Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Saturday, September 8, 2012

3.7 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል



(Sept. 8) ድርቅ አሁንም ለኢትዮጵያ ፈተና ሆኖ እንደሚቀጥልና፤ ከነሀሴ እስከ መጪው ታህሳስ ድረስ፤ 3.7 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው፤ የግብርና ሚኒስቴር አቶ ምትኩ ካሳ ገለጡ።

ከነሀሴ በፊት በነበሩት ስድስት ወራት ውስጥ፤ የምግብ ተረጂዎች ቁጥር 3.2 ሚሊዮን የነበረ ሲሆን፤ በቀጣዮቹ 4 ወራት ግን የተረጂዎች ቁጥር 16 በመቶ ጨምሮ፤ በአሁኑ ሰዓትና እስከሚቀጥለው ታህሳስ መጨረሻ፤ የተረጂዎች ቁጥር 3.7 ሚሊዮን እንደሚደርስ፤ የግብርና ሚኒስትሩ መናገራቸውን ካፒታል ኢትዮጵያ ዘግቧል።


ይሄንን የምብግ ፍላጎት ለመሸፈን፤ 314 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶንስ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልግና፤ ካለፈው አመት የተረፈ 120 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ምግብ እንዳለ፤ ተጨማሪ 194 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ግን ባስቸኳይ እንደሚያስፈልግ ታውቋል።

ከኢትዮጵያ ግብርና ሚኒስቴር በተገኘው መረጃ መሰረት፤ ከ3.7 ሚሊዮን ተረጂዎች ውስጥ 47 ከመቶው በሶማሊ፤ 27 በመቶው ከኦሮሚያ፤ 10 ከመቶው ከትግራይ፤ እንዲሁም 7.7 ከመቶው ከአማራ ክልል እንሚገኙ ታውቋል።

ባለፈው አመት በተመሳሳይ ወቅት 4.5 ሚሊዮን ህዝብ የምግብ እርዳታ ይፈልግ እንደነበርና፤ የኢትዮጵያ መንግስት ለአለምአቀፉ ማህበረሰብ፤ የ398.4 ሚሊዮን ዶላር የአስቸኳይ ግዜ እርዳታ ጠይቆ እንደነበር የካፒታል ዘገባ ያስረዳል።

ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ከ20 አመታት በፊት ደርግን ጥለው ስልጣን ሲይዙ የኢትዮጵያ ህዝብ በ20 አመት ውስጥ በቀን ሶስት ጊዜ እንደሚበላና ኑሮው በአዎንታዊ መልኩ እንደሚቀየር ቃል ቢገቡም፤ ኢህአዴግ ሰልጣን ከያዘ ጀምሮ ላለፊት 21 አመታት፤ በየአመቱ በአማካይ ከ3 እስከ4 ሚሊዮን ህዝብ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው፤ የግብርና ሚኒስቴርና የአለምአቀፍ ተቋማት መረጃዎች ይጠቁማሉ።

የምግብ እርዳታ ከሚፈልገው 3.7 ሚሊዮን ህዝብ በተጨማሪ፤ የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ በኢትዮጵያ ውስጥ የምግብ ዋጋ እንዳሻቀበና የጤፍ ዋጋ በ600 ብር አድጎ ወደ 2050 ብር መግባቱን በዘገባችን ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment