Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Friday, September 7, 2012

ኢትዮጵያዊው አርሶአደር የእንግሊዝን መንግስት ሊከስ ነው

ኢሳት ዜና:-አንድ ኢትዮጵያዊ አርሶአደር በእንግሊዝ የገንዘብ ድጋፍ የተቋቋመ ድርጅት የሰብአዊ መብቴን ጥሶብኛል ሲሉ ነው ክስ ለማቅረብ የተነሳሱት ።

ሚስተር ኦ የተባሉት ሰው ለእንግሊዝ ጠበቆች እንደተናገሩት በመንደር ምሰረታ መርሀ ግብር የተነሳ ከመሬታቸው ተፈናቅለዋል፣ ተገርፈዋል እንዲሁም አስገድዶ መድፈሮች ሲፈጸሙ ተመልክተዋል።  የአርሶአደር ኦ ጠበቆች እንዳሉት የመንደር መስረታው መርሀ ግብር ከእንግሊዝ አለማቀፍ የልማት ዲፓርትመንት የገንዘብ ድጋፍ አግኝቷል።

የልማት ትብብሩ መስሪያቤት በበኩሉ ለሰፈራ መርሀግብሩ ገንዘብ አለመስጠቱን አስታውቋል። በስደት ኬንያ ውስጥ የሚኖሩት በጋንቤላ የተወለዱት  አርሶአደር ኦ  የስድስት ልጆች አባት ናቸው። አርሶአደሩ ብዙ ሰዎች መደብደባቸውን፣ሴቶች መደፈራቸውንና ተወሰኑ ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁን  ለጠበቆች ተናግረዋል።

No comments:

Post a Comment