Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Saturday, September 8, 2012

የጋንቤላው ተወላጅ እንግሊዝን ሊከሱ ነው

(Sept. 8) ከእንግሊዝ መንግስት በተገኘ ድጋፍ የሰብአዊ መብቴ ተጥሶብኛል ያሉ አንድ የጋምቤላ ተወላጅ ኢትዮጵያዊ፤ የእንግሊዝ መንግስትን ሊከሱ እንደሆነ ቢቢሲ ዘገበ። 

ስማቸው ያልተጠቀሰውና በስደተኝነት በኬንያ የሚገኙት ከሳሽ በጠበቆቻቸው በኩል እንደተናገሩት፤ በጋምቤላ አካባቢ በሚካሄድ የሰፈራ መርሀግብር የተነሳ፤ ከመሬታቸው እንደተፈናቀሉና እንደተደበደቡ፤ እንዲሁም ሴቶች ሲደፈሩ እንደተመለከቱ ተናግረዋል።


በጋምቤላ አካባቢ የሚደረገው የሰፈራ መርሀግብር፤ የእንግሊዝ አለምአቀፍ የዴቭሎፕመንት ድርጅት መምሪያ የገንዝብ ድጋፍ እንዳለበት ቢነገርም፤ ይህ መምሪያ ግን በኢትዮጵያ ውስጥ እንደዚህ ያሉ የሰፈራ መርሀግብሮች የሉኝም ሲል አስተባብሏል።

ኢትዮጵያ ከእንግሊዝ መንግስት ልገሳ ተቋዳሽ አገሮች አንዷ ስትሆን፤ የእንግሊዝ መንግስት፤ በኢትዮጵያ መሰረታዊ አቅርቦቶችን ለመጠበቅ በያዘው መርሀ ግብር የተመደበ ገንዘብ፤ ለግዴታ የሰፈራ መርሀ ግብር እንደዋለ የከሳሽ ጠበቆች ይናገራሉ። በጋምቤላ በሚደረገው የግዴታ ሰፈራ 1.5 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ከመሬታቸው ተፈናቅለው ወደሌላ ስፍራ እንዲሰፍሩ መገደዳቸው ታውቋል።

በሎንደን፤ እንግሊዝ በሚገኝ አንድ የጥብቅና ድርጅት የተወከሉት የጋምቤላ ኢትዮጵያዊ፤ 6 ልጆች ሲኖሯቸው፤ እሳቸውና ቤተሰቦቻቸው በህዳር 2004 አመተ ምህረት ላይ፤ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ከመሬታቸው እንዲነሱ እንደተደረጉና፤ በዚህ ሂደትም ውስጥ ብዙ ሰዎች ሲደበደቡ፤ ሴቶችም ሲደፈሩ ማየታቸውን እንዲሁም፤ የግዴታ ሰፈራውን ተከትሎም አያሌ ኢትዮጵያዊያን የገቡበት እንደማይታወቅ ምስክርነት ሰጥተዋል።

ከመሬታቸው የተፈናቀሉት ኢትዮጵያዊያን በሰፈሩበት አዲስ ስፍራ የእርሻ መሬት፤ ምግብና ውሀ፤ እንዲሁም መሰረታዊ አቅርቦቶች እንደሚኖር ቃል ቢገባላቸውም፤ በአዲሱ የሰፈራ ስፍራ ግን ቃል የተገባላቸው ነገር በሙሉ እንደሌለ እማኞች ተናግረዋል። ከሳሹ ወደቀድሞ መሬታቸው ለመመለስ ሲሞክሩ፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት በመሳሪያ ሰደፍ እንደደበደቧቸውና፤ ወደጦር ካምፕ ወስደው እዳሰቃዩዋቸው ጨምረው ተናግረዋል።

አለማቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሁውመንራይትስ ወች ባለፈው መጋቢት ወር የጋምቤላውን የግዴታ ሰፈራ አውግዞ መግለጫ ማውጣቱ የሚታወቅ ሲሆን፤ ኢሳት በወቅቱ፤ በኢትዮጵያ በጋምቤላ አካባቢ ተገኝተው የሁውማን ራይትስ ወችን ሪፖርት የጻፉትን ተመራማሪ፤ ፌሊክስ ሆርንን ቃለምልልስ እንዳደረገላቸው ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment