው እንደነበር ለማወቅ ተችሎአል።

No comments:

Post a Comment