Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Friday, September 7, 2012

የአቶ መለስ እናት ወ/ሮ አለማሽ ገብረልዑል ቤተሰቦች ከአስመራ በአይጋ ፎረም ድረ ገጽ ላይ ያስተላለፉት የሀዘን መግለጫ

ትርጉም ኢየሩሳሌም አርአያ
“የሃዘን ማፅናኛ መግለጫ “
“ በኤርትራ ምድር እና በመላው አለም የምንገኝ የደጃዝማች ገብረልኡል ተስፋማርያም እና የአቶ ካህሱ መላ ቤተሰቦች የሆንን፤ በሞት በተለየን በምናፈቅረው፣ ልጃችን እና ወንድማችን፣የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ የተሰማን መሪር ሃዘን እየገለጽን ፤ ለዘመዶቹ ለቤተሰቡ እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጽናቱን ይስጠን እንላለን።


አቶ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ እና አፍሪካ ታሪክ ርሃብን ከሰፊው ህዝብ ለመንቀል ፣የታመመው እንዲፈወስ ፣መሃይሙ እንዲማር፣መብቱ የተገሰሰው ፍትህ እና ነጻነት እንዲከበርለት እና እንዲረጋገጥለት ፣ለአንድ ቀን እና ሰአት ሳያርፍ እና እፎይ ሳይል ፣ተወዳዳሪ የሌለው ዘላለማዊ የታሪክ ሃውልት ማኖሩ ፣ለህዝቡ እና ለቤተሰቡ የማይረሳ የድል ችቦ ፣የማይናድ ቅርስ ፣የማይጠፋ መብራት ፣ተጠብቆ የሚኖር ዘላለማዊ ክብር ፣. . . . ወዘተ ትቶ በማለፉ ፣የተሰማንን ትልቅ ኩራት እየገለጽን ፤በተለይ ለኢትዮጵያ እና ኤርትራ ህዝብ በተለይም ደግሞ ለመላው ቤተሰቡ የጀመረውን ስራ ሳይጨርስ ፣ገና በ57 አመት እድሜው ማለፉ ሃዘናችንን ጥልቅ መሪር እና በጣም ከባድ ሸክም አድርጎታል።

አቶ መለስ ዜናዊ እድሜውን ሙሉ ሲያከናውነው የቆየው ፣መልካም እና የተቀደሰ ተግባራት ባይኖር ያለምንም ማጋነን እና አድሎ የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት አሁን ላለበት ደረጃ ሊበቃ እንደማይችል በማመን ፣እርሱ የጀመረው ወደር የሌለው የአገር እና ህዝብ ግንባታ አጠናክረው እንደሚገፉበት እና እንደሚያጎለብቱት ያለንን እምነት እና ተስፋ በዚህ አጋጣሚ እንገልጻለን ።ለአቶ መለስ ደግሞ ያንን ሁሉ የህዝብ እና ቤተሰቡ ጸሎት እና መሪር ሃዘን ፈጣሪ አምላክ ሰምቶለት በመንግስተ ሰማያት ያኑረው ።

ከወይዘሮ አለማሽ ገብረሉልኡል ቤተሰቦች

No comments:

Post a Comment